እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን።-1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:19
ሁላችንም የምናልፍበት የህይወት መንገድ የተለያየ ይሁን እንጂ ይብዛም ይነስም ገመናዬ ብለን በውስጣችን አምቀን የያዝነውና የተጋፈጥነው ጉዳይ ነበረን፤ ምናልባትም ካለንበት ሁኔታ የወጣነው የረዳን፣ያዳመጠንና እውነተኛ የሆነ ፍቅር የለገሰን ሰው ስላጋጠመን ነው፡፡ .
በዚህ አስቸጋሪ የሂወት ጉዞአችን ወቅት አብሮን ከእኛ ጋር ሲጓዝ የነበረው ሰው ውስጥ፣ እንደዚያ ያዳምጠን በነበረው ጆሮው በኩል አንዳች ነገር ተምረናል፤ ያ! አስደናቂ ፍቅር የሚዳሰስ ፊትና ገጽታ ያለው መሆኑን ተምረናል፤ አስረግጬ ያለ ጥርጥር የምነግራችሁ እርሱ የኢየሱስ ክርስቶስ ገጽታ መሆኑን ነው፡፡
አሁንም ቢሆን በህይወታችን ገመናዬ ብለን የምንለው የህይወት ስንክ ሳር ይገጥመናል፤ ሆኖም ከገጠመን ስንክ ሳር በላይ ሀሴት የምናደርግበት የተትረፈረፈ ህይወትን አግኝተናል፡፡
እናም ይህንን የተትረፈረፈ ህይወት አንተም/አንቺም ታገኝ/ኚ ዘንድ ልንረዳህ/ሽ እንፈልጋለን!
እኛ ሁላችንም የሆነ ተጨማሪ ነገር (አላማችንን ለማሳካት፣ ወይም ማንነታችንን ለመግለጽ የሚረዳን ወይም ፍቅርን ለማግኘት) በናፍቆት እንደምንጠብቀው ወይም እንደምንራበው ሁሉ፤ እግዚአብሄርም የልቡ ናፍቆት እኛን የተወደዱ ወንድና ሴት ልጆቼ ብሎ መጥራት ነው፡፡
እግዚአብሄር የፈጠረን ህይወትን በሙላት እንድንኖርና እንድናጣጥማት ነው፡፡ ያለ ምንም መሰናክል እርሱን በግላችን እንድናውቀው ነው፤ የየቀኑ ህይወታችን ሀሴትና አላማ እንዲሁም ትርጉም የተሞላ እንዲሆን ተደርገን ተፈጥረናል፡፡
ነገር ግን እኛ ረክተን መኖር አልቻልንም ነበር፤ ምክንያቱም ትዕቢትና ኩራት ጀርባችንን ለእግዚአብሄር እንድንሰጥ አድርጎን ነበር፡፡ የገዛ መንገዳችንን በመምረጥ ሃጢያትን አደረግን፣ በዚህ መንገድ ነው እንግዲህ ሞት፣ ህመም፣ ክፋትና ብቸኝነት ወደ አለም የገባው፡፡
እውነታውን ለማመንና ለመቀበል ባንወድም በየቀኑ በራስ ወዳድነት እንመላለሳለ ፤ ራሳችንን አንደኛ ደረጃ ላይ እናስቀምጣለን፤ የተፈጠርነው ራስ ወዳድ ላልሆነው ፍቅር ሆኖ እያለ ራስ ወዳድነትን ግን እንመርጣለን፡፡
በአንድ አመጸኛ የተሳሳተ ምርጫ ምክንያት ከእግዚአብሄር ጋር ያለው ግንኙነት ተበላሸ፡፡
ምንም እንኳን አመጸኞች ብንሆም እኛ ልንሞት የተገባውን ሞት እንዲሞትልን አንዱንና ብቸኛውን ደግሞም እጅግ የሚወደውን ልጁን ኢየሱስን እስኪሰጠን ድረስ እግዚአብሄር አፍቅሮናል፡፡ ኢየሱስ እኮ ፍጹም ነበር፤ ነገር ግን በሀጢያት ምክንያት ከግዚአብሄር ጋር ተበላሽቶ የነበረውን ግንኙነት ለመመለስ፣ ለማደስና የሀጢያታችንን ዕዳ ለመክፈል በመስቀል ላይ ወንጀለኛ ሊሞት የተገባውን ሞት ሞተ፡፡
እግዚአብሄር ኢየሱስን በሶስተኛው ቀን ከሙታን አስነስቶታል፤ ከዚያም ወደ ዘላለም ህይወት በክብር እንደገባ ሁሉ እኛንም ለዚህ ለከበረ ዘላለማዊ ሀይወት ይጋብዘናል፡፡
በእርሱና እርሱ ለእኛ በሰራው ስራ ለማመን ፈቃደኛ ለሆኑት ሁሉ ሙሉ፣ እውነተኛና የተትረፈረፈ ህይወትን ይሰጣል፡፡ ስጦታው ነጻ ነው፤ ሆኖም ኩራታችንና ትዕቢታችንን ያሳጣናል፡፡
አሁኑኑ ከኢየሱስ ጋር ኝኙነት ለመጀመር ከወሰንክ/ሽ እንደዚህ ብለህ/ሽ መጸለይ ትችላለህ/ያለሽ፡፡
“እግዚአብሄር ሆይ! እስከአሁን ድረስ በራሴ መንገድ ሀይወቴን ስመራ ኖሬአለሁ፤ ኢየሱስ እኔን ከራስ ወዳድነት ህይወት ነጻ ለማውጣት እንደሞተልኝ አምናለሁ፤ እባክህን ሃጢያቴን ሁሉ ይቅር በለኝ፡፡ ኢየሱስ ሞቶ ስላልቀረና ከሞት ስላስነሳኧው አመሰግንሃለሁ! የሰጠኧኝን ነጻ ህይወት እቀበላለሁኝ፤ ህይወቴ አሁን የአንተ ናት፤ እባክህ አንተ የምትፈልገውን ህይወት እንድንኖር እርዳኝ፡፡
ጌታን ለመቀበል ከወሰንክና አዲስ ህይወትን ከጀመርክ ወይም ማናገር የምትፈልገው ነገር ካለህ እባክህ አሳውቀን/ቂን፡፡ ሊጸልዩልህና/ሽና ሊያማክሩህ/ሽ እንዲሁም በጀመርከው/ሽው አዲስ ህይወት ሊያበረታቱህ/ሽ የሚችሉ አማካሪዎችና የጸሎት አገልጋዮች ጋር ልናገናኝህ እንወዳለን፡፡ አንድ ጊዜ ስምህንና/ሽንና አድራሻህን/ሽን በቅጹ ላይ ከሞላህ/ሽ ወዲያውኑ ከሚጸልዩልህና ከሚያማክሩህ ሰዎች ምላሽ ታገኛለህ/ሽ፡፡ ሁሉም ንግግሮች ነጻና ሚስጥራዊነታቸው የተጠበቀ መሆናቸውን ልንገልጽሎት እንወዳለን፡፡