ለጎዳህ ሰው መራራት የቻልከው መቼ ነው? እስቲ እራስህን ጠይቅ “ነገሮች ጥሩ ወይስ አስቸጋሪ እንዲሆኑ ነው ምትፈልገው?” ይቅርታ በጤናችን እንዲሁም ስሜታዊ ደህንነት ላይ ትልቅ ተጽኖ አለው። ሌላውን ይቅር የማለት ተግባር ለልባችን የሚሰጠን እረፍት ይቅር ከምንለው ሰው የበለጠ ነው።
ይቅርታ በተበደልን ጊዜ ፍትህን ከመጠየቅ ይልቅ ምህረትን የመስጠት ውሳኔ ነው። ይቅርታ መሰናክሎችን በማስወገድ ቅጣትን ያነሳል። ይህ ማለት ያን በደል በሌላው ሰው ላይ ዳግመኛ ላለመያዝ መወሰን ማለት ሲሆን፤ ግንኙነቱ እንዲታደስ እና እንደገና እንዲያድግ እድል መክፈቻም ነው። ይቅርታ እጅግ ጥልቅ ሃሳብ ነው።