የተገፋው ልቤ

ባለቤቴን ባገኘሁት ጊዜ እኔ ገና የ15 ዓመት ልጃገረድ እርሱ ደግሞ የ16 ዓመት ጎረምሳ ነበር፡፡ በዛ እድሜዬ እንኳን በራሴ የምተማመን ጠንካራ ሴት ነበርኩኝ፡፡ በህይወቴ ምን እንደምፈልግ የማውቅ እና ለማግኘት ደግሞ ማድረግ ያለብኝን ሁሉ የማደርግ ሰው ነበርኩ፡፡ ከምፈልጋቸው ነገሮች አንዱ ባለቤቴን ነበር፤ እርሱን ማግባት፡፡ አገባሁት፡፡ የሚጠብቀኝን ህመም እና ሰቆቃ ገና አላወኩም ነበር፡፡

ከተጋባን ከጥቂት አመታት በኃላ ባለቤቴ በኢንተርኔት ከሚያውቃት ሴት ጋር ወሲባዊ መልዕክቶችን እንደሚላላክ ደረስኩበት፡፡ በጣም ተናድጄ ቁጭ አድርጌ ጠየኩት፤ አመነልኝ፡፡ ነገር ግን ይቅርታ ስለጠየቀኝ እና በድጋሚ እንደማያደርገው ቃል ሰለገባኝ በዛው ታረቅን፡፡ ይህ ከሆነ ከአንድ አመት ተኩል በኃላ እዛው እኔ በምኖርበት አከባቢ ከሌላ ሴት ጋር ፆታዊ ግኑኝነት እንዳለው ደረስኩበት፡፡ የሚገርመው ከሌላ ሀገር አንዲት ሴት አስመጥቶ ሆቴል ይዞላት ከስራ ቀን ውጪ ሁልጊዜ አብረው ወሲብ ይፈፅማሉ፡፡

በዚህ ጊዜ ከመናደድም አልፌ ነበረ እና ከቤት አስወጣሁት፡፡ ከአንድ ሳምንት በኃላ ግን በጣም ልቡ ተሰብሮ እና እያለቀሰ ደውለልኝ፡፡ መነጋገር እንደምንችል ነግሬው ተገናኝተን በጋብቻችን ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድነት ተንበርክከን ፀሎት አደርግን፡፡ የጋብቻ አማካሪም እና አስተማሪዎችን እያመከርን በአንድ ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ሁሉም ነገር ተስተካክሎ ወደ ነበረበት መልካም ነገር ተመለሰ፡፡

ነገር ግን እርቅ ሰላሙ ከወረደ በኃላ ሁሉ ነገር የሚያደርገው በሚስጥር መሆን ጀመረ፡፡ ከሴተኛ አዳሪዎች ጋር እራሱ ገንዘብ እየከፈለ ወሲብ ይፈፅም እንደነበረ ያወኩት ነገሮች ከተበለሻሹ በኃላ ነበረ፡፡ ይህም አንድ ውሽማ ካስቀመጠ በጊዜ ሂደት ፍቅር ይዞት ወሬው እኔ ጋር እንዳይደርስ ሰለፈራ ነበር ሴተኛ አዳሪዎችን መቀያየር የመረጠው፡፡ ይህ የወሲብ ሱስ በዘጠኝ አመቱ ማየት ከጀመረው የፖርኖግራፊ ፊልም የመነጨ ነበረ፡፡

በጣም ነበር የተሰበርኩት፡፡ ለሶስት ተከታታይ ቀናት እንቀጠቀጥ ነበር፡፡

ሁሉንም ነገር ባወኩኝ ሰዓት ደደብ እንደሆንኩኝ ብቻ ሳይሆን የተሰማኝ ጋብቻውንም ለማፍረስ እራሴን አሳመንኩ፡፡ የጋብቻ ቀለበቴን ፍቺ እንደምፈልግ ከሚገልፅ ደብዳቤ ጋር በሳሎን ቤታችን ጠረጴዛ ላይ አሰቀመጥኩኝ፡፡ እቃዬን በሙሉ እንድሰበስብ እናቴ አግዛኝ ከአንድ ወር በፊት ከባለቤቴ ጋር እንኖርበት ወደ ነበረ አከባቢ ለመኖር ሄድኩኝ፡፡ በጣም ነበር የተሰበርኩት፡፡ መብላትም፣ መጠጣትም ሆነ መተኛት እስከማልችል ድረስ፡፡ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ያለማቋረጥ እንቀጠቀጥ ነበር፡፡ በጋብቻችን ውስጥ ያሳለፍኩት መንገድ በሽተኛ፣ ደካማ እና ሀሳቤንም ሆነ ስሜቴን ገደለብኝ፡፡

ብዙ ኪሎ ሜትሮችን ርቄው ከሄድኩኝ በኃላ መልስ መፈለግ ጀመርኩኝ፡፡ ችግሩ መልሱን ከየት መፈለግ እንዳለብኝ አላውቅም ነበር፡፡ በዚህ ሁሉ ችግር እና ህመም ውስጥ ከከተተኝ በኃላም ባለቤቴን እወደው ነበር፡፡ ነገር ግን የሰራው ነገር ደግሜ አብሬው መኖር እንዳልችል አድርጎኛል፡፡

እኔ ፍፁም ነኝ እያልኩኝ አይደለም፡፡ እኔም የራሴ የሆኑ ብዙ ችግሮች አሉብኝ፡፡ በፊት በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት የማይገባ ነገር አደርግ ነበር፡፡ ሰለዚህ ከጋብቻችን ውጪ የሆነ ነገሮቹን ሳይቀር ከጋብቻችን ጋር አያይዤ እጨቃጨቀዋለሁ፡፡ በእርግጥ የእርሱን ፍላጎት ለማሟላት እንደሚስት ብቁ አልነበርኩም፡፡ ይህ ከሌላም ሰው ጋር ግኑኝነት ብጀምር ይፈጠራል የሚል ስጋት አለኝ፡፡

ወሲብ ሱስን አጥብቆ በመያዙ የሚወሰናቸው እያንዳንዱ አጥፊ ውሳኔዎቹ መውጣት ወደማይችልበት ድቅድቅ ጨለማ አስገብቶት ነበር፡፡

ፍቺያችን ከመጠናቀቁ በፊት በስልክ እና በኢሜል እናወራ ጀመር፡፡ የልባችንን በግልፅ በማውራት ጋብቻችን የዚህን ያህል እንዲበላሽ ምክንያት የሆነውን ነገር መፈለግ ጀመርን፡፡ እውነታው ባለቤቴ ገና እኔን ከማወቁ በፊት ጀምሮ በወሲብ ሱስ ውስጥ ተዘፍቆ የነበረ መሆኑ ነው፡፡ ሱስን አጥብቆ በመያዙ የሚወሰናቸው እያንዳንዱ አጥፊ ውሳኔዎቹ መውጣት ወደማይችልበት ድቅድቅ ጨለማ አስገብቶት ነበር፡፡ መለወጥ ይፈልጋል፡፡ እንዴት እንደሚለወጥ ግን አያውቅም፡፡ እኔም እንዴት መለወጥ እንደሚችል አላውቅም ነበር፡፡ እኔ ተስፋ ማደርገው በሚቀጥሉት ግኑኝነቶቼም ተመሳሳይ ስህተት እንዳልፈፅም ነበር፡፡ ነገር ግን እንዲህ በግልፅ ስናወራ በጣም መቀራረብ እና የተጎዳዳናቸውን ነገሮች በመነጋገር ጀመርን፡፡

ከስድስት ወራት መለያየት በኃላ እኔና ባለቤቴ እንደገና ታረቅን፡፡ በስህተት እንዳትረዱኝ፡፡ ችግሮቻችንን በአንድ ለሊት አልፈታናቸውም፡፡ ትዳራችንን የተዋበ ለማድረግ ከአስር አመት በላይ ፈጅቶብናል፡፡ ቀላል መንገድ አልነበረምነገር ግን አሁን ግኑኝነታችን ከቀድሞው የተሸለ ሆኗል፡፡

ይህ ተሞክሮዬ ወደ አንድ ድምዳሜ አደረሰኝ፡፡ የባለቤቴን ህይወት መጠገን የምችለው እኔ አይደለሁም፡፡ እኔ ማድረግ የምችው የራሴ ደካም ጎን እና አመለካከቴን በማስተካከል የተሸልኩኝ ለመኆን መጣር ነው፡፡ ችግሩ እኔ ብቻ ባልሆንም ለራሱ ምርጫዎች ተጠያቂው እራሱ ቢሆንም፤ የመፍትሄው አካል ግን ለመሆን ወሰንኩኝ፡፡

በህይወት አጋሮ አመንዝራነት ምክንያት መፍትሄ መፈለግ በጣም ከባድ እና አስቀያሚ መንገድ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለብቻዎት ማለፍ የለቦትም፡፡ ልክ እንደኔው በዚህ ውጣ ውረድ ያለፉ ብዙ ሊረዷችሁ የሚችሉ ሰዎች አሉ፡፡ የትዳር አጋራችሁ ለመለወጥ ዝግጁ ቢሆንም ባይሆንም የእርሶን ጉዳት እና መገፋት ግን በተሸለ መንገድ እንዲወጡ ልንገዳዎት እንችላለን፡፡ ከታች ያለውን ፎርም ከሞሉ ከእኛ ቡድን አንድ ሰው መልስ ይሰጦታል፡፡ ሚስጥሮት ይጠበቃል እንዲሁም በዚህ አገልግሎት የሚጠየቁት ክፍያ አይኖርም፡፡


ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡


እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡

የእርስዎ ፆታ:
የዕድሜ ክልል:

ተገቢውን አማካሪ እንዲመድብዎት የእርስዎ ፆታ እና ዕድሜ እንጠይቃለን። የአገልግሎት ውሎች & የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ.

እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!