አባቴ ከአሁን በኋላ አብሮኝ አለመኖሩን ሳስብ እጅግ ደነገጥኩ። አባቴ ለእኔ ፤ የቅርብ ጓደኛዬ፣ መተማመኛዬ ፣ ጠበቃዬ ፣ ጀግናዬ እና የመጀመሪያ ፍቅሬ ሲሆን ለብዙ ትናንሽ ልጆች ደግሞ እንደ አባት ነበር።
አንገቱን ወደ እኔ አዞረ እና በትጋት ለመጨረሻ ጊዜ “እወድሻለሁ” አለኝ። ለመጨረሻ ጊዜ እየተሰናበተኝ እንደሆነ ገባኝ። በእጆቼ እንዳቀፍኩት የመጨረሻውን ትንፋሽ ተነፈሰ። በዚያች ቀን አርሱን በማጣት ያየሁት መከራ አንድ ብሎ ተጀመረ።