ይቅር ማለት ለምን በጣም ከባድ ሆነ?
ሰዎች በባህሪያቸው በሌሎች ሰዎች ሲጎዱ ለመቀበል እጅግ ይከብዳቸዋል፡፡ ኩራታችን ወይም ለራሳችን ያለን ግምት ተጎድቷል። ጉጉታችን ወይንም ህልማችን ከስሟል፡፡ ለደረሰብን ከባድ ጉዳትና ላጣነው ጠቃሚ ነገር ማካካሻ እንፈልጋለን፡፡ ነገር ግን ይቅር ለማለት ያለንን መነሳሳት የሚገቱ ተቃራኒ ሃሳቦች አሉ፡፡ ቅጽበታዊ ሃሳቦች ወይም እምነቶች ሌሎችን ይቅር እንዳንል እንቅፋት ይሆናሉ። “ይቅር አልልም ምክንያቱም እሱ/እሷ ላደረገው ነገር ሀላፊነቱን አይወስድም” ወይም “ይቅር ለማለት ስላልፈለኩ ይቅር ብባል ግብዝ እሆናለሁ” ወይም ደግሞ “ይቅር ማለት የደካማ ሰዎች መገለጫ ነው” እንላለን፡፡
ሌላው እንቅፋት ሊሆን ሚችለው ባህሪን በጥልቀት ማብራራት ነው፡፡ አንድ ሰው ሲጎዳን ወይም ሲያሳዝነን ለፈጸመው በደል ባህሪ ውስጣዊ ምክንያቶችን እናስቀምጣለን ድርጊቱ ባህሪውን ወይም ስብዕናውን መሰረት ያደረገ ነው ብለን እንከራከራለን። ለራሳችን፣ “እሱ በጣም የሚረሳ ወይም ግድ የለሽ ነው” ወይም “አታደንቀኝም” ወይም ደግሞ “ይህን ሆን ብላ ነው ያደረገችው” እንላለን። አጥብቀን እንፈርድባቸዋለን።
ይቅርታ በጤናችን እንዲሁም ስሜታዊ ደህንነት ላይ ትልቅ ተጽኖ አለው
በአንጻሩ እኛ የተሳሳተ ወይም የሚጎዳ/አሳዛኝ ነገር ስናደርግ የተለያዩ ምክንያቶችን በማንሳት ለራሳችን ባህሪ ማስተባበያ እንሰጣለን። በህይወት ውስጥ ለሚከሰቱት መልካም አጋጣሚዎች ብቻ ሃላፊነት እየወሰድን ስህተቶቻችንን ወደሌሎች እንገፋለን፡፡ በትምህረት መመዘኛዎች ላይ የምናገኛቸው ጥሩ ውጤቶች በሙሉ የኛ የልፋት ውጤቶች እንደሆኑ እንናገራለን፡፡ በውድቀታችን ግን ጣታችንን ወደሌሎች እንቀስራለን፡፡ ‘’A’’ አገኘው እንልና ‘’F’’ ሰጠኝ እንላለን፡፡ እራሳችንን ከተጠያቂነት ለማዳን ለውድቀታችን ፍቃድ እንሰጣለን.
የሥነ ልቦና ባለሙያዎች “መሰረታዊ የአመለካከት ስህተት” ብለው የሚጠሩት ይህንን ነው። የራሳችንን አሉታዊ ድርጊቶች ከሁኔታዎች አንፃር እያስረዳን ሌሎችን ግን ለባህሪያቸው ሙሉ ሀላፊነት እየሰጠን እንነቅፋለን ። በሌላ አነጋገር፣ ለድርጊታችን ሰበብ በመደርደር ጥፋተኞች እንዳልሆንን እናስባለን። ይሁን እንጂ በስነምግባር ላይ ያለውን ስህተት መረዳት እና መቀበል ጥፋተኛውን ከሥነ ምግባራዊ ሃላፊነት እንደማያስቀረው ልብ ሊባል የሚገባው ጉዳይ ነው። አንድን ሰው ይቅር ማለት ድርጊቱ የሚያስከትለውን መዘዝ አያስቀርም፡፡
በስነልቦናው ረገድ የይቅርታ ዋናው መንገድ ርኅራኄ ሲሆን ይህን ማጣት ይቅር የማለት አቅማችንን ሊፈትን ይችላል። በመሆኑም አስተሳሰባችንን በመቀየር ለሌሎች ርኅራኄን ማዳበር እንችላለን። አንድ ሰው ያዘንበትን ድርጊት ለምን እንደፈጸመ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ልንሆን አንችልም፡፡ በመሆኑም ግቡ ርህራሄን እና ይቅርታን በማሳደግ ጎጂ የሆኑትን ክስተቶች ከነሱ እይታ አንጻር መመልከት ነው። ይህ ሰዎችን ስለ ባህሪያቸው ወይም አላማቸው ከባድ መደምደሚያ ላይ ከመድረስ ይልቅ ያላቸውን ጥሩ ነገር ማሰብን ይጨምራል። ይቅርታ የፈለክበትን ጊዜ አስብ።
ሕይወትህ በቂም እንዲታሰር አትፍቀድ፤ አንተን እና ሌሎች ግንኙነቶችህን ያጠፋል
ለጎዳህ ሰው መራራት የቻልከው መቼ ነው? እስቲ እራስህን ጠይቅ “ነገሮች ጥሩ ወይስ አስቸጋሪ እንዲሆኑ ነው ምትፈልገው?” ይቅርታ በጤናችን እንዲሁም ስሜታዊ ደህንነት ላይ ትልቅ ተጽኖ አለው። ሌላውን ይቅር የማለት ተግባር ለልባችን የሚሰጠን ረፍት ይቅር ከምንለው ሰው የበለጠ ነው። ይቅርታ ለኛ ጥቅም ቢሆንም፣ነገር ግን ብዙ ጊዜ፣ ሁኔታዎች እንቅፋት ይሆናሉ።
ሕይወትህ በቂም እንዲታሰር አትፍቀድ፤ አንተን እና ሌሎች ግንኙነቶችህን ያጠፋል፡፡ ሉዊስ ስሜድስ “ይቅር ማለት እስረኛውን ነፃ መውጣት ነው ፤ እናም እስረኛው እርስዎ መሆንዎን ማወቅ ነው” ሲል ጽፏል።
ጉዳቶቻችሁን መተው ብዙ ጊዜ በአንድ ጀንበር የሚደረግ ልምድ አይደለም። ጊዜ ይወስዳል፡፡ ነገር እሱን ለመተው ስትጥሩ፣ ውሳኔያችሁ በርግጥም ትክክል እንደሆነ ትረዳላቹ፡፡
ይቅር የማለት ችሎታ ራሳችንን ይቅር የማለት አቅማችን ላይ የተመሰረተ ነው፡፡አማካሪዎች የተጎዱ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ሌሎችን እንደሚጎዱ ይጠቁማሉ። ማናችንም ብንሆን እንከን የለሽ አይደለንም። ሰዎች እንደመሆናችን መጠን እርስ በርስ የመበዳደል ዝንባሌ አለን። ማናችንም ብንሆን ፍጹም የሆነ ሕይወት የለንም ወይም ለተናገርነው ወይም ላደረግነው ነገር ይቅርታ ሳንሻ አልቀረንም። ሁላችንም ስህተት እንሰራለን።
በመጽሃፍ ቅዱስ ውስጥ እግዚአብሔር አለምን በጣም ከመውደዱ የተነሳ ይቅር እንድንባል አንድያ ልጁን እንደላከ ይናገራል (ዮሐ. 3፡16)። ኢየሱስ በዚህ ምድር ላይ በነበረበት ወቅት ከፍተኛ ሥቃይ፣ ውድመትና ውርደት ተሰምቶት ነበር፤ ነገር ግን ከመሞቱ በፊት በተናገረለት የመጨረሻ ቃል እሱን የሚገድሉትን ሰዎች ይቅር እንዲላቸው አምላክን ጠየቀ። ከዚያ በኋላ የኖረ ብቸኛው ኃጢአት የሌለበት ኢየሱስ የሰው ልጆችን ኃጢአት በሙሉ ለመክፈል በመስቀል ላይ ሞተ። ይህም ማንም ሰው በእግዚአብሔር ይቅር እንዲለው እና ከፈጣሪው ጋር እንዲታረቅ አስችሏል.
ለፈጸሟቸው በደል ሁሉ በእግዚአብሔር ይቅር መባል የሚያስገኘውን ደስታ ከተለማመዱ ሌሎችን ይቅር ማለት በጣም ቀላል ይሆናል። በእሱ እርዳታ, ጠባሳዎቹ በጣም ጥልቅ ቢሆኑም እንኳ ሌሎችን ይቅር ማለት ይችላሉ. ጊዜ እና ጥረት ሊወስድ ይችላል, ግን ዋጋ ያለው ይሆናል.
የእግዚአብሔርን ይቅርታ አጋጥሞህ የማታውቅ ከሆነ ዛሬ እንዴት እንደምትችል እነሆ።
ይቅር ለማለት የምትቸገሩ ከሆነ፤ ብቻችሁን እንዳልሆናችሁ እወቁ። እና ስለምታልፉበት ነገር የምታወሩት ሰው ቢኖር በእውነት ይረዳል። ሚስጥርዎ የተጠበቀ እና ሁልጊዜም በነፃ የሚሰጥ አገልግሎት ነው። የግል አማካሪ ከፍለጉ ከታችኛው በለው form ያገኙናል።
ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡
እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡
እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!