ባለቤቴ የተዋጣለት ይቅርታ ጠያቂ ነው። እኔ ይቅርታ አልጠይቅም ማለት አይደለም። ጥፋት ስታጠፉ ጥፋታችሁን ማመን በጣም ከባድ ነገር ነው ግን እኔ እንዳጠፋሁ ካመንኩኝ ሁሌም ይቅርታ እጠይቃለሁ። ነገር ግን የይቅርታ አጠያየቄ ከልቤ እንደሆነ እንዳይታሰብ ያደርጋል። ይቅርታ አጠያየቄን ለማስተካከል እየተማርኩኝ ነው እና እስከ አሁን የተማርኩት ይህንን ይመስላል።

በየትኛውም የይቅርታ ጥየቃ አዳማጩ አካል ይቅርታ ጠያቂው ከልቡ እየጠየቀ እንደሆነ ከተሰማው ይቅርታውን ይቀበለዋል። ችግሩ የሚፈጠረው ከልብ ይሁን አይሁን በመለየት ሂደት ውስጥ ነው። ይህ ሁሉ የሚመዘነው በተማርነው የይቅርታ አጠያየቅ ልክ ነው።

ሁለታችንም አልተደማመጥንም

እኔ ባደኩበት ቤተሰብ የሆነ ጥሩ ነገር ማድረግ ወይም መናገር ይቅርታ እንደተጠየቀ ያስቆጥራል። ምሳሌ “ይቅርታ” የሚለውን ቃል መናገር በቂ ነው። ነገር ግን ባለቤቴ ባደገበት ቤተሰብ ይቅርታ ከቃሉ የዘለቀ ነው። ይቅርታ ከመጠየቃችሁም በላይ ይቅርታ የምትጠይቁበትን ጉዳይ ጥፋታችሁን በመግለፅ ልትዘረዝሩ ይገባል። በእርሱ ቤተሰብ ይቅርታ አንዱን ጉዳይ ብቻ የሚመለከት እንጂ በጅምላ የሚደረግ አይደለም። እርሱ የለመደው “በቅድሚያ ጉዳዩ ግልፅ ሳይሆንልኝ ለመልስ በመቸኮሌ ይቅርታ” የሚለውን ነው።

የይቅርታ አጠያየቃችን መለያየት በቤታችን ውስጥ ችግር ፈጥሮ ነበር። የሆነ የማይረባ ነገር አደርጋለሁ። ባለቤቴ ይደርስበታል። በደንብ አስብበት እና በውስጤ ያደረኩት ነገር ትክክል እንዳልሆነ ተረድቼ ይቅርታ ለመጠየቅ ለምልክትነት የሆነ ጥሩ ነገር አድርጌ ላስደስተው ሞክራለሁ። ባለቤቴም ጥፋቴን ጥሩ ነገር በማድረግ ለመሸፈን በመሞከሬ በጣም ይናደዳል። በተፈጠረው ነገር ግራ እጋባለሁ። ለእኔ ላስደስተው ሞከርኩ ማለት ይቅርታ ጠየኩት ማለት ነው።

በሌላም ጊዜ በግድ የለሽነት ነገሮችን አደርጋለሁ። አሁንም ባለቤቴ ይደርስበታል። አስብበት እና “ይቅርታ” እጠይቀዋለሁ። ባለቤቴም “ይቅርታ” ስለው “በጥፋትሽ አልተፀፀትሽም በምን ምክንያት እንኳን ይቅርታ እየጠየቅሽ እንዳለሽ አታውቂም” ይለኛል። እኔም “ከአንተ ጋር ተስማምቻለሁ በጣም ይቅርታ!” እለዋለሁ። እሱም “ይቅርታሽ ከልብ ስለመሆኑ አላመንኩም” ይለኛል። አሁንም ግራ ያጋባኛል።

5 የይቅርታ አጠያየቅ መንገዶች

እኔ እና ባለቤቴ ላይ የሚታየው ይቅርታን የምንቀበልበት ልዩነት የተለመደ ነው። የምታፈቅሩት ሰው ይቅርታ ስትጠይቁት አልሰማ ካላችሁ ምን ታደርጋላችሁ? ዶ/ር ጌሪ ቻፕማን Things I Wish I’d Known Before Getting Married, በሚለው መፅሀፉ አለማቀፍ የሆኑ አምስት የይቅርታ አጠያየቅ መንገዶችን አብራርቷል።

  1. መፀፀታችሁን ግለፁ

ይህ ቋንቋ ለስሜታቸው መናገር የሚችል ነው። እንደጎዳናቸው እንዳወቅን የሚያመለክት ነው። “በሀይለ ቃል በመናገሬ ይቅርታ። ስሜትህን እንደጎዳሁ አውቃለሁ እና ይህንን በማድረጌ በጣም ይቅርታ።”

  1. ሀላፊነት መውሰድ

ይህ ቋንቋ የጠፋውን ጥፋት የሚገልጥ ነው። “በሀይለ ቃል መናገሬ ስህተት ነው። በእንደዚህ መንገድ ልመልስልህ አይገባም ነበር።”

  1. መካስ

ይህ ጥፋትን ስለማረም ነው። ይህ በእርግጥ በተበዳይ የፍቅር ቋንቋ ላይ መሰረት የሚያደርግ ነው። “በዚህ መንገድ መመለስ አልነበረብኝም። ይህን ለመካስ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ንገረኝ።”

  1. ፀባይሽን ለመቀየር ያለሽን ፍላጎት ግለጪ

ይህ እራሱ በራሱ የሚገልፅ ይመስለኛል። “ሁል ጊዜ በጣም እናደዳለሁ እና እንደዚህ ማድረግ እንደሌለብኝ አውቃለሁ። ይህንን መድገም አልፈልግም። ይህ በድጋሚ እንዳይፈጠር ሊያረጋግጥልህ የሚችል ነገር ማሰብ ትችላለህ?”

  1. ይቅርታ እንዲያደርግ መጠየቅ

ይቅርታው ከልብ ይሁን አይሁን ከመታየቱ በፊት ይቅርታ እንዲያደርግላችሁ መጠየቅ አለባችሁ። “በቁጣ በመናገሬ እና በዚያ መልኩ በመመለሴ ይቅርታ። ይህ እንደሚጎዳህ አውቃለሁ። ይቅርታ ልታደርግልኝ ትችላለህ?”

ከእነዚህ አንደኛው የይቅርታ አጠያየቅ መንገድ እናንተ ከለመዳችሁ ጋር የሚስማማ ሊሆን ይችላል። ለእኔ መፀፀቱን መግለፁ ብቻ በቂ ነው። እና በሌላ በኩል ደግሞ አንደኛው ለባለቤታችሁ የሚስማማ ይሆናል። ለእኔ ባለቤት የሚስማማው ለጠፋው ጥፋት ሀላፊነት መውሰድ ነው። አሁን በእያንዳንዳችን ቋንቋ እንዴት ይቅርታ መጠየቅ እንምደንችል እና በምንመርጠው ቋንቋ ያልተነገረን ይቅርታ እንዴት መቀበል እንደምንችል እየተማርን ነው።

አንድ ነገር የተማርኩት በሌላኛው ወገን ጥፋት ቢኖር እንኳን “ይቅርታ ግን…” መቼም ማለት እንደሌለብኝ ነው። “ግን” የምትለው ቃል መላው የይቅርታን መንፈስ ታደፈርሰዋለች። ይህ የእናንተን መጥፎ ባህሪ በእነርሱ መጥፎ ባህሪ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ለማሳየት የሚደረግ ጥረት ነው። ይህ ትልቅ ጥንካሬን እና ትህትናን የሚጠይቅ ሲሆን ሁልጊዜም ድርጊትዎ የምርጫ ጉዳይ ነው። የእርሶን ድርሻ በመወጣት ሀላፊነት ይውሰዱ።

በህይወትዎ የተበላሽ ግንኙነትን ለመጠገን እየሞከሩ የመሸነፍ ስሜት እየተሰማዎት ነው? ከሰው ጋር ይህንን ማውራት መፍትሄ ሊያመጣ ይችላል። እናንተን ለመርዳት እና ለማበርታት የሚችሉ አማካሪዎችን በእኛ በኩል ማግኘት ይችላሉ። ከክፍያ ነፃ የሆነ እና ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ አገልግሎት ነው። መረጃዎቹን ከታች ከሞሉ ከአንድ አማካሪያችን ጋር መገናኘት ይችላሉ።




ፎቶ በ:: keira-burton