እውነተኛ ማንነታችንን መግለፅ

ማርታ አየር በደንብ ከሳበች በኋላ ፊቷ ላይ ትልቅ ፈገግታ አድርጋ የጓደኛዋን ቤት አንኳኳች። ሁሌም በዙርያዋ የሚሆን ነገር አለ ግን የትኛውም የመጀመሪያ ምርጫዋ አይደለም። ማርታ በራስ መተማመኗ እና በዙርያዋ ሰፊ ማህበራዊ ህይወት በመኖሩ ትታወቃለች ግን በድንገት ምን ያህል በራስ መተማመን እንደሌላት እና የብቸኝነት ስሜት ተሰማት።በህይወቷ እየሆነ ያለውን ነገር ሁሉ ሌላ ሰው የመረጠላት ነበር የሚመስለው። ቀኖቿ እና እንቅስቃሴዎቿ ሌሎች ሰዎች በሚፈልጓቸው ላይ የተመሰረቱ ናቸው። ሌሎች የሚጠብቋትን በመሆን ውስጥ ተስፋዋ እና እሷነቷ ተሸፈነ። ማርታ በር ላይ ቆማ ስትጠብቅ ይሰማት የነበረው ጓደኞቿ መሀል ምን ያህል ብቸኝነት እንደሚሰማት ነበር።

ራሳችሁን እንደ ማርታ ሲሰማችሁ አግኝታችሁት ታውቃላችሁ? እውነተኛ ማንነታችሁን ብታወጡ ሰዎች ምን እንደሚሏችሁ ስታስቡ ራሳችሁን አግኝታችሁ ታውቃላችሁ? ለብዙ ሰዎች በውጫዊ ማንነታቸው እና በእውነተኛ እነሱነታቸው መካከል በጣም ትልቅ ክፍተት አለ። ሰዎች ራሳቸውን የመሆን ፍላጎት አላቸው ግን በዛው ልክ ተቀባይነት ያለማግኘት ወይም ተቃውሞ ይደርስብናል የሚል ፍራቻ እነሱነታቸውን እንዲደብቁ ያደርጋቸዋል። እውነተኛ ማንነታችሁን ሰዎች ያውቃሉ?
ብዙዎቻችን ህይወታችንን የምናሳልፈው የተለያዩ ጭምብሎችን አድርገን ነው። አንዳንድ ጭምብሎችን የምናደርጋቸው የማንወዳቸውን ማንነታችንን ለመሸፈን እና ሌሎቹን ደግሞ የምናቆያቸው ሰዎች እኛን የሚያዩበትን እይታ ለመቀየር ነው። ብዙ ጭምብሎችን ባደረግን ቁጥር ይበልጥ እኛነታችን እንቀብረዋለን።

እነዚህን ጭምብሎች ሁሌ ማድረጋችን ብቸኝነት እንዲሰማን ያደርገናል።

እነዚህን ጭምብሎች ሁሌ ማድረጋችን ብቸኝነት እንዲሰማን ያደርገናል።አንድ ታዋቂ አባባል እንዲህ ይላል “የምትታወቁበት ደረጃ ድረስ ነው የምትወደዱት።” እኛ በእኛነታችን የማንታወቅ ከሆነ በእኛነታችን እንደተወደድን አይሰማንም። በዛውም ጊዜ እውነተኛ ማንነታችንን ከገለፅን የምንገፋ ይመስለናል። ይሄ አስጨናቂ ኡደት እውነተኛ ማንነታችን ጭምብል እንዲለብስ እና ከሰዎች ጋር ያሉን ግንኙነቶች ባዶ እና የማያሳደስቱ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። በዛሬው ባህላችን ውስጥ ለመመሳሰል መሞከር አዲስ ነገር አይደለም፤ ብዙዎቻችን በማያልቅ የአይጦች ውድድር ውስጥ ገብተን ሌሎች ሰዎች እኛን ይጠብቃሉ በምንለው ነገር ውስጥ ለመኖር ስንሞክር ራሳችንን እናገኘዋለን። ሆኖም እውነተኛ ማንነታችን አብሯ ውስጥ ገብቶ ከኋላችን ወድቆ ይቀራል። በተጨማሪም እንደ ሰው የመቀየር እና የመለወጥ ተፈጥሯዊ ፍላጎት አለን ግን ሌሎችን ማስደሰት መፈለግ ውስጥ ብዙ ጊዜ የመለወጥ ፍላጎታችን ከውስጣዊ ጠቀሜታ ይልቅ ውጫዊ ለውጥ ላይ ያተኩራል። የዚህ አይነት ለውጥ ብዙም አይቆይም እና ተመልሰን የጀመርንበት ቦታ ላይ ዞረን እንቆማለን፤ የማንታወቅ እና የማንዋደድ በማይጠቀስ ሁኔታ ደግሞ የማንቀየር ስሜት ይሰማናል። ሰው ለማድረግ የሚመርጣቸው ብዙ ጭምብሎች ቢኖሩም በጣም የተለመዱ ሁለት አሉ።

1· ህመምን መሸፈኛ ጭምብል።

በህይወታችን ዙርያ ያለው ነገር ሁሉ መበላሸት ሲጀምር የምናደርገው የፈገግታ ጭምብል ነው። ይሄን ጭምብል ማውለቅ ማለት ደህና እንዳልሆንን አምነን መቀበል ማለት ነው። ምናልባትም የሚረዳም ማንም ሰው እንደማይኖር ማሰብም ማለት ነው። እንደዚህ አይነቱ ራስን ማወቅ ጥልቅ የሆነ ለውጥ ይፈልጋል። ምክንያቱም የመውደቅን (ያለመሳካትን) ፍርሃት ብዙ ሰዎች መጋፈጥ የማይፈልጉት ፈተና ነው። ይሄን ጭምብል ለማውለቅ ጥልቅ የሆነ ጥንካሬ ይጠይቃል ግን መሆን ይችላል።

2· ውርደትን መሸፈኛ ጭምብል።

እነዚህ ጭምብሎች በንብረት ብዛት በራስ መተማመናቸውን ወይም ኩራታቸውን የሚያሳዩባቸው ናቸው፤ ያደረጋቸው ያ ባይሰማውም። እነዚህን ጭምብሎች የምንጠቀመው ሌሎች የምንወደውን ነገር እንዲያዩልን ለማድረግ ወይም ያስከብሩናል ብለን የምናስባቸውን ነገሮች ለማየት እንዲረዳቸው ነው። እነዚህ ጭምብሎች የውጭ ሰዎች ድክመታችንን እና የሚያዋርደን ነገር የቱ ጋር እንዳለ ከማየት እንዲገደቡ ነው። ከእውነተኛ ማንነታችን፣ ከሰውነታችን የሰዎች ትኩረት ይነሳል።

የተወሰኑ እውነታዎች

እነዚህን ጭምብሎች የምናደርገው ለመልካም ምክንያቶች ነው። ሁላችንም የግል ህመም እና መገፋት ደርሶብናል። ሆኖም በእውነተኛ ማንነታችን መታወቅ እንፈልጋለን። ይሄን በሁለት የተከፈለ ነገር እንዴት እንፈታዋለን? የሚደርሱብንን አስጊ ነገሮች እያወቅን ጭምብሎቻችንን ማውለቅ እንችላለን? ከዛ ህመም በደንብ የተጠበቅን መሆናችንን ካላወቅን በስተቀር ራሳችንን የመሆን ነፃነታችን በመገፋት ስሜት ሁሌ እየተሸፈነ ይሄዳል። ሆኖም ሌሎች ሰዎች ለዚህ ዋስትና ሊሆኑን አይችሉም። ልክ እንደ እኛ ሰዎች ናቸው እና ስህተት ይሰራሉ። ስንፈልጋቸው ላናገኛቸው እንችላለን እና የቻሉትን ያህል ቢሞክሩ እንኳን ሊያሳዝኑን ይችላሉ። እውነተኛ ማንነታችሁ የጠፋባችሁ መስሎ ከተሰማችሁ ልንረዳችሁ እንወዳለን። እዚህ ድህረ ገፅ ላይ ላካሉ ነፃ እና ሚስጥር ጠባቂ አማካሪዎቻችን ጋር ይገናኙ።


ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡


እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡

የእርስዎ ፆታ:
የዕድሜ ክልል:

ተገቢውን አማካሪ እንዲመድብዎት የእርስዎ ፆታ እና ዕድሜ እንጠይቃለን። የአገልግሎት ውሎች & የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ.

እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!