እያንዳንዱ ቀጠሮ ውጊያ ነበር
ለ7 አመታት የወንድ ጓደኛዬ እና እኔ አንዳችን ከአንዳችን ላይ እጃችንን መሰብሰብ ከብዶን ነበር። ከመጀመሪያው ጀምሮ እንደምንጋባ አውቀናል ግን ይሄንን መቼም ለዝሙት ፍላጎታችን ምክንያት አድርገን አቅርበን አናውቅም። ክርስትያን ቤተሰብ ውስጥ እንዳደገ ንጽህና በጣም አስፈላጊ እንደሆነ አውቃለሁ ግን እንደዚህ ከባድ ይሆናል ብዬ አስቤ አላውቅም።
እያንዳንዱ ቀጠሮ ውጊያ ነበር። ሁሌ አይኖቻችን ሲገናኙ ስጋችን መንፈሳችንን ይዋጋዋል።
ሁሌም “በጣም ርቀን” እንድንሄድ የፈቀድን ጊዜ ወዲያው እንጸጸታለን። “ይቅርታ” “መምጣት እንዳልነበረብኝ አውቃለሁ።” “ይሄ በድጋሜ ሊፈጠር አይገባም።” “ከዚህ መውጣት አለብን።” “የሆነ ሰው እናናግር።” የመጀመሪያ “በጣም ረዥም ርቀት” የወሰድነው ጊዜ አለቀስኩ። ባለፈው ግንኙነቴ የነበረው የተበላሸ የወሲብ ህይወቴ ወደ “እግዚአብሄራዊው” ግንኙነቴ መምጣቱን ማመን ከበደኝ። ጓደኛዬ ጋር ደወልኩ እና በንጽህና ለመኖር እንደከበደን ነገርኳት። “ተጠያቂ” እንድታደርግኝ ጠየኳት። አሁን ዞር ብዬ ሳየው ለችግራችን መፍትሔ ትሆናለች ብዬ ነበር የጠበኩት ግን ነገሩ እሱ አልነበረም። ከሳምንታት በኋላ ውጊያው ቀጠለ። በግንኙነታችን ውስጥ ያለው የንጽህና ውጊያ የበለጠ ከበደ። ለየብቻችንም ሆነን ለንጽህና እንቸገር ነበር። በልጅነቴ ነው ለወሲብ ፊልም የተጋለጥኩት እና ከዛ ጊዜ ጀምሮ በማስተርቤሽን እቸገር ነበር። የእሱም ልጅነት አንድ አይነት መስመር ያለው ነው። በአንድ በኩል ብቻ ያለ ችግር አልነበረም። በሁለታችን ህይወት ሰይጣን በብዙ በኩል እግሩን እያስገባ ነበር።
ፍጹም መሆን እፈልግ ነበር። ‘ሀጢያት’ መስራት አልፈልግም ነበር። ግን እውነታው እንደዛ አይደለም።
በአመታቱ ውስጥ የእምነቴ እውነተኝነትን እጠይቅ ነበር። “ በእውነት ክርስትያን ከሆንኩ እንደዚህ አልቸገርም ነበር። እንደዚህ ከባድ መሆን የለበትም።” “አሁን ላይ ራሳችንን መቆጣጠር የምንችልበት ጊዜ መሆን ነበረበት። ፍጹም መሆን ፈልግ ነበር። ‘ሀጢያት’ መስራት አልፈልግም ነበር። ግን እውነታው እንደዛ አይደለም። ሰው ነኝና በህይወት እስካለሁ ድረስ፤ ችግር የህይወት አንድ አካል መሆኑን አምኜ መቀበል አለብኝ። በተለመደው የድሮው ኡደት እየተኖረ ሁለት አመታት አለፉ። ‘እንወድቃለን’ እግዚአብሄር ይቅር እንዲለን እንጠይቀዋለን፤ ጓደኞቻችን ተጠያቂ እንዲያደርጉን እንናገራለን ከዛ በድጋሜ እንወድቃለን። መጋባት ብቸኛው “መፍትሔ” ሆኖ ታየን ግን መጋባት በጣም ሩቅ ነበር። ሁሌም እቀልድ ነበር፤ “ወላጆቼ እንዳገባ የሚፈቅዱልኝ ብቸኛው መንገድ ካረገዝኩ ብቻ ነው” እያልኩ። 5 አመታችን ላይ አስታውሳለሁ ማግባት ፈልጋለሁ ምክንያቱም እየተፈተንን ነው ብዬ ስነግራቸው። “ለምን ፈተና ይኖራል? እንዳትፈተኑ።” ብለው ወላጆቼ መለሱልኝ።
ከራሳችን ጋር በመጣላት ሰባት አመት አለፈን፤ አንዳችን ሌላችን የበለጠ ለማወቅ በመፈለግ ውስጥ ግን ሁሌም አብሮ መሆናችን የሚመራን እግዚአብሄርን ወደ መጉዳት ብቻ ነው።
እሱም ለወላጆቹ ነገራቸው፤ ፈተናው ከባድ እንደሆነ። “ሁሌም ጸልይ” ነበር የወላጆቹ መልስ። እንግዲህ 7ተኛው አመት መጣ እና ከብዙ የዝሙት ፍላጎታችን እና እግዚአብሄርን የመፍራት ውጊያ በኋላ፤ በጣም በጣም በረዥሙ ሄድን። ለማህበረሰባችን ነገርን እና ተጋባን። ዞር ብዬ ሳየው በጣም ዝያለሁ። በእያንዳንዱ ቀን የወሲባዊ ንጽህናን ህመም እና ችግር እኖረዋለው። ከራሳችን ጋር በመጣላት ሰባት አመት አለፈን፤ አንዳችን ሌላችን የበለጠ ለማወቅ በመፈለግ ውስጥ ግን ሁሌም አብሮ መሆናችን የሚመራን እግዚአብሄርን ወደ መጉዳት ብቻ ነው። ለማህበረሰባችን ስንናገር፤ የሰዎች አዕምሮ ውስጥ ምን እንደነበር ባውቅ እላለሁ ሰዎች “ከጋብቻ በፊት ወሲብ ፈጽመዋል” ሲባሉ።
ከንጽህና ጋር የታገሉ እና “እኔ ብቻ አይደለሁም የተያዝኩት” ብለው ያሰቡ ስንት ሰዎች እንዳሉ ማወቅ ፈልግ ነበር። የምናልፍበትን በእርግጥ የሚረዳ ሰው ላወራው የምችል ብዬ እመኛለሁ፤ “አቁሚ” የሚሉኝ ሰዎች ብቻ ሳይሆኑ ግን በዚህ ውስጥ ከእኔ ጋር የሚጓዙ፤ የሚገኙ እና ሳይፈርዱ የሚያዳምጡ ሰዎች። ምናልባት በዚህ መንገድ ቀላል ይሆን ነበር። በእኔ እይታ መፍትሔው በሰዎች መከበብ እና በግልጽ ከሰዎች ጋር መነጋገር ነው። ስለሚከብዱን ነገሮች ከሚታመን ሰው ጋር በግልጽ ማውራት እውነተኛ ነጻነት ይሰጣል። ከእኔ ታሪክ ጋር የሚመሳሰል ነገር አላችሁ? ከንጽህና ጋር ትታገላላችሁ? ከሆነ ብቻችሁን አይደላችሁም። ከስር ያለው መጠይቅ ሙሉ እና ከአማካሪዎቻችን መካከል አንድ ሰው በሚያጋጥማችሁ የትኛውም ነገር ውስጥ አብሯችሁ ለመጓዝ ደስተኛ ነው።
ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡
እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡
እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!