ይቅርታ ስሜት አይደለም
ጤናማ ትዳር ለመመሥረት፤ ይቅር ማለትን መማር ወሳኝ ነው። በትዳራችን የመጀመርያ አመት "ትንንሽ" ሊባሉ በሚችሉ የጥፋት ደረጃዎች ሁሉ ነበር እርስ በርሳችን ይቅር የምንባባለው። ነገር ግን "ትንሽ" የሚባሉት ጥፋቶቸ ትዳራችንን ምን ያህል ይጎዱ እንደነበር የማልክደው ሀቅ ነው። ቢሆንም፣ በዚህ የመጀመሪያ አመት ይቅርታን ለመለማመድ ብዙ እድሎችን አግኝቻለሁ (ባለቤቴም እንዲሁ)። ይቅርታ ስሜት ብቻ ነው ብሎ ማሰብ ቀላል ነው። ግን አይደለም።
ታዲያ ይቅርታ ምንድን ነው?
እንደ ጋሪ ቻፕማን ገለጻ፣ ይቅርታ በተበደልን ጊዜ ፍትህን ከመጠየቅ ይልቅ ምህረትን የመስጠት ውሳኔ ነው።
ይቅርታ መሰናክሎችን በማስወገድ ቅጣትን ያነሳል። ይህ ማለት ያን በደል በሌላው ሰው ላይ ዳግመኛ ላለመያዝ መወሰን ማለት ሲሆን፤ ግንኙነቱ እንዲታደስ እና እንደገና እንዲያድግ እድል መክፈቻም ነው። ይቅርታ እጅግ ጥልቅ ሃሳብ ነው።
እንዲሁም ስለይቅርታ ያለንን መረዳት ማጥራት በጣም አስፈላጊ ነው
- ይቅርታ ትውስታን አያጠፋም
በተለይ ከስሜታዊ ጉዳት ጋር በተያያዘ አንዳንድ ሁኔታዎች ከጉዳቱ ጋር የተያያዙ ብዙ ትውስታዎችን ያመጣሉ። ነገር ግን ቁስሉን ማስታወስ ማለት የጎዳችሁን ሰው ይቅር አላላችሁም ማለት አይደለም። ይህ ማለት እርስዎ ሰው ነዎትና ስሜት አለዎት ማለት ነው። ሆኖም ያለፈው በደል ትዝታ ይቅር ላላችሁት ሰው ዛሬ በምትሰጡት ምላሽ ላይ ተጽዕኖ እንዳያደርግ መጠንቀቅ ያስፈላጋል።
- ይቅርታ የበደል ውጤትን ሁሉ አያስወግድም
ይቅርታ ጉዳቱ ከመከሰቱ በፊት ግንኙነታችሁ ወደነበረበት ቦታ ወዲያውኑ አይመልስም። በአንጻሩ ይቅር ማለት ግንኙነቱን ወደነበረበት ለመመለስ ፈቃደኛ መሆን ማለት ነው።
- ይቅርታ ዳግም መተማመንን ወዲያውኑ አይገነባም
እምነት ማጣት ከስህተት የሚመነጭ ተፈጥሯዊ ውጤት ነው። ከእውነተኛ ይቅርታ በመነሳት እና ቀጣይነት ያለው የባህሪ ለውጥ በማሳየት መተማመን እንደገና መገንባት አለበት። ግልጽነት ባለው አመለካከት እና ወጥነት ባለው ታማኝነት፣ መተማመንን እንደገና መገንባት ይቻላል።
- ይቅርታ ሁልጊዜ እርቅን አያመጣም
እርቅ በመፍጠር ሂደት ውስጥ፤ ሁለቱም ወገኖች ለይቅርታ ፈቃደኛ ከሆኑ እርቅ ሊፈጠር ይችላል። ነገር ግን ግንኙነቱን ወደነበረበት ለመመለስ ፈልጋችሁ ሌላው ሰው ተመሳሳይ ልብ ከሌለው፤ ለእግዚአብሔር ተውት። ቁጣችሁንና ሀዘናችሁንም ከእርሱ ላይ አንሱ። ለእርቅ ፍቃደኛ አለመሆናቸው ህይወቶን እንዲረብሽ ከቶ አትፍቀዱለት። ይልቁንስ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች የራሳቸውን ችግሮች እስኪለዩና እስኪያስተካክሉ ድርስ እርቅ አለመፍጠር አስፈላጊ ስለሚሆን በቂ ጊዜን ስጧቸው።
እውነተኛ ይቅርታ ትዳራችሁን ከመራራነትና አሰልቺነት መጠበቂያ ብቸኛው መንገድ ነው። ሰዎችን ለመነጣጠል በመካከላቸው የሚገነባን የጥል ግድግዳን ማፍረሻ ወሳኙ መሳሪያም እርሱ ነው። በእርቅ ውስጥ ትልቁ ጉዳዩ ሌላው ሰው ይቅርታ መጠየቁ ወይም አለመጠየቁ ሳይሆን ይቅርታውን መቀበላችን ላይ ነው። ይቅርታን አለመቀበል የራስን ልበ ደንዳናነት፣ ግብዝነት እና ራስን ፍጹም አርጎ ማሰብን ማሳያ ነው። ሌላው ሰው ይቅርታ ሊደረግለት የማይገባው ነው ብዬ ካሰብኩ፣ በኢ-ሚዛናዊ የዳኝነት አመለካከቴ የተነሳ ራሴ ይቅርታ ማግኘት በሚያስፈልገኝ ደረጃ ላይ ነኝ ማለት ነው። ሂደቱ እጅግ ትኩረት የሚስብ ነው።
ጉዳቶቻችሁን መተው ብዙ ጊዜ በአንድ ጀንበር የሚደረግ ልምድ አይደለም። ጊዜ ይወስዳል። ነገር እሱን ለመተው ስትጥሩ፣ ውሳኔያችሁ በርግጥም ትክክል እንደሆነ ትረዳላቹ። ይቅር ለማለት የምትቸገሩ ከሆነ፤ ብቻችሁን እንዳልሆናችሁ እወቁ። እና ስለምታልፉበት ነገር የምታወሩት ሰው ቢኖር በእውነት ይረዳል። ሚስጥርዎ የተጠበቀ እና ሁልጊዜም በነፃ የሚሰጥ አገልግሎት ነው። የግል አማካሪ ከፍለጉ ከታችኛው ባለው form ያገኙናል።
ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡
እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡
እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!