በህመሜ ውስጥ

ሰዎች ህመም ህይወትን ይለውጣል ሲሉ ሰምቻለሁ። ይህንንም ህይወቴን ሙሉ ለሙሉ የቀየረውን ከሰው ወደ ሰው የማይተላለፍ ቲቢ የሚባል በሽታ በታመምኩኝ ጊዜ በራሴ ህይወት አይቼዋለሁ።

ነፍሰጡር እንደሆንኩኝ የምርመራ ውጤቴ ሲያረጋግጥ በጣም ደስ አለኝ። በእኔ እርግዝና ሁሉም ሰው ደስ አለው፡፡ ዘመድ፣ ጓደኛ ሁሉም። በአገጬ አጠገብ የሆነ ትንሽ እጢ የሚመስል ነገር ሲወጣብኝ ግን እነዚያ የደስታ ቀናት ወደ ሀዘን ቀናት ተቀየሩብኝ። ሀኪሞች እጢውን አይተው ቲቢ እንደሆነ ቢጠረጥሩም ነፍሰ ጡር ስለሆንኩኝ እና ለበሽታው የምወስዳቸው ከባድ መድሀኒቶቹ እያደገ ያለውን ፅንስ ሊጎዱ ስለሚችሉ ህክምናውን መከታተል አልችልም። በጣም ነበር የተረበሽኩት። ቲቢ እንደሆነ በተረጋገጠ ጊዜ ቀለል ያሉ መድሀኒቶችን እየተጠቀምኩኝ እብጠቱ ሳይባባስ ልጄ እንድትወለድ እረዱኝ።

ነፍሰጡር ነበርኩኝ እና ለበሽታው የምወስዳቸው ከባድ መድሀኒቶች እያደገ ያለውን ፅንስ ሊጎዱት ይችላሉ።

እብጠቱ ሲቀንስ እኔ የተሸለኝ መስሎኝ ነበር ነገር ግን ወዲያው እንደገና ስለጀመረኝ መድሀኒት መጠቀም ጀመርኩኝ። መድሀኒት ስጀምር ህመም አልነበረኝም ግን እብጠቱ ይሄዳል ደግሞ ይመጣል፡፡ ለሁለት ወር ያህል በሽታውን ለመቆጣጠር ህክምና ከተደረገልኝ በኃላ እብጠቱ እንዳልጠፋ እና እንደውም መጠኑ እየጨመረ እንደሆነ አየሁኝ። ምንም እንኳን በጣም ጠንካራ እና ውድ መድሀኒቶችን እየተጠቀምኩኝ ከአመት በላይ ቢሆነኝም ጤናዬ ሳይመለስ በመክረሜ የቲቢ ስፔሻሊስት ሀኪም ለማናገር ወሰንኩኝ።

የተገኘብኝ የቲቢ በሽታ አይነት ከሰው ወደ ሰው የማይተላለፍ ቢሆንም እንኳን ገና አንድ አመት እንኳን ያልሞላትን ልጄን እና ሌሎች የቤተሰቤ አባላት ላይ እንዳይተላለፍ በጣም ነበር የምሰጋው። እኔን የያዘኝ እንዳይዛቸው እፈራለሁ።

በሽታው ከተገኘብኝ ከአምስት አመት በኃላም መድሀኒቱ አልተገኘልኝም። ህይወቴ ተዘበራረቀ። የቲቢ ስፔሻሊስት የሆነ በጣም ጥሩ ሀኪም እያከመኝ ነው። ነገር ግን የእኔ በሽታ መድሀኒቱን የሚቋቋም መሆኑን ሀኪሜ ስለተገነዘበ በጣም ከባድ መድሀኒቶችን እና ክትባቶቹን እየሰጠኝ በሽታውን ለማጥፋት ጥረት እያደረገ ነው። እጢው የቴኒስ ኳስ ሲያክል ቀላል የቀዶ ጥገና በማድረግ እጢው እንዲወጣ ተደረገ። ይህም ህመሙ እንዲቀንስ እና መድሀኒቱ የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን የሚረዳ በመሆኑ ነው።

ከአምስት አመት በኃላም ለበሽታዬ መድሀኒቱ አልተገኘለትም።

ቀዶ ጥገናውን አደረኩኝ ነገር ግን የምወስደው መድሀኒት ለደከመው ሰውነቴ በጣም ጠንካራ ነበር። ወደ ስራ መሄድ በጣም ነበር የሚከብደኝ፤ ያቅለሸልሸኛል፣ ያዞረኛል እና የምግብ ፍላጎት የለኝም። ካልበላሁ ደግሞ አቅም ከየት ይመጣል? ከሁሉም በላይ በጣም የምወደው ፀጉሬም መርገፍ ጀመረ። የስራዬ ጫና፣ ልጄን መንከባከብ እና ያለብኝን የቤተሰብ ሀላፊነት በአንድ ጊዜ መወጣት ስለከበደኝ በጣም የምወደውን እና ላለፈው አስር አመት የሰራሁትን ስራዬን ለማቆም ተገደድኩኝ።

እኔ የጠየኩት ከክፍያ ውጪ የሚሰጥ የሁለት ወር ፍቃድ ቢሆንም አለቃዬ ግን ያለሁበትን ሁኔታ ስለሚያውቅ ክፍያ ያለው የህክምና ፍቃድ ለተወሰኑ ወራት ሰጠኝ። ይህ የተሰጠኝ ጊዜም ከህመሜ እንዳገግም እረዳኝ።

በእንደዚህ አይነት አስከፊ በሽታዎች ውስጥ እያለፋችሁ ከሆነ ለብቻችሁ እንዳልሆናችሁ እወቁ። ለምን በከባድ ነገሮች ውስጥ እንደምናልፍ ላይገባን ይችላል። በህመም እያሳላፋችሁ ወይም እየተሰቃያችሁ ከሆነ ከኛ ቡድን አንድን ሰው ስለሁኔታችሁ ለማማከር ጊዜ አትውሰዱ። ሁሉም ምክክሮቻችን ሚስጥራዊ ናቸው።


ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡


እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡

የእርስዎ ፆታ:
የዕድሜ ክልል:

ተገቢውን አማካሪ እንዲመድብዎት የእርስዎ ፆታ እና ዕድሜ እንጠይቃለን። የአገልግሎት ውሎች & የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ.

እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!