በዝምታ መሰቃየት

ሁሉም ነገር የጀመረው የስድስት አመት ልጅ እያለሁ ነበር፡፡ አባቴ ባገኘው የስራ እድል ከምንኖርበት አከባቢ ወደሌላ አከባቢ ተዘዋወርን፡፡ በአውሮፕላን ለመሄድ ከፍተኛ ጉጉት ነበርኝ፤ ህፃንም አይደለሁ? ከሀገር ለመውጣትም የመጀመሪያዬ ነበር፡፡ ወደ አዲስ ሀገር ሄጄ አዲስ ጓደኛ ለማፍራት እና አዲስ ህይወት ለመኖር በጣም ጓጉቼ ነበር፡፡

ነገር ግን ይኼ ሁሉ ሃሳብ በአንዲት አስከፊ ቀን ተሰባብሮ ቀረ፡፡ በቤታችን ውስጥ የነበር የበር ጠባቂያችን ወሲባዊ ጥቃት ፈፀመብኝ፡፡ ይህንን ነገር ለማንም አልተናገርኩም፡፡ ማንም ሰው አላወቀም፡፡ የሌላን ሰው እርዳታ የምጠይቅበት አቅም አልነበረኝም፡፡ ሰውዬውን በጣም ፈራሁት፡፡ በዚህ ምክንያት ቤት ውስጥ ሌላ ሰው ከሌለ ሰው እስከሚመጣ ድረስ መታጠብያ ቤት ገብቼ በሩን በራሴ ላይ ቆልፌ እጠብቃሁ፡፡ በድጋሚ ጥቃት እንዳያደርስብኝ ሰለምፈራ፡፡ ከመታጠቢያ ቤቱ የምወጣው ሰው ከመጣልኝ ብቻ ነው፡፡ በመጨረሻም ያደረገብኝ ነገር ገሀድ ውጥቶ ከእኛ ቤት ተባረረ፡፡

ትልልቅ ሰዎች ህፃናትን መጉዳት ይሰልጋሉ ብዬ አስቤ አላውቅም፡፡

ያደረገብኝ ነገር ገሀድ ውጥቶ ከእኛ ቤት ተባረረ፡፡ ነገር ግን የእኔ ስቃይ በዚህ ብቻ አላበቃም፡፡ ከእሱ በኃላ ለቤተሰቤ በጣም ቅርብ የሆኑ ሰዎች ለስድስት ተከታታይ አመታት ወሲባዊ ጥቃት አድርሰውብኛል፡፡ ምን ለዚህ እኩይ ተግባራቸው እኔ ብቻ እንደሚመርጡ አይገባኝም፡፡ አይን አፋር ስለሆንኩኝ ለማንም አትናገርም ብለው ይሁን? ቤተሰቤ ጥሩ የኑሮ ደረጃ ሰለሌለው ይሁን? ከአጎቶቼ ልጆች የሚደርስብኝ ወሲባዊ ጥቃት ፈሪ አደረገኝ፡፡

ትልልቅ ሰዎች ግን ለምን ህፃናትን ይጎዳሉ? በእኔ ጥፋት ነው ብዬ አስብ ነበር፡፡ የተረገምኩ ሰለሆንኩኝ ይሁን? በደረሰብኝ ነገር በጣም እሸማቀቅ ሰለነበር ለማንም አልተናገርኩም፡፡ ቤተስቦቼ ምን ይላሉ የሚለው ያሰፈራኛል፡፡ ምንም እንዳልተፈጠረ ራሴን አሳምኜ መኖር ጀመርኩኝ፡፡ የሆነውን ነገር በረሳሁ ቁጥር ጥቃቱም ይቆማል ብዬ አሰብኩኝ፡፡፡ ምንም ያህል ጥርት ባደርግም እራሴን ከመውቀስ ማምለጥ አልቻልኩም፡፡ በዚህ ሁሉ እራሴን እንደመጥፎ ሰው ነበረ የማየው፡፡ እራሴን መውቀስ በዝቶብኝ ምንም ነገር በትክክል ማሰብ እንዳልች አደረገኝ፡፡

እያደኩኝ ስመጣ ግን የደረሰብኝ ነገር ጥቃት ብቻ ነው ብዬ ማሰብ እየተሳነኝ መጣ፡፡ የደረሰብኝን ጥቃት ልረሳው ብሞክርም የቁስሉ ጠባሳ የመረቀዘ ነበር፡፡ መርሳት አልቻልኩም፡፡ ሴትነቴን አጥብቄ እጠላው ጀመር፡፡ ወንዳወንድ ሆንኩኝ፡፡ ሰውን ማመን አቆምኩ በተለይ የቅርብ ዘመዶቼን፡፡ ተጠራጣሪ እና ሀይለኛ ነበርኩን፡፡

አሁን እድሜዬ ወደ አርባዎቹ ይጠጋል ነገር ግን የደረሰብኝ ጥቃት ትዝታዎች እስከአሁን አልደበዘዙም፡፡

ዚህ ጊዜ የምነግረው ሰው እንደሌለ ተረዳሁ፡፡ ወላጆቼ እንኳን የደረሰብኝን ከሰሙ በኃላ እንዴት ሊረዱኝ እንደሚችሉ አላወቁም፡፡ ጊዜ ይፈታዋል ወይም የተፈጠረውን ነገር በጊዜ ብዛት ትረሳዋለች ብለው ዝም አሉኝ፡፡ እኔ ግን እንኳን ልረሳው ህመሙ ልቤንም መንፈሴንም ተቆጣጥሮት አረፈው፡፡ ችግሬን የምነግረው ጓደኛ አጥብቄ እፈልግ ነበር፡፡ አንድ ሰው አስፈልጎኝ ነበር፤ የተፈጠረው ነገር የእኔ ጥፋት እንዳልሆነ የሚነግረኝ፡፡ ለብቻዬ እንዳልሆንኩኝ እንዳይሰማኝ የሚያደርገኝ ጓደኛ እፈልግ ነበር፡፡ ነገር ግን ማግኘት አልቻልኩም፡፡

አሁን እድሜዬ ወደ አርባዎቹ ይጠጋል ነገር ግን የደረሰብኝ ጥቃት ትዝታዎች እስከአሁን አልደበዘዙም፡፡ እያንዳንዱን ጥቃት በሚገባ አስታውሳለሁ፡፡ አሁን የልጆች እናት ሆኜ ልጆቼ ወደ ትምህርት ቤት ሲሄዱም ሆነ ለመጫወት ሲወጡ በጣም እጠራጠራሁ፡፡ ሰለወሲባዊ ጥቃት ነግሬቸው አስጠንቅቄቸዋለሁ፡፡ ወደኃላ ተመልሼ ምን አለበት ለሰው ተናግሬ እና እርዳታ አግንቼ ቢሆን ብዬ እፀፀታሁ፡፡ ዛሬ ካለኝ ህይወት የተሸለ ህይወት የኖረኝ ነበር ብዬም አስባለሁ፡፡

ተፈፅሞቦት የሚያውቅ ከሆነ እንደእኔ በዝምታ እንዳታልፉት፡ ወሲባዊ ጥቃት ፡ የጥቃቱን ትዝታ እና ህመም በውስጣችሁ መያዝ ጥቃቱ የባሰ እንዲጎዳችሁ ሀይል ይሰጠዋል፡፡ ይህንን ለብቻዎት መጋፈጥ የለቦትም፡፡ ከእኛ መካከል ሚስጥር ጠባቂ የሆነ አማካሪ በነፃ ማግኘት ይችላሉ፡፡ አድራሻዎትን ከታች ካስቀመጡልን ወዲያው የሚያማክሮት ሰው መልስ ይሰጦታል፡፡ ትክክለኛ ስሞትን ወይም የሌላ ሰው ስም መስጠት ይችላሉ፡፡

ፎቶ በ: Gift Habeshaw

ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡


እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡

የእርስዎ ፆታ:
የዕድሜ ክልል:

ተገቢውን አማካሪ እንዲመድብዎት የእርስዎ ፆታ እና ዕድሜ እንጠይቃለን። የአገልግሎት ውሎች & የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ.

እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!