ያለ አባቴ እንዴት እኖራለሁ?

አባቴ ለእኔ፤ የቅርብ ጓደኛዬ፣ መተማመኛዬ፣ ጠበቃዬ፣ ጀግናዬ እና የመጀመሪያ ፍቅሬ ሲሆን ለብዙ ትናንሽ ልጆች ደግሞ እንደ አባት ነበር።

ገና የ8 ዓመት ልጅ ሳለሁ በ1996 ዓ/ም ህዳር ወር ላይ አባቴ የኩላሊት እና የሳንባ ችግር እንዳለበት ታወቀ፤ ይህም የአልጋ ቁራኛ አደረገው። ብዙ ጊዜ እኩለ ሌሊት ላይ በጣም ያመውና ወደ ሆስፒታል እንወስደዋለን። ሁሌም ሆስፒታል ውስጥ አልጋው አጠገብ አንደነበርን አይነት ስሜት ነበር ሚሰማኝ። በየቀኑ፤ ቀስ በቀስ ሲሞት ማየት ለእኛ ቀላል አልነበረም። በወቅቱ ተአምር እንዲፈጠር ከልቤ ተስፋ አደረኩና ጸለይኩ። ለማንም ባይሆን እንኳን ለእኔ ሲል በህይወት እንዲቆይ ተመኘው! ይሁን እንጂ፤ በሽታው ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ ሄደ።

የክረምት እረፍት በተጀመረበት የመጀመሪያው ቀን፤ ከዚ በኋላ እሱን ትቼ ትምህርት ቤት ስለማልሆን ሙሉ ጊዜዬን አብሬው ማሳለፍ በመቻሌ ደስተኛ ሆኜ ወደ ቤት ሄድኩኝ። እንደ አለመታደል ሆኖ ያን ቀን አባቴ አረፈ።

ከምሽቱ ሁለት ሰአት ላይ፤ የቤታችን መግቢያ በር ተከፍቶ ብዙ ሰዎች ወደ ቤት ገቡ። ድባቡ እጅግ አሳዛኝ እና የሃዘን መግለጫዎቹ ከከፍተኛ ጩኸት ራስን እስከመሳት ይደርሱ ነበር። አባቴ ታላላቅ ወንድምና እህቶቹን እንዲሁም ወላጆቹን ጨምሮ መላው ቤተሰቡን ደጋፊ ነበር። አሁን ግን ሁላችንም ራሳችንን እንድንጠብቅ ቀርተናል። በሚቀጥለው ቀን የቀብር ስነስርአቱ ተፈጸመ።

አባቴ ከአሁን በኋላ አብሮኝ አለመኖሩን ሳስብ እጅግ ደነገጥኩ

አባቴ ከአሁን በኋላ አብሮኝ አለመኖሩን ሳስብ እጅግ ደነገጥኩ ሁሉም ነገር የሆነው በፍጥነት ስለነበር፤ ምን ማሰብና ማድረግ እንዳለብኝ እንኳን በቅጡ አላውቅም ነበር፡፡ በወቅቱ ትንሽ ልጅ በመሆኔ፣ በቅርቡ ተመልሶ ይመጣልኛል የሚል የልጅነት እምነት ነበረኝ። ያን ቀን ባይሆን እንኳን፤ ምናልባት ከ10 ዓመታት በኋላ። እናቴ ስለ ሞት ጽንሰ-ሀሳብ ለወንድሞቼ ለማብራራት ትሞክራለች፤ እኔ ግን የእኔን ውድ ሰው ስላጣው መስማት አልፈልግም ነበር።

ከሞቱ በኋላ ያለው የሕይወት ቅኝት አስቸጋሪ ሆን። ኑሯችን በጭራሽ እንደበፊቱ ሊሆን አልቻለም። ሙሉ የቤተሰቡ ሃላፊነት እናታችን ላይ በመውደቁ፤ እኛን ለማስተማር፣ ለመመገብና የሚያስፈልገንን ነገረ ለማቅረብ ተጨማሪ ስራዎችን መስራት ነበረባት፡፡ ሆኖም ገቢና ወጪያችን ሊመጣጠን ባለመቻሉ ጭንቀት ውስጥ ገባን። ብዙም ሳይቆይ ተስፋ እየቆረጥን መጣን። ደስታ ብርቅዬ ስሜት ሆነ። ከዚህ አሳዛኝ ሁኔታ እንዴት እንደምንወጣና ከፊታችን ያለውን ህይወት እንዴት እንደምንጋፈጥ አናውቅም ነበር። ቅዳሜና እሁድ እንደ ልማዳችን የልጆች ጊዜ ለማየት እሱ የተኛበት ክፍል የሄድኩባቸውን ጊዜያት አስታውሳለሁ። ብዙ መቆየት ግን አልችልም፤ አባቴ ከአሁን በኋላ አለመኖሩ በድንገት ወደ ውስጤ እየመጣ ይረብሸኝና ክፍሌ ተመልሼ ለጥቂት ሰአታት አለቅሳለሁ፣ ከዛም ከአልጋዬ ላይ ተነስቼ በዝግታ ቀኔን እቀጥላለሁ። ሕይወት፤ በድንገት ቀለሟን አጣች። ትዝታዎቹ ብቻ ቀሩ።

በእያንዳንዱ የሕይወቴ እርከኖች ውስጥ፣ ሊገለጹ የማይችሉ ስሜቶች ተሰምተውኛል፤ አብዛኛው ህመም ነው። በማደግ ላይ ያለች ሴት እንደመሆኔ፣ ስለ ህይወት መንገዴ እና ግንኙነቴ የአባቴ ምክር እና ሃሳብ ያስፈልገኝ ነበር። ለኔ ከወርቅ የጠራ ፍቅር ካለው ሰው ጋር ቀለል ብሎ ማውራትንና መነጋገርን በጣም ፈለግሁ። እያንዳንዱ የእሱ ትዝታዎች ቁስሌ እንዲያገረሽ ስለሚያደርጉኝ፤ አብዛኛውን ምሽት የማሳልፈው በእንባ ታጥቤ ነው። ብዙ ጊዜያት አለፉ። ለሕይወት ግድየለሽ እየሆንኩ፤ ሰዎችን ማመን እየተቸገርኩና ለራሴ ያለኝ ግምት እየወረደ መጣ። ሕይወቴን እንዴት መምራት እንዳለብኝና ወደ ተሻለ መንገድ ማምጣት እንደምችል አላውቅም። እሱ በሚያስፈልገኝ ሁኔታ ላይ እንዳለሁ በተሰማኝ ቁጥር አለቅሳለው። ወደ ሀያ ለሚጠጉ ዓመታት ከእዚህ ስሜት ለመውጣት አንድም ጊዜ አቅጄ አላውቅም። ህይወቴ አንድ ቦታ ላይ ቆሞ ነበር። ነገር ግን ከህመም በቀር ሌላ ነገር ያመጣልኛል ብዬ አስቤ አላውቅም።

ከዚያም አንድ ወዳጄ ከጥፋት መዳንን በተመለከተ ጥልቅ የሆነ ሃሳብ ነገረኝ። ፈውስ ማለት ስላጣነው ሰው ያለን ትዝታ ወይም ፍቅር ይሞታል ማለት ሳይሆን፤ ህይወታችንን እነሱ ደስ በሚያሰኛቸው መንገድ መምራት ማለት ነው። የምንወደውን ሰው በማጣታችን መኖራችንን አናቆምም። ይልቁንም ትዝታቸውን በሚያስከብር እና እሴታቸውን በሚያስቀጥል መንገድ እንኖራለን። እናም አሁን በዚህ የፈውስ ጉዞዬ፤ ይህን ያህል ርቀት በመጓዜ ደስተኛ ነኝ።

የምትወደውን ሰው በሞት ካጣህና ሃዘንህ ወደፊት እንዳትሄድ መንገድ ከዘጋብህ ብቻህን አይደለህም። ፈውስን ማግኘት ይቻላል። ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ፈውስን ለማግኘት ሆን ብለው ማሰብና መስራት አለብዎት። ነገሮችን በግልጽ መነጋገር ሊረዳ ይችላል። በዚህ ድረ-ገጽ በኩል፣ ታሪክዎን ለማዳመጥ እና በፈውስ ሂደት ውስጥ እርስዎን ለማበረታታት ዝግጁ የሆኑ ነጻ እና ሚስጥራዊ አማካሪዎች አሉ። ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ብቻ ይሙሉ እና አንድ ሰው በቅርቡ ያነጋግርዎታል።


ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡


እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡

የእርስዎ ፆታ:
የዕድሜ ክልል:

ተገቢውን አማካሪ እንዲመድብዎት የእርስዎ ፆታ እና ዕድሜ እንጠይቃለን። የአገልግሎት ውሎች & የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ.

እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!