ስሜትን ዝም ማሰኘት

ጭንቀት ስንፈራ ወይም በሆነ ነገር የለመድነውን ኡደት ስናዛባ የሚሰማን ጤነኛ የሆነ አካላዊ መልስ ነው። አደጋ ስናይ፤ እውነት ይሁን ወይም አዕምሯችን ውስጥ ያለ - በፍጥነት ሰውነታችን ወደ መከላከል ይገባል፤ “መጋፈጥ ወይም መሮጥ” ወደ ሚባለው አፀፋዊ መልስ ወይም የጭንቀት መልስ ወዲያው ለመመለስ ይገባል። የጭንቀት መልስ ሰውነታችን እኛን ለመጠበቅ የሚጠቀመው መንገድ ነው። በትክክል ከሰራ ትኩረት እንዲኖረን እና የነቃን እንድንሆን ይረዳናል። ድንገተኛ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ፤ በጭንቀት የምንመልሰው መልስ ህይወታችን ሊያድነው ይችላል፤ ራሳችንን ለመከላከል ተጨማሪ ጉልበት ይሰጠናል።

በአጠቃላይ ጭንቀት ከውጫዊ እና ውስጣዊ ነገሮች ጋር ይያያዛል።

ውጫዊ ነገሮች አካላዊ አካባቢያችንን ያካትታል ልክ እንደ ስራችን፣ ከሌሎች ጋር ያለን ግንኙነት፣ ቤታችን እና ሁሉም ሁኔታዎች፣ ተግዳሮቶች፣ የከበዱን ነገሮች እና በየቀኑ የምናገኛቸው የሚመቹን ነገሮችን ያካትታል።

ውስጣዊ ነገሮች የአመጋገብ ሁኔታችንን፣ አጠቃላይ የጤንነት እና የእንቅስቃሴ ደረጃችን፣ ስሜታዊ ጤንነታችን እና የምናገኘው የእንቅልፍ እና የእረፍት መጠንን ያካትታል። ጭንቀት የልብ በሽታ፣ ከፍተኛ ክብደት፣ ስጥመት እና ሁለተኛ ደረጃ የስኳር በሽታን ጨምሮ ሌሎች ብዙ ተያያዥ የጤና ችግሮች ያመጣል። ጭንቀትን መጋፈጫ ሁለት መንገዶች አሉ፡ ጭንቀትን በትዕግስት ማሳለፍ እና በፍጥነት ማገገም።

ጭንቀትን በትዕግስት ማሳለፍ ማለት በጫና ወይም በመከራ ውስጥ ሆነን በፊት የምናደርጋቸውን ነገሮች በተሳካ ሁኔታ ማድረግ መቀጠል ማለት ነው። በፍጥነት ማገገም ማለት ያሉንን ሰዋዊ ግብአቶችን ተጠቅመን መከራዎችን ያለ ምንም ጭንቀት በትዕግስት ማሳለፍ እና ማሸነፍ እና ሁኔታዎችን ተከትሎ ማደግ ማለት ነው። በሌላ ቃል ጭንቀትን በትዕግስት ማሳለፍ የሚያሳየው እስኪከብደን ድረስ ምን ያህል ጭንቀት መያዝ እንደምንችል ነው። የግል ስሜትን በፍጥነት እንዲያገግም ማድረግ በሌላ በኩል ለጭንቀት ሳንጋለጥ ምን ያህል መከራን መቋቋም እንደምንችል ያሳያል። ለጤንነታችን፣ ለደህንነታችን እና ለህይወታችን በአጠቃላይ ትርፋማ እንድንሆን በተለይ በስራ ቦታችን ላይ ስለሚረዳን በፍጥነት ማገገምን ማዳበር እና ማሳደግ ላይ ትኩረት ማድረግ አለብን።

ጭንቀትን በትዕግስት ማሳለፍ ማለት በጫና ወይም በመከራ ውስጥ ሆነን በፊት የምናደርጋቸውን ነገሮች በተሳካ ሁኔታ ማድረግ መቀጠል ማለት ነው።

ከስር ሰባት የግል ስሜታችንን በፍጥነት እንዲያገግም የሚረዱ እና የሚያሳድጉ እቅዶች፡ /

 1. ከምንወዳቸው ጋር ልዩ ጊዜ ማሳለፍ
  

  ከቤተሰባችን ጋር የጠበቀ ግንኙነት መገንባት የጭንቀት መጠናችንን ይቀንሳል እና ለሌሎች ማዘንን፣ ፍቅርን እና ድጋፍን እንጨምራለን። “አርብ ቀን የቤተሰብ እራት”ን ሁሉም ተሰብስቦ ጤነኛ ምግብ አዘጋጅቶ የሚበላበትን ዝግጅትን ማዘጋጀት። ከምንወዳቸው ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጦ ትርጉም ያላቸውን ጭውውቶችን መጫወት። ቲቪ ወይም ስልኮች አይፈቀዱም!

 2. ስፖርት / እንቅስቃሴ/
  

  ስፖርት ጭንቀትን ይቀንሳል፣ መተጣጠፍን እና ሚዛንን ይጨምራል፣ የደም ስኳርን ያስተካክላል እና ደም ግፊትን ይቆጣጠራል፣ በአጠቃላይ ሰውነትን ያጠነክራል እና ለህይወት ያለንን ቀና አመለካከት ይጨምራል። ጥሩ ስፖርት ካርዲዮ፣ ስትረች እና ክብደት ማንሳትን ያካትታል። አሜሪካ ህርት አሶስዬሽን ቢያንስ በሳምንት 150 ደቂቃ (ፈጣን እርምጃ ወይም ሳይክል መንዳት) መጠነኛ እንቅስቃሴ እንድናደርግ ይመክረናል፤ በተጨማሪም የጥንካሬ ስፖርት ቢያንስ በሳምንት ሁለት ቀን። በቀን ተቀን ህይወታችን ውስጥ ስፖርትን ስናካትት በደንብ መመገባችንን መዘንጋት የለብንም። ጤነኛ ያለሆነ አመጋገብን ለማስወገድ በየቀኑ ማስታወሻ መያዝ ጥሩ ነው። በደንብ ያለተነሳሳን ከመሰለን ተጠያቂ የሚያደርገን ጓደኛ መፈለግ። የምንተማመንበት ተጠያቂ የሚያደርገን ጓደኛ ወደ ስኬት እና ጤነኝነት በምናደርገው ቋሚ ጉዞ ላይ መሰረቱን በመስራት ይደግፉናል።

 3. ጎበዝ ካይሮፕራክተር መፈለግ
  

  በየቀኑ ከባድ የአንገት ህመም ወይም የጀርባ ቁስለት የሚሳማዎት ከሆነ እንዴት መዝናናት፣ ቀና አመለካከት ሊኖሮት እና ሊተባበሩ ይችላሉ? ካይሮፕራክተር የሚረዳበት ምንም አይነት መንገድ የለም። የጭንቀት መጠንን ሊጨምሩ የሚችሉትን ከፍተኛ ህመም የሚፈጥሩትን የተጣመመ አከርካሪያችንን የቱ ጋር እንደሆነ በማግኘት እና በማስተካከል ይረዳሉ። በቀን ተቀን ህይወታችን ካይሮፕራክቲክን በመጨመር በሰውነታችን እና አዕምሯችን ውስጥ የበለጠ ደስታ መጨመር እና ከጭንቀት በፍጥነት ማገገም እንችላለን።

 4. ዘና የማለት መንገዶችን መለማመድ
  

  አንዳንድ ሰዎች ዘና የማለት መንገዶችን ለመለማመድ ጊዜ እንደሌላቸው ይናገራሉ። እንግዲህ መኪና ያለ ነዳጅ እና በየጊዜ ዘይቱ ካልተቀየረለት መሄድ አይችልም። በተመሳሳይ ሁኔታ ሰውነታችን በደንብ መተንፈሰ እና ሌሎች መንገዶችን በመጠቀም ካላደስነው በሙሉ ችሎታው መስራት አይችልም።

 5. ጤነኛ አመጋገብ
  

  የየቀን ጭንቅት የምግብ አፈጫጨት ላይ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል፤ ከረዥም ጊዜ በኋላ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ሊያስከትል ይችላል። በተመሳሳይ ጊዜም ጤነኛ አመጋገብ ጭንቀት ውስጥ እንዳንገባ ሊከላከልልን ይችላል። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከመጠን በላይ ወፍራም ከሆኑ ሰዎች መካከል 41 ከመቶው ጤነኛ ያልሆነ አመጋገባቸው ምክንያት “በቂ ጊዜ” ስለሌላቸው እንደሆነ ያሳያል። በሲዲሲ የተሰራ ጥናት እንደሚያሳየው ክብደት ከቀነሱ እና በቀነሱት ክብደት ረዥም ጊዜ ከቆዩ ሰዎች 40 ከመቶው በቅድሚያ የሳምንት ምግባቸው በማቀዳቸው መሆኑን ይገልጻሉ። እናደግሞ የቁርስን አስፈላጊነት መዘንጋት የለብንም። ቁርስን መዝለል ከመጠን ላለፈ ውፍረት በከፍተኛ ሁኔታ አጋላጭ ነው። በየቀኑ አንቲኦክሲዳንትን መመገብ አለብን። በሰውነታችን ውስጥ ያሉትን አደገኛ ንጥረ ነገሮች የምንዋጋበት የተፈጥሮ መንገዶች ናቸው። ካንሰርን፣ የልብ ህመምን፣ ስትሮክን እና ከመጠን ያለፈ ክብደትን ለመከላከል ጎመን እና ሌሎች አረንጓዴ ነገሮችን መመገብ አለብን።

 6. ያልተቆራረጥ የስምንት ሰዓት እንቅልፍ እንድናገኝ ለራሳችን መፍቀድ
  

  ለስምንት ሰዓት ለመተኛት ጊዜ የማይኖረን ከሆነ ቀን ላይ ትንሽ እረፍት ማድረግ። ይሄ መንገድ ጭንቀትን ለመቀነስ ይረዳናል።፡ ወደ አልጋ ስንሄድ ስልካችንን ከመኝታ ክፍላችን ውጭ ማድረግ ወይም ቢያንስ ማጥፋት። ዘና የሚያደርጉ ሙዚቃዎችን መስማት። የተወሰኑ ሻማዎችን ማብራት። ደስ ስለሚያሰኝ ነገር ማሰብ። ከተማ ውስጥ የምንኖር ከሆነ፤ በከፍተኛ ድምጽ ላለመረበሽ የጆሮ ማዳመጫ መጠቀም። ማታ ላይ ለ8 ሰዓት መተኛት ካልቻልን፤ ቀን ላይ 1-2 ጊዜ ትንሽ እንቅልፍ መተኛት። አቅምን ለማደስ እና ለአዲስ፣ ጠንካራ ጉልበት፣ አስተሳሰብ እና ቀና አመለካከት እንዲኖረን ይረዳናል።

 7. አመስጋኝ መሆን
  

  የምስጋና መጠናችንን ለመጨመር የምናመሰግናባቸውን ነገሮች የምንጽፍበት ማስታወሻ መጀመር። አንድ አለኝ እኔ ስለዚህ በየቀኑ ከመተኛቴ በፊት፤ ለመልካም ድርጊታቸው ወይም ደስ ስለሚል የድጋፍ ንግግራቸው አምስት የማመሰግናቸውን ሰዎች እጽፋለሁ። እነዚህን መልካም ጊዜያት ዝም ብዬ አላያቸውም እና በምላሹ የማመስገኛ ማስታወሻዬ ህይወት መልካም መሆኑን የማሳይበት ግልፅ ማስረጃ ነው፤ ይሄም በቀና አመለካከት፣ ተስፋ እና ጉጉት ያሳድርብኛል። እነዚህን መንገዶች መለማመድ በአካልም ሆነ በስሜት ጠንካራ እንድንሆን፤ በፈታኝ ጊዜያትም ተስፋ እንዲኖረን፣ ከቤተሰባችን፣ ጓደኞቻችን እና አብረውን -ከሚሰሩ ጋር ትርጉም ያለው ግንኙነት እንዲኖረን፤ የህይወታችን ጥራት እንዲጨምር እና የጭንቀት መጠናችን እንዲቀንስ ይረዱናል።

አንድ ሰው አንዲያማክሮት አና ኣብሮት አንዲጓዝ ከፈለጉ ከታች ያለውን ፎርም ይሙሉና ከእኛ አንድ ሰው በተቻለ ፍጥነት መልስ ይሰጣችኋል፤ሚስጥርዎ የተጠበቀ እና ሁልጊዜም በነፃ የሚሰጥ አገልግሎት ነው።


ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡


እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡

የእርስዎ ፆታ:
የዕድሜ ክልል:

ተገቢውን አማካሪ እንዲመድብዎት የእርስዎ ፆታ እና ዕድሜ እንጠይቃለን። የአገልግሎት ውሎች & የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ.

እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!