የወደዱትን መነጠቅ
እጮኛዬ ከነበረችው ልጅ ጋር ትውውቃችን የጀመረው ሁለታችንም የዩኒቨርስቲ ሶስተኛ አመት ተማሪዎች በነበርንበት ወቅት ነበር። ብዙ ተማሪዎች ሚከብዳቸው እኔ ግን ጥሩ የነበርኩበት Machine የሚባል አንድ ኮርስ ነበር። እርሱን ኮርስ በቡድን ላስጠናቸው በምንገናኝበት ጊዜ ነበር ከሀና ጋር በተለየ መልኩ መቀራረብ የጀመርነው። እናም ይሄ ቅርርባችን እያደገ ሄዶ ወደ የፍቅር ጓደኝነት ከፍ አለ። እናስብ የነበረውም ከተመረቅን ከአንድ አመት በኋላ በትዳር ተጣምረን አብረን ቤተሰብ መመስረትን ነበር።
በሰው ህይወት ጣልቃ መግባት በምን መልኩ የዛን ሰው የህይወት እቅድ እና ሀሳብ እንደሚበጠብጥ ላናስተውለው እንችላለን። አንዳንድ ቤተሰብ ምትማረውን፣ ምትሰራውን ሁሉ ሊወስንልህ ይፈልጋል። አንዳንዱ ደግሞ የትዳር አጋርህን እኔ ካልመረጥኩልህ ይላል። እኔም የደረሰብኝ ይሄው ነው። ላገባት የመረጥኳት እጮኛዬ ቤተሰቦች በፍፁም እኔን እንድታገባ አይፈልጉም ነበር። ይልቅ የተሻለ ኑሮ የሚያኖራት፣ እነሱን የሚረዳ፣ ሀብታም እንድታገባ ነበር የሚፈልጉት።
ተቀጥሬ ከምሰራበት Software company በተጨማሪ በግሌ online ባገኝኋቸው ዌብሳይቶች ላይ የትርጉም እና coding ስራዎችን በመስራት ገቢዬን ለመጨመር እየተጋሁ በነበረበት ወቅት ሀና ቤተሰቦቿ የሚሏትን እየመጣች የምትነግረኝ እረፍት ይነሳኝ ነበር። ኑሮውን አሜሪካ ያደረገ አንድ ጎልማሳ እንድታገባ እየጨቀጨቋት እንደሆነ፣ እሺ የማትል ከሆነ ግን ከቤተሰቡ እንደሚያገሏትና ልጃቸው እንዳልሆነች እየነገሯትና እያስጨነቋት እንደሆነ ስሰማ ስራዬ ላይም ትኩረት ማድረግ እያቃተኝ እና እርሷን እንዳላጣት መስጋት ጀመርኩ። የቤተሰቧ ሁኔታ በእሷ ብቻ አላበቃም እኔም ጋር እየደወሉ መዛት እና እንደማልመጥናት ደረጃህን እወቅ በሚሉ ንግግሮች ያሸማቅቁኝ እና አንገት እንድደፋ ያደርጉኝ ነበር።
ቀስ በቀስ እነርሱ የተናገሩኝ ንግግሮች ስራዬ ላይ ያለኝን ትኩረት እየቀነሰብኝ እንዲሁም የተናገሯቸው ንግግሮች ሁሉ በውስጤ የእውነት እኔም እንደዛ እንደሆንኩ እንዳስብ እና በራሴ ተስፋ እንድቆርጥ እያደረገኝ መጣ።
ቀስ በቀስ እነርሱ የተናገሩኝ ንግግሮች ስራዬ ላይ ያለኝን ትኩረት እየቀነሰብኝ እንዲሁም የተናገሯቸው ንግግሮች ሁሉ በውስጤ የእውነት እኔም እንደዛ እንደሆንኩ እንዳስብ እና በራሴ ተስፋ እንድቆርጥ እያደረገኝ መጣ። ከዚህ አይነት ስሜት ጋር እየታገልኩ ባለሁበት ወቅት ነበር ሀና ቤተሰቦቿ የመረጡላትን ባል አግብታ ከሀገር ልትወጣ ዝግጅት ላይ እንደሆነች የሰማሁት።
በዚህ ጊዜ ነው የመኖር ትርጉሙ የጠፋብኝ፤ ለምን፣ ለማን፣ እንዴት እንደምኖር ለራሴ መልስ ያጣሁበት ጊዜ ነበር። ይሄ ስሜት በተደጋጋሚ ወደ ውስጤ ሲመላለስ በስተመጨረሻም የወሰንኩት እራሴን አጥፍቼ ለመገላገል ነበር።
በአንድ ዌብሳይት ላይ እራስን ስለማጥፋት ጥቂት ያነበብኩት ሀሳብ እርምጃዬን እንድገታውና ቆም ብዬ እንዳስብ አድርጎኛል። ራስን ማጥፋት ምን ያህል ራስ ወዳድነት እና እኛን በማጣት የሚጎዳውን ሰው አለማሰብ እንደሆነ፤ ነገ ሌላ ቀን እና ሌላ እድል ይዞ እንደሚመጣ አዲስ የህይወት ምዕራፍ እንደሆነ ይናገራል።
ይሄኔ እንደገና ማሰብ እንዳለብኝና ቢያንስ ለአንድ ሰው ማካፈል እና ሸክሜን በማጋራት መፍትሔ እንዲሰጠኝ ማድረግ እንዳለብኝ ተሰማኝ።
ይሄኔ እንደገና ማሰብ እንዳለብኝና ቢያንስ ለአንድ ሰው ማካፈል እና ሸክሜን በማጋራት መፍትሔ እንዲሰጠኝ ማድረግ እንዳለብኝ ተሰማኝ። አሁን ላይ የ 29 አመት ወጣት ነኝ። ይሄን ሁሉ ያለፍኩበትን ለመጀመሪያ ጊዜ አብሮኝ ለሚሰራ እንደ ጥሩ ወንድም ለቀረበኝ የስራ ባልደረባዬ አካፈልኩት። እነዛን መጥፎ ጊዜያት፣ መጥፎ ንግግሮች፣ እነዚያን ተስፋ የቆረጥኩባቸውን ጊዜያት ሁሉ አወራሁት። ሳወራው ከአይኖቼ እንባ ይወርድ ነበር፤ እጆቼ ይንቀጠቀጡ ነበር። በደንብ ከሰማኝ በኋላ ብዙ ምክሮችን መከረኝ። እናም የህይወቴን አቅጣጫ መስመር ማስያዝ ጀመርኩ።
ዛሬ ይህን የምታነቡ፦ እንደእኔ አይነት ሁኔታ ውስጥ የምታልፉ ካላችሁ፤ ትላንት በህይወታችሁ ያለፋችሁበት ከባድ ነገር ዛሬያችሁን እየጎዳው ከሆነ ብቻችሁን አይደላችሁም። እነርሱ ያሏችሁን፣ የተናገሩባችሁን አይደላችሁም። ልታወሩት እና የከበዳችሁን ነገር ልታካፍሉት የምትፈልጉት ሰው ከፈለጋችሁ እኛ አለን። ከዚህ በታች ባለው ክፍት ቦታ ልናገኝዎት የምንችልበትን ሙሉ አድራሻ ብቻ ይሙሉና አንድ ሰው ያነጋግሮታል።
ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡
እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡
እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!