ያልታቀደው እርግዝና

በእርግዝና መመሪያው ላይ አወንታዊ ውጤትን የሚያመለክቱትን እነዚያን ሁለት መስመሮች ባየሁበት ቀን መላው ዓለሜ ነበር ሙሉ በሙሉ የተገለባበጠው። የእያንዳንዷን ሴት አስከፊ ቅዠት እየኖርኩ ነበር፡፡ ያቺን ሴት ልሆን ነው። አባቴ በልጅነቴ ነው ያረፈው ለእናቴ አንድ ያለኋት ልጅ እኔ ነኝ። ማርገዜን ስትሰማ ምን ልትሆን እንደትችል ሳስበው ዞረብኝ።

ይህ ሁሉ የተፈጠረው በ21ኛ አመት የልደት ቀኔ ላይ ነበር፡፡ አብዛኛው ሰዎች በልደታቸው ቀን ጥቂት ከመጠን ያለፈ መጠጦችን በመጠጣት ይደሰታሉ በማግሰቱ ደግሞ ምን አልባት መጥፎ እራስ ምታት ይኖራቸዋል፡፡ የኔ አጋጣሚ ግን ከዚህ ለየት ይላል፡፡ ከመዝናናት ባለፈ ነገር ላይ ወድቄ ቀረሁ፡፡

ነፍሰ ጡር መሆኔን ባወኩበት ሰዓት እጮኛ አልነበረኝም ፣ ብቻዬን በፍርሃት ውስጥ ነበርኩ፡፡ ሄጄ የማማክረው ማንም ሰው እንደሌለኝ ተሰማኝ፡፡ በሰዓቱ በራሴ ላይ የመሸማቀቄ ፣ የሀፍረቴ ፣ራሴን የመጥላቴ ፣ ለራሴ ያለኝን ዋጋ የማጣቴ የነዚህን ሁሉ ሸክሞች ክብደት ልሸከመው ከምችለው በላይ ነበር፡፡

አንድ እንድትረዱልኝ የምፈልገው ነገር አንድ ሰክሬ ያመሸሁበት በስተመጨረሻም ከአንድ ወንድ ጋር ተኝቼ ራሴን ያገኘሁበት ምሽት ህይወቴን አልቀየረውም፡፡ ይልቅስ እዚህ ደረጃ ላይ ደርሼ እንድገኝ ያደረጉኝ ብዙ ትናንሽ ክስተቶች ነበሩ፡፡ ልክ ለመጀመሪያ ጊዜ ዕድሜዬ ሳይደርስ የአልኮል መጠጥ እንደጠጣሁበት ቀን ወይም ብዙም እንኳን ጠልቄ ለማላውቀው ወንድ ክብረ ንጽህናዬን እንደሰጠሁበት ቀን ወይም ደግሞ ለራሴ ያለኝን ክብር በማጣቴ በተደጋጋሚ እንደሰከርኩባቸውና እንደ ሴሰንኩባቸው ቀናቶች ወይም ደግሞ ጥበቃ እና ዋስትና እንዲሰማኝ እያልኩ ከወንድ ወንድ ሳቀያይርና ሳፈላልግ እንደሳለፍኳቸው ቀናቶች፡፡ ታውቃላችሁ ብዙ የተመሰቃቀሉና የተበላሹ ወሲባዊ ግንኙነቶች በኖሩኝ ቁጥር ይበልጥ ራሴን እንድጠላ የሚያደርጉና ዋጋ ቢስ እንደሆንኩ እንዲሰሙኝ የሚያደርጉ ሀሳቦች ወደ አዕምሮዬ ይመላለሳሉ፡፡

እነዚህ ሁሉ ነገሮች ታዲያ ተደማምረው ከቁጥጥር የወጣ ህይወት እንድመራ አድርገውኛል፡፡ ስለዚህም በ21ኛው የልደት በዓሌ ላይ መስከሬ - ምክንያታዊ ነው ለምን ልደቴ ስለነበረ - እና ከማላውቀው ሰው ጋር የወሲብ ግንኙነት መፈጸሜ ምንም አያስደንቅም፡፡ እነዛ ሁሉ ትናንሽ ነገሮች በስተመጨረሻ እዚህ የህይወት ደረጃ ላይ እንድደርስ ገንብተውኛል፡፡

በተስፋ መቁረጥ ስሜት በውስጤ እየጮህኩ ነበር አሁን ማን ሊወደኝ ይችላል

ለአንድም ሰው ቢሆን ማርገዜን አልተናገርኩም ነበር፡፡ እናም ምንም እንኳን በውስጤ ስህተት መሆኑን ባውቅም ግን ጽንሱን ለማስወረድ ቀጠሮ አስያዝኩኝ፡፡ እንደዛን ጊዜ በህይወቴ ብቸኝነት ተሰምቶኝ አያውቅም፡፡ በተስፋ መቁረጥ ስሜት በውስጤ እየጮህኩኝ ነበር አሁን ማን ሊወደኝ ይችላል። ጽንሱን ለማስወረድ እስከተቀጠርኩባት ቀን ድረስ የነበሩት ቀናቶች እጅግ ዘግናኝ ነበሩ፡፡ በጥፋተኝነት ስሜት፣ በመንፈስ ጭንቀት እና በብቸኝነት ስሜት ተጥለቅልቄ ነበር፡፡ መብላትም ሆነ መተኛት አቅቶኝ ነበር እና ሁሉንም ሰውም እርቅ ነበር፡፡

ከዚያም በሳምንቱ መጨረሻ ጽንሱን የማስወርድበት ቀን ከመድረሱ በፊት የሆነ ነገር ተለወጠ፡፡ በደንብ ልገልጸው የማልችለው ግን ትንሽ የሆነች የተስፋ እና የይቅርታ ስሜት ተሰማኝ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወር በላይ ካሳለፍኩበት የመንፈስ ጭንቀት፣ መበጥበጥ እና ሀፍረት ውስጥ እያለሁ እንደምወደድ ተሰማኝ፡፡ በተሰባረ እኔነቴ መካከል እያለሁ እንደምወደድ ተሰማኝ፡፡ ይህንን ሁሉ ነገር ለብቻዬ ማድረግ እንደሌለብኝ ተሰማኝ፡፡ የሆነን ሰው እኮ ማግኘት እችላለሁ፡፡ በርግጠኝነት የሆነ ሰው እኮ ለእኔ ሊደርስልኝ ይችላል፡፡ ያቺ ቀን ለዘለዓለሙ ለወጠችኝ፡፡ በመጨረሻም ቢያንስ ለአብሮ አደግ ጓደኛዬ ነፍሰጡር እንደሆንኩ ለመናገር እራሴን አደፋፈርኩኝ፡፡ ስነግራትም አልኮነነችኝም ይልቅስ አቀፈችኝ እና ብቻዬን እንዳልሆንኩ እና ለእናቴ መናገር እንዳለብኝ ነገረችኝ። እየፈራሁ ነገርኳት በጣም ደንግጣ ነበር ግን ልወስድ የነበረውን እርምጃ ስታውቅ “እንኳን ቀድመሽ ነገርሽኝ ትንሽ ቆይተሽ ቢሆን እኮ ላጣሽ እችል ነበር” ብላ አለቀሰች። ለእናቴ ከነገርኳት በኋላ ብዙ ሸክም ነው የቀለለልኝ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በህይወቴ ውስጥ ዋጋ ያለኝ መሆኑ ተሰማኝ ምንም እንኳን የተሰባበረችዋ ሴት ብሆንም ይቅር መባል እችላለሁ፡፡

አሁን ላይ አንዲት ቆንጅዬ ትንሽዬ ሴት ልጅ ከጸነስኩኝ 39 ሳምንቴ ነው ብዬ ስናገር በኩራት ነው፡፡ በቅርብ ጊዜያቶች ውስጥ ይህችን ውድ የህይወቴ ስጦታ በእጆቼ አቅፋታለሁ፡፡

ህይወት ምን ያህል ውድ ስጦታ እንደሆነች የመረዳት ጸጋን በመሰባበር መሃከልም እንኳን ቢሆን በጥቂቱ ስላጣጣምኩት እድለኛ ነኝ፡፡

እናንተስ ባልታቀደ እርግዝና ውስጥ ሆናችሁ ከራሳችሁ እና ከሁኔታው ጋር እየታገላችሁ ነውን በዚህ ሰዓት የተስፋ መቁረጥ እና የመጠመድ ስሜት እየተሰማችሁ ይሆናል ነገር ግን ብቻችሁን አይደላችሁም፡፡ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልታችሁ ከላካችሁልን ከቡድናችን የሆነ ሰው ያላችሁበትን ሁኔታና ታሪካችሁን ለመስማት ብሎም ተስፋ እንድታገኙ ለመርዳት ያነጋግራችኋል፡፡


ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡


እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡

የእርስዎ ፆታ:
የዕድሜ ክልል:

ተገቢውን አማካሪ እንዲመድብዎት የእርስዎ ፆታ እና ዕድሜ እንጠይቃለን። የአገልግሎት ውሎች & የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ.

እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!