የእርካታ እቃ
ሃና ለመጀመሪያ ጊዜ ስትደፈር አስራ አምስት ዓመቷ ነበር፡፡ በአንድ ሆቴል የሚገኝ የመዋኛ ገንዳ ለማዋኘት ሄዳ ብዙ ሰዎች አብረዋት እየዋኙ ስለነበር ደህነንት ተሰምቷት ነበር፡፡ ነገር ግን የነበሩት ሰዎች ትተው ሲሄዱ እርሷ እና አንድ ሰውዬ ብቻ ቀሩ፡፡ ይህ ሰውዬ እርሷ ያላሰበችውን ነገር አስቦ ነበር፡፡
ሙሉ ታሪኳን ይመልከቱ
ለሽኝት በሚል ሰበብ ወደ መኝታ ክፍሏ ተከተላት፡፡ ከዛም ተከትሏት ወደ ክፍሏ ገባ፡፡ ከዛ መታጠቢያ ቤቱን ውሃ ከፈተላት እናም በሚቀጥለው ቀን ጠዋት እዛው መታጠቢያ ውስጥ በቀዝቃዛ ውሃው ገንዳ ውስጥ ሆና እራሰዋን አገኘችው፡፡
ሀያ አንድ አመት ሲሞላትም በድጋሚ የአስገድዶ መድፈር ጥቃት ሰለባ ሆነች፡፡ ከፍቅረኛዋ እና ከሌሎች ጓደኞችዋ ጋር ፊልም ለማየት ሄዳ የተዘጋጀላትን ድግስ አላወቀችም ነበር፡፡ በዛን እለት የእነርሱ መዝናኛ እርሷ እንደሆነች፡፡
ምንም እንኳን የእርሷ ጥፋት ባይሆንም ሃና የደረሰባትን ሀፍረት እና የጥፋተኝነት ሰሜት ለመውጣት አመታትን ፈጅታለች፡፡ እራሷን ይቅር ማለት ይህም በእርሷ ህይወት ያለፈው የእርሷ መገለጫ ወይም የሚከተላት አለመሆኑን ከመረዳት መጀመር ነበረበት፡፡ በሂደት መወደድ የሚገባት መሆኑን ተረዳች፡፡ የእርሷ ዋጋ ሌሎች ሰዎች በእርሷ ላይ ባደረሱት ቆሻሻ ነገር የሚቀንስ አይደለም፡፡ ሰለዚህ ቆሻሻዋን አራግፋ እራሷን አሳምና ተነሳች፡፡
**የአስገድዶ መድፈር ጥቃት ሰለባ ከነበሩ ቁስሉ በጣም የጠለቀ፣ ጠባሳው አስከፊ እና ስሜቱ የተዘበራረቀ ነው፡፡ ነገር ግን ብቻዎትን አይደሉም፡፡ አድራሻዎትን ከስር ካስቀመጡል ከቡድናችን አንድ ሰው ይገኛኞታል፡፡ **
See also: Swati story: "Suffering in Silence".
Author's initials used for privacy.
ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡
እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡
እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!