ነፍሰ ጡር እንደሆንኩኝ የምርመራ ውጤቴ ሲያረጋግጥ ጥልቅ ደስታ ውስጥ ነበርኩኝ። ነገር ግን በአገጬ አጠገብ የሆነ ትንሽ ጠጣር እጢ ሲወጣብኝ እነዚያ የደስታ ቀናት ወደ ሀዘን ቀናት ተቀየሩብኝ።
ከ24 ሰዓት በኋላ የኢንፌክሽን መከላከያ ቢሮ ያለችው ደወለች እና ኮቪድ እንዳለብኝ ነገረችኝ። በጣም ነው የደነገጥኩት። የኢንፌክሽን በሽታዎች ኮሜቴን አነጋገርኩ። የማቃቸው ሀኪሞች እና ከእዚህ በፊት አብሬያቸው የሰራኋቸው ምልክቶቼን ይጠይቁኛል፤ ምን አይነት እንክብካቤዎችን ማድረግ እንዳለብኝ ይመክሩኛል እና ወደ ድንገተኛ ክፍል ለምን መግባት እንዳለብኝ ያስረዱኝ ነበር እና ሌሎች ራሴን ለይቼ ማቆየት የምችልባቸውንም መንገዶች ይጠቁሙኝ ነበር።