ኮቪድ-19 እንዳለብኝ አወኩ

በጣም ደክሞኛል፣ አፍንጫዬ በፈሳሽ ተሞልቷል፣ ያስለኛል፣ ብርድ ብርድ ይለኛል እና ደረቴ ላይ ወጥሮ ይዞኛል። አንዳንዴ ትንፋሽም ያጥረኛል። ቫይረሱ ይዞኛል። ይሄ ነው ታሪኬ። ኮቪድ እንዳለብኝ ተመርምሬ አወኩ፡ እውነተኛው ህይወት ይሄ ነው?

በለይቶ ማቆያ ውስጥ ከገባሁ ስንት ጊዜ ሆነኝ? ከአርብ መጋቢት 4 2012 ጀምሮ። ስለ እዚህ ኮሮና ቫይረስ ከሰማሁ ትንሽ ቆይቻለሁ። እንደ ነርሶች፤ አብረውኝ የሚሰሩ እና እኔ የጤና ማዕከል ውስጥ መረጃ አለን ብለን ራሳችንን አኩራርተን ነበር። ይሄ ቫይረስ ሁላችንም የምናወራበት ነገር ነበር። ግን በአለም ዙሪያ ነበር። ለብዙ ወራት ወደ አውሮፓ ጉዞ አደርጋለሁ ብዬ ሳቅድ ነበር። የካቲት 23 ላይ ሌስቦን፣ አምስተርዳም፣ አየርላንድ እና ባርሴሎናን ለመጎብኘት ጉዞ ላይ ነበርኩ።

ባርሴሎና ግን አልደረስኩም። ወደ ሌስቦን የሄድንበት በረራ ባዶ ነበር ማለት ይቻላል። ለእኛ ሰፊ ቦታ ነበረው! ዙሪያዬ ያለውን ሁሉንም ነገር በሳኒታይዘር አፀዳሁ፤ በተደጋጋሚ እጄን በሳኒታይዘር አፀዳ ነበር እና ቫይታሚኖችን መዋጥ አላቆምኩም። ሌስቦን በጣም ደስ የምትል ሀገር ናት። አምስተርዳም በጀብድ የተሞላች ናት። አየርላንድ በአጭሩ ነው የተቋጨው።

ሀሙስ ንጋት ላይ (ወደ 1፡30 አካባቢ ይመስለኛል) አሜሪካ ግልፅ ያልሆነ የበረራ እገዳ እንዳደረገች በሚናገር ዜና ተነሳን። በዛን ሰዓት ኮቪድ-19 የአለም ዋና ዜና ሆኗል እና ወረርሽኝ ተብሎ ተፈርጆ ነበር። ስፔን የገደቦች አዘቅት ውስጥ እየገባች ነበር። አየርላንድ ውስጥ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው። በእንቅልፍ ልባችን በመደንገጣችን ወደ ኢትዮጵያ መመለስ አለብን ብለን ወሰንን እና ወዲያውኑ ቲኬት ቆረጥን። ከረዥም ሰዓት እንቅልፍ የሌለበት፤ ፍፁም ድካም የሞላበት በረራ በኋላ ቤት ደረስን። በጤና። የተመለስኩ ቀን ማግስት ጠዋት ላይ በጣም ደክሞኝ መንቀሳቀስ አቅቶኝ ነቃሁ። አፍንጫዬ በጣም ፈሳሽ ነበረው ግን ከወቅቶች መቀያየር እና ጉዞ ጋር የመጣ አለርጂክ ነው ብዬ አሰብኩ። ሀይለኛ ትኩሳት አልነበረኝም። ወደ ስራ ቦታዬ ደውዬ መቼ መመለስ እንደምችል ጠየኳቸው። ወረርሽኝ ስለነበረ አዎ ሁሉም ነረሶች ስራ እንዲገቡ ይፈልጉ ነበር።

ወደ አውሮፓ ተጉዤ ስለነበር የ14 ቀን የህክምና ፈቃድ ሰጡኝ እና ምንም አይነት ምልክት ቢኖርብኝ እንዳሳወቅ ነገሩኝ። እነሱ ይከታተሏቸዋል። የዛን ቀን አመሻሽ ላይ በጣም ያስለኝ ጀመር። ቴርሞሜትር ወስጄ ሙቀቴን ለካሁ እና ትንሽ ትኩሳቴ ጨምሯል። በእርግጥ ድንገተኛ ጉዞ ከማድረግ እና ከእንቅልፍ እጦት በኋላ ደህና እሆናለሁ ብዬ አላሰብኩም። መውሰድ ያለብኝን ቅድመ ጥንቃቄ ሁሉ ወሰድኩ። እጆቼ የ12 ሰዓት ተረኝነት ስራዬ ከጨረስኩ በኋላ እንደሚታጠቡት እና እንደሚፀዱት ንጹህ ነበሩ። ሁሉም ደህና ይሆናል። ጥቂት ቀናት ሰጥቼ አየዋለሁ። ለይቶ ማቇያ ውስጥ ስለሆንኩ በአጭሩ ያልቃል ብዬ አሰብኩ። የሚቀጥሉትን ሁለት ቀናት፤ በጣም ይደክመኝ ነበር፤ አፍንጫዬ ፈሳሹ እየጨመረ ሄደ፣ ያስለኛል፣ ትኩሳቴም ጨመረ እና ደረቴ ላይ ያፍነኝ ነበር። አንዳንዴም ትንፋሽ ያጥረኝ ነበር። የስራ ቦርሳዬ ከፍቼ ፐልስ ኦክዚሜትሬን አወጣሁ (ነርስ መሆን አንዳንዴ በጣም ተግባራዊ ያደርጋል!) የኦክስጅን መጠኔን ለመለካት። የኦክስጅን መጠኔ የተለመደው ላይ ነው ግን የልብ ምቴ ጨምሯል። የዛን ቀን ለስራ ቦታዬ ምልክቶቼን ሳስገባ “ኮቪድ-19 እንዳለብኝ ያምናሉ” ብዬ አሰብኩ ለራሴ። ከኢንፌክሽን መከላከል ክፍል ስልክ ተደወለልኝ። የደወለችው ብዙ የበሽተኞች ጉዳይ ላይ አብረን ሰርተናል፤ ወዲያው እሷ እንደሆነች ሳውቅ በጣም ነው ደስ ያለኝ፤ ከተለመደው ኮስተር ባለ ድምፅ እንዲህ አለችኝ

“የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግ ያለብሽ ይመስለኛል። የአንቺን ጉዳይ ወደ ጤና ቢሮ ልከዋለሁ ግን አሁን ላይ የሚቀርብሽ ሀኪም ጋር ደውይ እና ሙሉ የመተንፈሻ ምርመራ ያድርጉልሽ። ወደ ቢሮ መምጣት የሚፈቅዱልሽ አይመስለኝም። እንደዛ ከሆነ ሳትመጪ የምትመረመሪበትን መንገድ እንፈልጋለን። ምን እንደሚሉሽ አሳውቂኝ። ይሄ የሞባይል ቁጥሬ ነው፡ በየትኛውም ጊዜ ላይ ደውይልኝ ወይም መልዕክት ላኪልኝ” ሁሉንም የሚሰሙኝን ስሜቶች ዝም አሰኘኋቸው እና ወደ አዳበርኩት እና ምቾት ወደ ሚሰማኝ በጭንቀት ውስጥ መስራት ወደ ምትችለው ነርስ ስሜቴን ለወጥኩት። የሐኪሜ ቢሮ ወደ ኮቪድ-19 መመርመሪያ ጣቢያ ላከኝ፤ ከዛ ነርሷ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ነገረችኝ እና ተመረመርኩ እና ውጤት መጠበቅ ጀመርኩ።

ከ24 ሰዓት በኋላ የኢንፌክሽን መከላከያ ቢሮ ያለችው ደወለች እና ኮቪድ እንዳለብኝ ነገረችኝ። በጣም ነው የደነገጥኩት። የኢንፌክሽን በሽታዎች ኮሜቴን አነጋገርኩ። የማቃቸው ሀኪሞች እና ከእዚህ በፊት አብሬያቸው የሰራኋቸው ምልክቶቼን ይጠይቁኛል፤ ምን አይነት እንክብካቤዎችን ማድረግ እንዳለብኝ ይመክሩኛል እና ወደ ድንገተኛ ክፍል ለምን መግባት እንዳለብኝ ያስረዱኝ ነበር እና ሌሎች ራሴን ለይቼ ማቆየት የምችልባቸውንም መንገዶች ይጠቁሙኝ ነበር። ይሄ እውነት ነው? የሚቀጥሉት ቀናት በጣም ከባድ ነበሩ፤ አንድ አይነት ምልክቶች ነበሩ። ይብስብኛል ብዬ አላሰብኩም ነበር። ማንበብ የምችለውን ሁሉ ስለ ኮቪድ-19 አንብቤያለሁ፤ ሌሎች እንዲያደርጉት የማልመክረው ነገር ነው። ግን ዝም ማለት አልቻልኩም።

ሰዎች፣ አካላዊ ንኪኪ እና ከሰዎች መገናኘት በጣም የሚያስፈልገኝ ደረጃ ላይ ደረስኩ። በማህበረሰብ ውስጥ እንድኖር ሆኜ ነው የተፈጠርኩት።

ሙሉ በሙሉ ለይቶ ማቆያ ውስጥ መሆን ማለት አለምን በፍርሃት አያናዳት ያለው ቫይረስ ይዞኛል ማለት ብቻ ሳይሆን ግን ወደ ስራ መመለስ አልችልም እና መቼ እንደምችል አላወቅም ነበር። መለየት እና ለይቶ ማቆያ ውስጥ መግባት ቀላል ነው ብዬ አስቤ ነበር። ተለይቶ ብቻውን እንደሚኖር ሰው ህይወቴ ሙሉ እንደዚህ ነበር አሁን እስክፈተን ድረስ። ግን ሰዎች፣ አካላዊ ንኪኪ እና ከሰዎች መገናኘት በጣም የሚያስፈልገኝ ደረጃ ላይ ደረስኩ። በማህበረሰብ ውስጥ እንድኖር ሆኜ ነው የተፈጠርኩት። ሁለተኛው ሳምንት ላይ፤ ህመሙ ሲቀንስልኝ ምን እየተሰማኝ እንደሆነ መለየት ጀመርኩ። ሀዘን፣ ብቸኝነት እና ፀፀት ነበር የሚሰማኝ፡ * መቆጣጠር አለመቻል * ታካሚ መሆን * ጉዞዬ በአጭር መቋጨቱ * ስራ መስራት አለመቻል * ሌላ ሰው ማየት አለመቻል * በግድ እረፍት ማድረግ እና ዝርዝሩ እዚህ ላይ አያበቃም። በሆነው ያጣሁትን እያሰብኩ ሀዘን ውስጥ ነበርኩ። ነፃነት። ጤንነት። ማህበረሰብ።

ምልክቶቹ አሁንም አሉ፤ በእዚህ ሰዓት ቀንሰዋል ግን እንደ ድሮ ጉልበታም አይደለሁም። ስለዚህም አመሰግናለሁ። መቼም ካየሁት በላይ ብዙ መልካምነት እና ፍቅር እና ድጋፍ አይቻለሁ በእነዚህ ሁለት ሳምንታት። ገና እያገናዘብኩ ነው ምን እንደተፈጠረ፣ ምን እየሆነ እንዳለ እና ምን መሆን እንዳለበት። ግን ደግሞ እርግጠኛ ነኝ። እኔ መቆጣጠር እንደማልችል፤ ሰላም እንዳለ፤ መልካምነት እንዳለ፤ ፀጋ እንዳለ እና አላማ እንዳለው እርግጠኛ ነኝ። ልብ ወለድ ታሪክ ያልሆነ በሚታይ መልኩ፤ ለእነዚህ ለተሰበሩ ስሜቶች እና ነገሮች በወደፊት የሚታደሱበት ተስፋ አለ።

ይህንን ለብቻቹ መጋፈጥ የለባችሁም፥ ከታች ያለውን ፎርም ይሙሉና ከእኛ አንድ ሰው በተቻለ ፍጥነት መልስ ይሰጣችኋል፤ሚስጥርዎ የተጠበቀ እና ሁልጊዜም በነፃ የሚሰጥ አገልግሎት ነው፤ አማካሪዎቻችን ሰዎችን በመንገዳቸው በሀዘኔታ እና በማክበር ለማገዝ ፍቃደኛ የሆኑ መልካም ሰዎች ናቸው፡፡ እባክዎ ከእርሶ ጋር ግኑኝነታችን እንዲቀጥል ከስር ያለውን ፎርም ይሞሉ? ካልተጠቀሰ በስተቀር ሁሉንም መሙሏት ይጠበቃል፡፡


ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡


እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡

የእርስዎ ፆታ:
የዕድሜ ክልል:

ተገቢውን አማካሪ እንዲመድብዎት የእርስዎ ፆታ እና ዕድሜ እንጠይቃለን። የአገልግሎት ውሎች & የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ.

እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!