አዕምሮዬ የሚያስፈራ ቦታ ነው

የመዛል ስሜት የሚሰሙኝን ጊዜያት አሳልፌያለሁ። ድንገተኛ የውጋት ስሜት ደረቴ አካባቢ ይሰማኛል እና ይሄም ልቤ እንደፈነዳ ወይም በልብ ድካም ልሞት ጫፍ ላይ እንደደረስኩ ያሳምነኛል። አሁን እንኳን ይሄን በምፅፍበት ሰዓት ደረቴ ላይ እያደገ ያለ ክብደት ይሰማኛል። እየታፈንኩ፣ እየሰመጥኩ እና ራሴን ልስት እንደደረስኩ አይነት ስሜቶችን በአንድ ላይ በአንድ ጊዜ እየተሰሙኝ ነው።

በጣም ልጅ እያለሁ ስለትናንሽ ነገሮች እጨነቅ ነበር። ምሳ ምንድን ነው የምበላው? በቂ ገንዘብ ካለኝ ብስኩት መግዛት እችላለሁ ወይ? የሚሉ ትናንሽ ነገሮች ያስጨንቁኝ ነበር። እያደኩ ስመጣ የመጨነቅ አዝማሚያዎቼ እየቀነሱ ነበር። ስለተለመዱ ነገሮች ብቻ ነበር የምጨነቀው፤ ጥሩ ውጤት ስለማገኘት፣ የትርፍ ጊዜ ስራዬን ስለማስጠበቅ እና አንድ ቀን ባል ስለማግኘት። ሆኖም ግን እናቴ የመጨረሻ ደረጃ የደረሰ የካንሰር ህመም እንዳለባት ታወቀ፤ ሁሉም ነገር ተቀየረ። ከዛ ጊዜ ጀምሮ ጭንቀቴ ተመለሰ። ቀድሜ በማላያቸው ወይም ልቆጣጠራቸው በማልችላቸው ነገሮች ሁሌም እንድሰጋ ሆኛለሁ።

  • እኔ ወይም ከቤተሰቤ መካከል አንዳችን በካንሰር መሞታችን የጊዜ ጉዳይ ነው ብዬ እፈራለሁ።
  • የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አብሬ ከተማርኳቸው ሰዎች ጋር የአንድነት ጊዜ ላይ ሳሳልፍ ከጠበቃው፣ ከሀኪሙ ወይም ስኬታማ ቢዝነስ ካለው ሰው አጠገብ ስቆም የውድቀት ስሜት ይሰማኛል ብዬ ፈራለሁ።
  • እርግዝናዎቼ ሁሉ ወደ ፅንስ መጨንገፍ ያመራሉ ብዬ እፈራለሁ - ምንም እንኳን ነፍሰ ጡር ሆኜ ባላውቅም። ዝርዝሩ እያለ ይቀጥላል።

    ሰዎችን አስከፋለሁ ብዬ እሰጋለሁ ስለዚህ ብዙ ጊዜ ወደ አደጋ የሚወስደኝን ነገር አልደፍርም። ሌሎች ሰዎች ባሉበት ቦታ ስለሚጨንቀኝ ማህበራዊ ስብሰባዎች ላይ አልሳተፍም። በአዕምሮዬ በጣም አስከፊ የሆኑ ሁኔታዎችን የማሰብ አሳዛኝ አዝማሚያ አለኝ። ተሰርቄ፣ ታስሬ፣ ከስራ ተባርሬ፣ ተፋትቼ እና ተቀብሬ በሀሳቤ ስላለሁ። አእምሮዬ አንዳንድ ጊዜ ለመሆን የሚያስፈራ ቦታ ላይ አገኘዋለሁ።

የሚያስፈራው ደግሞ ጭንቀቴ የሚነሳበት እንዲህ የሚባል ጊዜ የለውም። አንድ ጊዜ ከአለቃዬ ጋር ባለኝ ስብሰባ ላይ በጣም ፈርቼ ነበር እና በሚያሳፍር ሁኔታ ትንፋሼ ይቆራረጥ ነበር እና አንድ አረፍተ ነገር መናገር አቅቶኝ ነበር። ቤት ወስጥ ብቻዬ ሆኜ ስጨነቅ፤ ቀጥታ ማሰብ የምጀምረው የልብ ድካም ይይዘኝ እና ብቻዬን ሞታለሁ ብዬ ነው። ቲያትር ቤት ሆኜ ስልኬ መጥራት ሲጀምር፤ ወዲያውኑ ማሰብ የምጀምረው መጥፎ ነገር እንደተፈጠረ ነው እና እያለቀስኩ ብዙ ሁከት ሳልፈጥር እንዴት ከቲያትር ቤቱ እንደምወጣ ነው።

ሌሎች ሰዎች ባሉበት ቦታ ስለሚጨንቀኝ ማህበራዊ ስብሰባዎች ላይ አልሳተፍም። በአዕምሮዬ በጣም አስከፊ የሆኑ ሁኔታዎችን የማሰብ አሳዛኝ አዝማሚያ አለኝ። ተሰርቄ፣ ታስሬ፣ ከስራ ተባርሬ፣ ተፋትቼ እና ተቀብሬ በሀሳቤ ስላለሁ፡፡

አንድ ቦታ "ቅር እሰኛለሁ ብላችሁ ከጠበቃችሁ፤ መቼም ቅር አትሰኙም!" የሚል ፅሁፍ አንብቤ ነበር። ብዙ ሁኔታዎች ላይ የከፋውን እንዲጠብቅ ራሴን አዘጋጃለሁ። የሚያስደንቀው ነገር ያገባሁት ሰው በአጠቃላይ ነፃ እና ብዙ የማይጨነቅ ሰው ነው። ስለዚህ ሳያማክረኝ ማህበራዊ ህይወት ውስጥ እንድንሳተፍ ሲያደርገኝ እንዴት እንደምደነግጥ መገመት ትችላላችሁ። እውነት ለመናገር ትጋቱን እና አዲስ ነገሮችን ለመሞከር ያለውን ጥረት አደንቃለሁ፤ ትንሽ የሚያስፈሩ ቢሆኑም። ብዙ ጊዜ በእንባ ሆኜ እንዴት ነገሮች እንዳያሳስቡኝ ማድረግ እንደምችል ጠይቀዋለሁ። የመውደቅ ነፃነት እንዳለው በሚያውቅባቸው ሁኔታዎች ውስጥ ይደሰታል፣ እኔ በበኩሌ ለውድቀት በማሰብ ብቻ እደናገጣለሁ። እርስዎም “ምን ይሆናል” በሚለው ዓለም ውስጥ የሚኖሩ እና ወደ ሌላ አቅጣጫ የሚዞሩበት ቦታ ሳይኖር ጥግ ላይ እንደ ሆኑ ከተሰማዎት፣ ስለዚህ ጉዳይ ያነጋግሩን። ጭንቀት በጨለማ ክፍል ውስጥ እንኳን እርስዎን እንደሚከተል የሚያንዣብብ ጥላ ሆኖ ሊሰማዎ ይችላል። ማምለጥ የማይችሉ ሆኖ ሊሰማዎት ይችላል፣ ግን እባክዎን ብቻዎን አይጋፈጡት። መረጃዎን ከዚህ በታች ይተዉት እና ከታች ያለውን ፎርም ከሞሉ ከእኛ ቡድን አንድ ሰው መልስ ይሰጦታል።


ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡


እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡

የእርስዎ ፆታ:
የዕድሜ ክልል:

ተገቢውን አማካሪ እንዲመድብዎት የእርስዎ ፆታ እና ዕድሜ እንጠይቃለን። የአገልግሎት ውሎች & የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ.

እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!