የተደበቁ ነገሮች
ለመጀመርያ ጊዜ ያየሁት ካፌ ውስጥ ነበር። በ17 አመቴ። ከጓደኞቼ ጋር ነበርኩ። የተቀመጥንበት ቦታ መጥቶ ተዋወቀን። ከእኛ ቢያንስ በ10 አመት ቢበልጠንም ጓደኞቼ በጣም ተምችቷቸው ወደውት ነበር። እኔ ግን ምንም ደስ አላለኝም ነበር። ፍቅረኛ እንዳለችው ሲያወራ ነበር ግን ሁሉንም ሴቶች ያሽኮረምማል፣ ከሁሉም ሰዎች ጋር ይቀልዳል። በእርግጥ ባህሪው ደስ የማይል ቢሆንም ከእሱ ጋር መሆን ብዙም አይደብርም ነበር።
አንድ ቀን ከትምህርት ቤት ወደ ቤት እየሄድኩ እያለ ከኋላዬ መጥቶ “ወደ ቤት እየሄድሽ ከሆነ ልሽኝሽ በሰላም መግባትሽን ማረጋገጥ ፈልጋለው” አለኝ። ድፍረቱ ገረመኝ ፈገግ አልኩና “ይቻላል” አልኩት። ይሄ የየቀኑ ልማዳችን ሆነ። ሁልጊዜ ሲሸኘኝ ስላነበባቸው መጽሐፎች እና የድሮ ታሪኮች ይነግረኝ ነበር። ብዙ ጊዜ በአንድ ነገር ሳንስማማ ቀርተን ስንከራከር ደስ ይለው ነበር። በክርክር ችሎታዬ ይገረም ነበር። በእኔ እድሜ ካሉት ሴቶች በአስተሳሰብ የተለየሁ እንደሆንኩ እና ከእድሜዬ በላይ እንደማስብ ሲነግረኝ ፊቴ በደስታ ይድምቅ ነበር።
በሚያሳየኝ ፍቅር እና እንክብካቤ የተለየው ሴት እንደሆንኩ ተሰማኝ። ለእሱ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆንኩ ይነግረኝ ነበር። ምን ያህል ተሰጥኦ እንዳለው እና ለትልቅ ነገር እንደተፈጠረ ግን በጣም ደካማ እንደሆነ እና የሚያግዘው ሰው እንደሚፈልግ ይነግረኛል። ቤተሰቦቹ እንዳልተረዱት ፍቅረኛው ራሱ እንዳልተረዳችው እና በትክክል የተረዳሁት እኔ ብቻ እንደሆንኩ ሲነግረኝ በጣም አዘንኩለት።
የምናወራውን ነገር በሚስጥር መያዝ እንዳለብኝ ይነግረኝ ነበር። ምክንያቱም ጓደኞቻችን ጥሩ ነገር ላያስቡ ወይም ግንኙነት እንዳለን ሊጠረጥሩ ይችላሉ። ስለዚህ ለወላጆቻችንም ሆነ ለጓደኞቻችን በተለይ ለፍቅረኛው መናገር እንደሌለብን ተስማማን። ሰዎች እንዳይጠረጥሩን በማሰብ ይሄን ሚስጥር ለመጠበቅ ምን ያህል እጨነቅ እንደነበር አስታውሳለሁ። እንዚህን ነገሮች የተጠቀመው እኔን ለማታለል እንደሆነ የገባኝ አሁን ነው።
እነዚህ ነገሮች አታላይ የሆኑ ወንዶች ሴቶችን ለማታለል የሚጠቀሙባቸው ነገሮች እንደሆኑ የገባኝ ዘግይቶ ነበር። በመጀመርያ ልሸኝሽ እያለ ከሌሎች ሰዎች ማግለል በመቀጠል በሽንገላ ቃላት እና ስለ ጋራ ፍላጎቶችና አስተሳሰቦች ማውራት በተለይ ስሜታቸውን በመቆጣጠር እና በርህራሄ መቅረብ ይሄ ደግሞ በጋራ ሚስጥሮች ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ትስስር ይፈጥራል።
18 አመት ሆነኝ። አንድ ቀን እንደተለመደው ከሸኘኝ በኋላ ቤቴ በር ላይ ስደርስ ሳላስበው ለመጀመርያ ጊዜ ሳመኝ። ከዚያ ሁሉም ነገር እየጨመረ መጣ። ማታ ላይ በመኝታ ቤቴ መስኮት በኩል ይመጣና “ይሄ ልቤ ነው ውሰጂው አንቺ ጋር ይሁን” የሚል ደብዳቤ ሰጥቶኝ ይሄዳል።
ላይለቀኝ አጥብቆ የያዘኝ ይመስል ነበር። እውነት ለመናገር እኔም መያዙን ወድጄው ነበር። የሚያስደስተኝን ነገር አስታውሶ ሲያደርግ ይገርመኝ ነበር። ነገር ግን ጥንካሬው በጣም የሚያስደነግጥ እና የሚያስፈራ ነበር።
ስመኘው የነበረው እያንዳንዱ ፍቅር ከጊዜ ወደ ጊዜ ይበልጥ ግልጽ በሆኑ ባህሪዎች መተካት ጀመረ።
እንደፈራሁት ጥንካሬው ወደ ወሲባዊ ፍላጎት ተቀየረ። ግራ የተጋባ ስሜት እንደተሰማኝ አስታውሳለሁ። ድንጋጤ፣ የማወቅ ጉጉት፣ መገፋት፣ መደሰት፣ መነቃቃት እነዚህ የተደበላለቁ ስሜቶች ቋሚ ከሆነው የሀፍረት ስሜት ጋር ተደምረው ግንኙነታችን ወሲባዊ ግንኙነት እንዲሆን የፈቀድኩ መስሎ ይስማኝ ጀመር።
ስመኘው የነበረው እያንዳንዱ ፍቅር ከጊዜ ወደ ጊዜ ይበልጥ ግልጽ በሆኑ ባህሪዎች መተካት ጀመረ። ሁሉም ነገር እየተቀየረ የመጣው ቀስ በቀስ ስለነበር ግንኙነታችን ወደ ወሲባዊ ግንኙነት እየተቀየረ መሆኑን ማስተዋል አልቻልኩም ነበር። ሲያደርጋቸው የነበሩት ነገሮች በሙሉ እኔን ኢላማ አድርጎ ቢሆንም እኔም የድርጊቱ ተባባሪ እንደሆንኩ እንዳምን አድርጎኝ ነበር። በዚህ ከቀጠልን ልቤን ሊሰብረው ወይም ስሜቴን ሊጎዳው እንደሚችል አሰብኩ እና ግንኙነታችንን በፍጥነት ማቆም እንዳለብኝ ወሰንኩ። ግንኙነታችንን ማቆም እንዳለብን የነገርኩት ቀን በጣም ተናደደብኝ፣ አመንጫጨቀኝ፣ ሰደበኝ። የምወደውና ይወደኛል ብዬ ማስበው ሰው በዚህ መንገድ ያስተናግደኛል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር። ባላስተዋልኩት እና ባላሰብኩት መንገድ ወሲባዊ ጥቃት ሊደርስብኝ እንደነበር ለማመን አመታት ፈጅቶብኝ ነበር።
ምንም እንኳን ከወሲባዊ ጥቃት ባመልጥም አልፎ አልፎ በአጋጣሚ ከልጁ ጋር መንገድ ላይ እንገናኛለን። አንዳንዴ ሳየው ምንም አይመስለኝም። አንዳንዴ ግን ስለ እሱ ማሰብ እጀምራለሁ፤ አሁንም ለእሱ ያለኝ ፍቅር እንዳልጠፋ አስባለሁ። ሆኖም አንዳንድ ቀን እንደተገፋሁ እና እንደተደፈርኩ ይሰማኝና መንቀጥቀጥ እጀምራለሁ። በዚህ ጊዜ ከባድ የሆነ ድብርት እና ጭንቀት ውስጥ እገባለሁ።
አሁንም ራሴን ለወሲባዊ ጥቃት ተጋላጭ ያደረኩት ራሴው ነኝ ብዬ ስለማስብ ሊደርስብኝ ለነበረው ጥቃት ተጠያቂ ራሴ እንደሆንኩ አስባለሁ። ምንም እንኳን አሁን ባለኝ እውቀት፣ ከወሰድኳቸው ህክምናዎች እንዲሁም ከአመታት ጸሎት በኋላ አሁንም ጥፋተኛ እንደሆንኩ ይሰማኛል።
የወሲባዊ ጥቃት ሙከራ ደርሶቦት የሚያውቅ ከሆነ ቁስሎቹ ጥልቅ ናቸው። ጠባሳዎቹ ከባድ ናቸው። ስሜቶቹ ውስብስብ ናቸው። ነገር ግን ብቻዎትን አይደሉም። ልናማክሮት ዝግጁ ነን።
ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡
እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡
እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!