መተማመንን እንደገና መገንባት

በአንድ ወቅት ከደንበኞቼ አንዷ ሌላውን ሰው ማመን ምን ማለት እንደሆነ ጠየቀችኝ። የትዳር ጓደኛዋ ወይም በህይወቷ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው አንድ ሰው ግድየለሽ፣ እምነት የጎደለው ወይም ከሌላ ሰው ጋር ያልተገባ ግንኙነት ሲፈጠር ምን ማድረግ እንዳለባት ማወቅ ፈለገች። በጣም ባሳዘናት ሰው ላይ ድጋሚ እምነት መገንባት ይቻልስ እንደሆን ጠየቀችኝ።

ሰውን ማመን ምንን ያሳያል? እምነት፤ በተግባራዊ መልኩ አንድ ሰው ለእርስዎ ታማኝ እንደሆን መተማመን ማለት ነው። ለእርሶ ታማኝ እንዲሆኑ እና ቃላቸውን፣ መሐላቸውን እና ሚስጥርን እንዲጠብቁ ይጠብቃሉ። ከምንም በላይ በምንም ሁኔታም ቢሆን አይተወኝም ብለው ያስባሉ።

  • ስለ እምነት ግምት ውስጥ መግባት ያለባቸው አንዳንድ ነገሮች:

ሰውን ማመን፤ ስለ ሰዎች ትክክለኛ አመለካከት መያዝን እና ምናልባትም የግንኙነት መሻከር ሊፈጠር እንደሚችል መጠበቅን ይጠይቃል። መተማመን የሰዎች ቅቡልነት እና ፍቅር እንዲሁም ይቅር የማለት ልብ ባለባቸው ግንኙነቶች ውሰጥ እጅጉን ይዳብራል።

እምነት፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚጨምር የሂደት ውጤት ነው። ሰዎች በብዙ ነገሮች ስሜታቸው የተጎዳ ውስብስብ ፍጥረታት በመሆናቸው፣ ከዚህ ቀደም የደረሱባቸው ጉዳቶች፣ ወይም መጥፎ የግንኙነት አጋጣሚዎች፤ በግንኙነት ውስጥ ለመተማመን ወይም ግልጽ ለመሆን ያላቸውን ፍላጎት ሊገታ ይችላል። ነገር ግን ሰዎች ወደ እውነተኛነትና ታማኝነት የማደግና የመለወጥ ታላቅ አቅም እና ችሎታ አላቸው።

  • ለሰዎች የሚሰጡትን ግምት ያስተካክሉ

ሰዎች ሰው በመሆናቸው፣ አቅመ ደካሞች እና ለበደል የተጋለጡ ናቸው። ስለዚህ፣ አንድን ሰው ለማመን በምትወስኑበት ጊዜ የገሃዱን አለም መሰረት ያደረገ እውነተኛ የእምነት ደረጃ ሊኖራችሁ ያስፈልጋል። ከአንድ ሰው ጋር ጊዜ ሲያሳልፉ፤ ስለዛ ሰው ያለዎት የእውቀት ደረጃ፤ መረዳት እና ትክክለኛነት ስለሚጨምር፤ ከጊዜ ወደ ጊዜ መተማመናችሁ እና ግንኙነታችሁ ይጎለብታል፡፡ ስለዛኛውም ሰው ባህሪ፣ ፍላጎት፣ ተነሳሽነት እና ፍራቻ በቂ ግንዛቤ ያገኛሉ።

ቅድመ ሁኔታ የሌለው ፍቅር ቅን እና ታጋሽ ነው

ይህን አይነት ፍቅር ለአንድ ሰው በገለጽክ ቁጥር፤ እሱ ወይም እሷ በአጠቃላይ ተቀባይነትህን ስለሚገነዘቡ በመሀከላችሁ ያለው መተማመንን ይዳብራል። ባላቸው ስሜት እውነተኛና ትክክለኛ መሆን የበለጠ ምቾት ይሰማቸዋል። ቅድመ ሁኔታ የሌለው ፍቅር በሌሎች ላይ በራስ የመተማመን ስሜትን ከማዳበር ባሻገር፤ በሌሎች የመተው ፍርሃታቸውን ያቃልላል። ሰዎች ስለ ስሜታቸው፣ ሃሳባቸው እና ድክመቶቻቸው ከእርስዎ ጋር እውነተኛ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይማራሉ። ውጤቱም በሌላው ሰው ላይ ያለው እምነት እያደገ መምጣት ነው። ይህም የሚሆነው ያ ሰው ፍጹም እየሆነ ስለመጣ ሳይሆን፤ በሐቀኝነት እያደገ በመምጣቱ ነው።

በፍርሃት ላይ የተመሰረተ ፍቅር ሁኔታውን መሰረት ያደረገ ነው። አለማመንን፣ አለመተማመንን እና አለመረጋጋትን ይፈጥራል ቅድመ ሁኔታ የሌለው ፍቅር ማለት፤ ራስን መፈለግ ማለት አይደለም፤ በደልንም እያጠራቀመ አይዝም። ፍቅር ታጋሽ ወይም ዘላቂ ካልሆነ ይልቁንም ይቅር የማይልና ሁልጊዜ የሚያሳዝን ከሆነ ወይም ደግሞ ስህተት ፈላጊ ከሆነ፤ በሌላኛው ሰው ላይ ፍርሃትን ይፈጥራል። እናም የሌላውን ጉድለት እና ክፍተት ብቻ ይፈልጋል።

ሰዎችን በጥልቀት እያወቅናቸው ስንሄድ የተወሰነ እምነት ልናዳብር እንችላለን። እነርሱም ስለእነሱ ግድ እንደሚለን ይገነዘባሉ። እውነታው ግን ይዋል ይደር እንጂ ሰዎች ያሳዝኑናል። በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው አንድ ሰው ቃልኪዳኑን ካፈረሰና ታማኝ ካልሆነ፤ ወይም በግንኙነት ውስጥ ሲዋሽ ወይም እምነት የጎደለው ከሆነ መለወጥ አለበት። ድርጊቱ አግባብ እንዳልሆነ በማስረዳት እንዲለወጥና ባህሪውን እንዲያስተካክል በመጠየቅ ግንኙነቱን ለማስቀጠል ሃላፊነት ልንወስድ እንችላለን። ሆኖም ግን፣ ያ ሰው ካልተቀየረና መዋሸቱን ወይም ክህደቱን ከቀጠለ፤ ግንኙነቱን ማቆምን ግምት ውስጥ ማስገባት አስፈላጊ ነው።

  • እራስህን ተመልከት

መቼም ፍፁም ስላይደሉ የሚወዱትን ሰው ያሳዝኑ ይሆናል። የሚጎዳ ነገር ላለመናገር፣ በፍጹም ላለመዋሸት፣ በጭራሽ ላለማጋነን ወይም ሁልጊዜ የገቡትን ቃል ለመጠበቅ ቃል ሊገቡ ይችላሉ። ነገር ግን፣ ሰው ስለሆኑ፣ የገቡትን ቃል መጠበቅ ይሳንዎታል። እናም በዚህ ምክንያት ሌሎችን ያሳዝናሉ። ማንኛውም የሰው ልጅ በግንኙነት ውስጥ ጉዳት ይገጥመዋል። ስለዚህ ሁላችንም የተሻልን ይቅር ባዮች እና በደላችንን አማኞች መሆን አለብን። ለእርቅ የትህትና መንፈስ ካለን፤ የፍቅራችንን እና የፍላጎታችንን ጥልቀት ያረጋግጣል። ይቅር ለማለት እና ለመተማመን ስለሚደረገው ትግል የበለጠ ለመረዳት፣ ይቅር ማለት በጣም ከባድ የሆነው ለምንድነው? የሚለውን ያንብቡ። ፍቅር፣ ይቅር ባይነት እና ቁርጠኝነት በግንኙነት ውስጥ እንደ መታመን እና ሐቀኝነት አስፈላጊ ናቸው። ይቅርታ አዲስ ግንኙነት እንድትጀምሩና ሌላ የሚሳሳት የሰው ልጅ እንድታምኑ እድል ይሰጣችኋሃል። ፍቅር እምነትን ያጠነክራል። የልብ ፍላጎትና ታማኝነት አንዱ ለሌላው ያለውን ሃላፊነት ያጎለብታል። እነዚህን ሶስት በጎነቶች ይኑሩ። እናም መተማመን በግንኙነትዎ ውስጥ ማደግ ሲጀምር ያያሉ።


ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡


እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡

የእርስዎ ፆታ:
የዕድሜ ክልል:

ተገቢውን አማካሪ እንዲመድብዎት የእርስዎ ፆታ እና ዕድሜ እንጠይቃለን። የአገልግሎት ውሎች & የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ.

እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!