ራስን ማጥፋት - ለህይወት ሌላ ዕድል መስጠት

ይሄን የምታነበው ምናልባት ራስህን ለማጥፋት አስበህ ሊሆን ይችላል። ወይም ሊያጠፋ ያሰበ ሰው ታውቅ ይሆናል። ምናልባት ለህይወት ተስፋ ያጣህ ሰው ብትሆን፤ እባክህን ማንበብህን ቀጥል። ህይወትህን ለማጥፋት አስበህ ጨርሰሃል ወይም ሞክረሃል። ልታስብ የምትችለው ሁሉ ህይወትህ ምን ያህል ተስፋ እንደሌለው፤ ይሄን ህይወትህን እንደዚህ መኖር መቀጠል እንደማትችል ይሆናል። ስቃዩ በጣም ከባድ ነው። ማንም የተሸከምከውን ሸክም ወይም ውስጥህ ያለውን የስሜት ብጥብጥ አይረዳህም። ግን አሁን እዚህ ነህ እና እዚህም ስለሆንክ እባክህን የሆነ ተስፋ ላካፍልህ ህይወትህ የተለየ እንዴት ሊሆን እንደሚችል እና ለህይወት ሌላ ዕድል ለምን መስጠት እንዳለብህ።

አማራጭ፡ ህይወትን ከማጥፋት ከመሞከር ውጪ ያለ ሌላ ነገር ለማድረግ እንድትሞክር በትህትና ጠይቅሃለሁ። ማማከር ወይም የሆነ ሰው ማውራትን ሞክረህ ምንም ለውጥ አላገኘህ ይሆናል። ሆኖም ግን በድጋሜ ሌሎች እርምጃዎችን ለማድረግ እንድትሞክር ጠይቅሃለሁ፤ በሌላ አቅጣጫ እንድትሄድ የሚረዱህ እርምጃዎች፤ ካጨናነቀህ ውስጥህ ካለው ራስህ ላይ ጥፋት ከሚያደርስ ሀሳብ የተለየ አቅጣጫ መውሰድ።

በመጀመሪያ ለምን ድብርት /Depression/ ውስጥ እንደገባህ መረዳት አለብህ። እንዲህ ልትል ትችላለህ “ ለምን እንደማይሳካልኝ አላውቅም፣ እዳ ውስጥ ነኝ፣ ሚስቴ/ባሌ ትታኝ/ትቶኝ ሄዳለች/ሄዷል፣ የምወደው ሰው ሞቷል፣ ስራ የለኝም፣ ብቸኛ ነኝ፣ ብዙ ችግሮች እና የከበዱህ ነገሮች ቢኖሩህም፤ ከዛም ባለፈ በነርቭ ስርዓትህ ውስጥ የኬሚካሎች አካላዊ እጥረት ጋር እየታገልክ ነው። ለሚሰማህ ድብርት ዋናው ምክንያት ይሄ ይሆናል። ብዙ ድብርት ውስጥ ያሉ ሰዎች፤ ስጥመት በኒውሮኬሚካል ማነስ ሊከሰትም እንደሚችል አያውቁም።

በቅርብ ጊዜ ከታዋቂው ማዮ ክሊኒክ የወጣ ፅሁፍ እንደሚገልፀው “የስነ ባህሪያችን ደካማ ጎን ከአካባቢያዊ ነገሮች ጋር ሲቀላቀል ልክ እንደ፡ ጭንቀት ወይም አካላዊ ህመም ኒውሮትራንዝሚተርስ የሚባሉት የአዕምሮ ኬሚካሎች ላይ መዛባት ሊያመጣ ይችላል ይሄም ድብርት ያስከትላል። በሶስቱ ኒውሮትራንዝሚተርስ - ሴሮቶኒን፣ ኖሪፓይነፍራይን እና ዶፓሚን ላይ የሚፈጠረው መዛባት - ከስጥመት ጋር የሚያያዝ ይመስላል።” እነዚህ ኬሚካሎች ሰዎች ትኩረት እንዲያደርጉ፤ ስሜታቸው እንዲስተካከል እና ጉልበታቸው እንዲጨምር በማድረግ ይረዳሉ። የታዘዙ መድሀኒቶችን በመውሰድ እና የተፈጥሮ መንገዶችን መጠቀም ልክ እንደ እንቅስቃሴ ማድረግ እና መንፈሳዊ ማንነታችንን ለማሳደግ ጊዜ መውሰድ እነዚህ ኒውሮኬሚካሎችን ለመጨመር ይረዳሉ። ሆኖም ግን ሌሎች ጉዳዮች ላይ መስራት አለብህ ልክ እንደ በሞት ወይም በፍቺ ያጣህው የምትወደው ሰው ካለ፤ ዝቅተኛ በራስ መተማመን፣ ፀፀት፣ ቅሬታ፣ ንዴት ወይም ያለፈ የፆታ ጥቃት ካለ። እንደነዚህ አይነት ችግሮች ወይም ማጣቶች ችላ መባል የለባቸውም እና በትክክለኛው መንገድ መፍትሄ ሊገኝላቸው ይገባል።

ወደ ማማከር ሄደህ ድብርት እንዳለብህ ተነግሮህ ይሆናል? ካልሆነ አሁኑኑ ወደ ቤተሰብ ሀኪም ወይም የአዕምሮ ሀኪም ወይም በቅርብ ካለ ድንገተኛ ክፍል ሂድና እርዳታ ጠይቅ። አማካሪ ማግኘት ትችላለህ ወይም ቅርብ ወዳለ የአዕምሮ ህክምና ማዕከል ሂድ። አሁን ደግሞ ማማከር አገልግሎት እየወሰድክ ከሆነ ቴራፒስትህን ወይም የአዕምሮ ሀኪምህን አግኝተህ ለዚህ ራስ የማጥፋት ሃሳብህ እርዳታ እንደሚያስፈልግህ ልትነግራቸው ይገባል። አብረውህ የቤተሰብ አባልህ ወይም ጓደኛህ አብሮህ ቢሄድ ጥሩ ነው። ድብርትን መረዳት እና ስሜትን መጋፈጥ

ሁሌም የሚሰማህን ነገር እንዲሁም ድብርትህን ማመን የለብህም። ስሜቶች በገሀድ አለም የሚታዩ እውነታዎች አይደሉም። ስሜቶች የግል አስተሳሰቦችን የሚያሳዩ ናቸው፤ እና ራስን ወደማጥፋት አስተሳሰብ የመራህን ሃሳብ መመርመር ያስፈልጋል።

ራስን ለማጥፋት ማሰብ ማለት ስለ ህይወት እና ስለ ወደፊት ውሸትን ማመን ማለት ነው። ከድሮ ጀምሮ ብዙ ሰዎች በድብርት ተሰቃይተዋል ግን ለስሜታቸው አልወደቁም ወይም ስሜታቸውን አላመኑትም። በሱ ፈንታ ለመቀጠል ጽናት ነበራቸው፤ የወደፊት ህይወታቸው የተሻለ እንደሚሆን በማመን ውስጥ ያለ ጽናት። አንተም ይሄ ጽናት ሊኖርህ ይችላል።

የስነ መለኮት ፕሮፌሰር የሆኑት ማርቲን ሉተር ብዙ ጊዜ የሚያጋጥመውን በጣም የወረደውን ስሜቱን እንዲህ ሲል ገለፀው “ከሳምንት በላይ ለሞት እና ሲኦል ደጅ ቀርቤ ነበር። መላው አካሌ ይንቀጠቀጥ ነበር። ክርስቶስ ጠፍቶብኝ ነበር። በእግዚአብሔር ላይ ተስፋ ቆርጬ እና ስሙን በመጥፎ ሳነሳ ነበር።” (Here I Stand, Abingdon Press)

ዶን ቤከር ፓስተር እና ጸሀፊ ነው፤ ከድብርት ጋር ያለውን ልምድ እንዲህ ሲል ጻፈው፦ "ከእውነታ ውጭ የሆንኩ ነበር የምመስለው። ህይወት ብዥ ብላብኛለች፤ ከትኩረት ውጭ ነበረች። ህይወት ማስመሰል ብቻ እና ከእውነት የራቀች ነበር የምትመስለው። ማንም ግድ አይለውም ነበር። እግዚአብሔር እንኳን እንዳለ አይሰማኝም ነበር። በዛን ጊዜ ብቸኛው መፍትሔ ራስን ማጥፋት ብቻ ነበር።"

እነዚህ ሰዎች ስሜታቸውን አልተከተሉም። በሱ ፈንታ ድብርት ውስጥ የሚከቷቸውን ሃሳቦች ትተው ወደ ፊት ነው የሄዱት። ያጋጠማቸውን መሰናክል እና የመሸነፍ ስሜት ማሸነፍ ችለዋል። በአሉታዊ ስሜቶች እና ሃሳቦች ተመርተህ ከመንገድ መውጣት የለብህም።

ይሄ አስተሳሰብህን የምትጋፈጥበት ጊዜ ነው። ህይወትህን በጤነኛ እይታ የምታይበት ጊዜ ነው። ዋጋ ያለህ ሰው ነህ። ታስፈልጋለህ እና አስተሳሰብህን እና ባህሪህን መቀየር ትችላለህ እና ህይወትህን የተሻለ ማዳረግ ትችላለህ! እግዚአብሔር ተስፋ እንዲሰጥህ እድል እንድትሰጠው እለምንሃለሁ። ምን ማድረግ እንደሚችል ለምን አታይም? በእውነት እንዴት ህይወትህን እንደሚቀይር፤ የተጣለውን እንደሚያነሳ እና ለጠፉት ተስፋ ሲሰጥ አይቻለሁ። ራስህን ጠይቅ

§ ከድብርቴ ስር ያሉት ስሜቶች ምንድን ናቸው?

§ ዝቅተኛ በራስ መተማመን ነው ያለኝ?

§ የፀፀት ችግር ነው ያለብኝ?

§ ከሰው ጋር ባለኝ ግንኙነት ነው ችግር ያለብኝ?

§ የሆነ ነገርን ፈርቻለሁ?

§ የሆነው ሰው በማጣቴ ባለ ስሜት ነው እየተቸገርኩ ያለሁት?

§ ምን አይነት ሃሳቦች ናቸው አዕምሮዬን የሚመሩት?

§ እግዚአብሔርን ወደ መፈለግ ምን አይነት እርምጃ ነው ማድረግ ያለብኝ?

ተስፋ አትቁረጥ! አሁኑኑ ወደ ሚቀርብህ ሰው ሄደህ አውራው ምክንያቱም አስፈላጊ ሰው ነህ።

ተስፋ ከሚያስቆርጥ ስሜት በላይ ማለፍ ብዙ ጊዜ ድብርት የሚሰማቸው ሰዎች ደህና እንዲሆኑ የሚያደርጋቸውን ነገሮችች እያደረጉ አይደለም። ስጥመቱን ተዋግተህ ወደፊት መሄድ አለብህ። ስለ ስሜትህ እና ህይወትህ ከሆነ ሰው ጋር አውራ። ስሜትህን ለሆነ ሰው መግለጽ በጣም ጠቃሚ ነው። ከሆነ ሰው ጋር፤ በተለይ ከአማካሪህ ጋር ሆነህ ከስሜትህ በስተጀርባ ያለው ምን እንደሆነ ለማወቅ መሞከር ችግሩን ለመፍታት መጀመር ይረዳሃል።

ለአካላዊ ህክምና ሀኪም ጋር ሄደህ ያለብህን ድብርት ብትነግረው ወደ ሌላ አዕምሯዊ ህክምና ሊመራህ ትችላለህ። ምናልባትም የድብርት መድሀኒት መውሰድ ሊኖርብህ ይችላል፤ ይሄም ጥሩ ነው! ሁሌም እንቅስቃሴ ማድረግ እና የተመጣጠነ ምግብ መመገብ በጣም ይረዳሉ እና ሰውነታችን ያጣውን ኒውሮኬሚካል ሊጨምር ይችላል። በተጨማሪም ከሚያስብልህ ሰው፣ ጓደኛ፣ የቤተሰብ አባል ጋር እንዲሁም ቤተ-ክርስትያን በመሄድ ጊዜ ማሳለፍ ለህይወትህ ትርጉም እንድታገኝ ይረዳሃል።

ከየት መጀምር ነው ያለብህ አሁን ይሄን ጽሁፍ ካነበብከው በኋላ፡ ለህይወት ሌላ ዕድል ለመስጠት ታስባለህ? ህይወትህ በድጋሜ ለመገንባት እርምጃ ትጀምራለህ? እርዳታ ለመጠየቅ እርምጃ ትጀምራለህ? ሃሳብህ ውስጥ እየዞሩ ያሉትን ውሸቶች ላለማመን እንቢ ማለት አለብህ፤ እነዚህ ውሸቶች ናቸው ከእውነት ሊያርቁህ የሚሞክሩት። እውነቱ ዋጋ ያለህ እና ከፊትህ ያለው ህይወትህ ብሩህ እንደሆነ ነው። እውነቴን ነው። በእውነት ከፊትህ ያለው ህይወትህ ተስፋ አለው። ብዙ ሰዎች እርዳታ ሲያገኙ እና ሄደው የተሻለ ህይወት ሲኖሩ አይቻለሁ! በድጋሜ ለመጀመር የሚረዱህን ነገሮች በዝርዝር ጻፋቸው። እዚህ ጋር የተወሰኑ አማራጮች አሉ፡

  1. ከባለሙያ ጋር መመካከር

  2. አካላዊ ህክምና እና የታዘዘ መድሀኒትን መውሰድ

  3. ስፖርት

  4. ከቤተሰብ እና ጓደኛ ድጋፍ ማግኘት

  5. በሀዘን ውስጥ ለማለፍ መሞከር

  6. ሌላ፡ _____________________ (ባዶ ቦታውን ሙላ)

ራስህን ከመጉዳት ያወጣሁህ ይመስለኛል። እባክህን ለእርዳታ የሆነ ሰው አናግር፤ ልክ እዚህ ገመናዬ ላይ እንዳሉት ነጻ እና ምስጢር የሚጠብቁ አማካሪዎች። ፓስተርህ፣ አማካሪህ፣ ጓደኛህ፣ ሀኪምህ ጋር ደውል። ወደ ህይወት አንድ እርምጃ ሂድ እና አሁን ተስፋ አድርግ። አማካሪህ ጋር አውራ


ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡


እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡

የእርስዎ ፆታ:
የዕድሜ ክልል:

ተገቢውን አማካሪ እንዲመድብዎት የእርስዎ ፆታ እና ዕድሜ እንጠይቃለን። የአገልግሎት ውሎች & የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ.

እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!