ራስን ለማጥፋት ማሰብ ማለት ስለ ህይወት እና ስለ ወደፊት ውሸትን ማመን ማለት ነው።
ጭንቀት ስንፈራ ወይም በሆነ ነገር የለመድነውን ኡደት ስናዛባ የሚሰማን ጤነኛ የሆነ አካላዊ መልስ ነው። አደጋ ስናይ፤ እውነት ይሁን ወይም አዕምሯችን ውስጥ ያለ - በፍጥነት ሰውነታችን ወደ መከላከል ይገባል፤ “መጋፈጥ ወይም መሮጥ” ወደ ሚባለው አፀፋዊ መልስ ወይም የጭንቀት መልስ ወዲያው ለመመለስ ይገባል። የጭንቀት መልስ ሰውነታችን እኛን ለመጠበቅ የሚጠቀመው መንገድ ነው።
በእርግዝና መመሪያው ላይ አወንታዊ ውጤትን የሚያመለክቱትን እነዚያን ሁለት መስመሮች ባየሁበት ቀን መላው ዓለሜ ነበር ሙሉ በሙሉ የተገለባበጠው። የእያንዳንዷን ሴት አስከፊ ቅዠት እየኖርኩ ነበር፡፡
በአዕምሮዬ በጣም አስከፊ የሆኑ ሁኔታዎችን የማሰብ አሳዛኝ አዝማሚያ አለኝ። ተሰርቄ፣ ታስሬ፣ ከስራ ተባርሬ ፣ ተፋትቼ እና ተቀብሬ በሀሳቤ ስላለሁ። አእምሮዬ አንዳንድ ጊዜ ለመሆን የሚያስፈራ ቦታ ላይ አገኘዋለሁ።