ሴትነቴን ሸጥኩት

የአስራ አምስት አመት ልጅ እያለሁ የማልመጥን መስሎ ይሰማኝ ነበር። በተደጋጋሚ ት/ቤት እቀራለሁ፣ አደገኛ እፅ እጠቀማለሁ እና እንደ አብዛኛው የአስራዎቹ እድሜ ልጅ እራሴን አልረዳም ነበር። ሃያ አንድ አመት ሲሆነኝ አገባሁ። ከባለቤቴ ጋር ወደ አዲስ ከተማ ሄደን መኖር ጀመርን እና በአንድ ምግብ ቤት ውስጥ በአስተናጋጅነት ተቀጠርኩ። ብዙም ሳልቆይ ከአሰሪዎቼ ጋር ስላልተስማማን ስራዬን አቆምኩ። በዚህ ጊዜ ነበር በጭፈራ ቤት የመደነስ ስራ ብዙ ገንዘብ እንደሚያስገኝ የሰማሁት። ስለዚህ በጭፈራ ቤቶች መደነስ ጀመርኩ። በመጀመሪያ በጣም ወደድኩት ምክንያቱም ጥሩ ገንዘብ ያስገኛል እናም የወንዶችን ትኩረት እንዳገኝ ያደርጋል። ይህንን ስራ እንደጀመርኩ ከባለቤቴ ጋር መስማማት አልቻልንም እና ፍቺ ፈፀምን።

ብዙም ሳይቆይ ስራውን ለመወጣት በየቀኑ መጠጣት ጀመርኩ። የሚያሳንስ እና ነፍስን የሚያደርቅ ስራ በመሆኑ በሆነ መንገድ መቋቋም ነበረብኝ። በፍጥነት የአልኮል ሱሰኛ ሆንኩኝ። በሂደት ግን በጭፈራ ቤት የተባለውን ያህል ገንዘብ እንደሌለ ተረዳሁ። ስለዚህ ወደ ቀጣዩ ደረጃ እንድሻገር አንድ ሰው አማከረኝ - ሴተኛ አዳሪነት። ነገር ግን ለእኔ የሴተኛ አዳሪነት ሀሳብ እንግዳ ነበር። እኔን እና ጓደኛዬን የሴተኛ አዳሪነት ስራ አስጀመረን። መጀመሪያ ለእኛ እንደ ጨዋታ ነበር፤ ልክ እንደ ቀለድ። ብዙ ገንዘብ ማግኘት፣ መስከር እና አደገኛ እፅ መጠቀም ጀመርን። አዝናኝ እንደሆነ ነበር ያሰብነው። ሁሉም ነገር በፍጥነት ተባባሰ።

በመጀመሪያው አመት የጭፈራ ቤት ስራዬ ወደ ሴተኛ አዳሪነት ገባሁ። ምን እየተፈጠረ እንዳለ አላስተዋልኩም ነበር። ሀላፊያችን “ገንዘብ ለማግኘት የግድ ከወንድ ጋር መተኛት አይጠበቅባችሁም” ብሎን ነበር። ነገር ግን እንደዛ አልነበረም። ገንዘብ ለማግኘት ከወንዶች ጋር እተኛ ነበር። ከጥቂት አመታት በኋላ ጓደኛዬ ስትወጣ እኔ ግን በዚያ ህይወት ተይዤ ነበር። ለአራት አመታት ሴተኛ አዳሪ ነበርኩኝ። ቀን በቀን ኑሮዬ በሆቴል ክፍሎች ሆነ። ገንዘብ ባገኝም ሁሉንም ገንዘቤን በውስጤ የሚሰማኝን ቆሻሻነት ፀጥ ለማሰኘት እፅ እና መጠጥ በመግዛት አባክነዋሁ። ነገር ግን ምንም ነገር ብገዛም ሆነ ምንም ያህል ገንዘብ ባገኝ የውስጤን ባዶነት ሊያስታግስልኝ አልቻለም። ስለዚህ ማድረጌን ቀጠልኩኝ፤ በቂ ገንዘብ ባገኝ በሚል ተስፋ፤ አንድ ቀን እረካለሁ በሚል ፍላጎት። ነገር ግን ያቀን ሊፈጠር አልቻለም።

እፅ ለማግኘት ወሲብ መፈፀም ጀመርኩኝ በቀጥታ ልዋጭ። በዛን ጊዜ ነበር ህይወቴ ከቁጥጥር ውጪ እንደሆነ የተረዳሁት።

ከጥቂት አመታት በኋላ አዲስ አሰሪ አገኘሁ። ሁልጊዜ ይመታኛል እና አንድ ጊዜ ወድቄ ጥርሴ እሰከሚነቀል ድረስ መታኝ። በጣም ሀይለኛ እና አስፈሪ ጊዜ ነበር። ከእርሱ ጋር ሁለት ወር ከቆየሁ በሃላ “ይህንን ከዚህ በኋላ ማድረግ የለብኝም” አልኩኝ። ትቼው ሄድኩኝ ግን በራሴ የሴተኛ አዳሪነት ስራውን ቀጠልኩኝ፤ ይህ ግን ከሚጠበቀው በላይ አደገኛ ነበር። ማን እንደሚጎዳችሁ የሚነግራችሁ ሰው የለም ወይም ከማን መራቅ እንዳለባችሁ የሚያስጠነቅቃችሁ ሰው የለም። በዚህ ጊዜ ነበር ወደ ከባድ እፆች የገባሁት። የማገኘውን ሁሉ እፅ እጠቀም ነበር። ከዛ እፅ ለማግኘት ወሲብ መፈፀም ጀመርኩኝ በቀጥታ ልዋጭ። በዛን ጊዜ ነበር ህይወቴ ከቁጥጥር ውጪ እንደሆነ የተረዳሁት። ከፖሊስ ጋር ሳይቀር ችግር ውስጥ ገባሁ በጣም ነበር ያስፈራኝ። ከዛም የኣኗኗር ዘይቤዬን ለመቀየር እና ከእፅ ለመራቅ የምኖርበትን ከተማ ቀየርኩኝ።

ከዛም ከሴተኛ አዳሪነት ይሻላል ብዬ አስቤ የጭፈራ ቤት ስራዬን እንደገና ጀመርኩኝ። ነገር ግን ለእፅ የነበረኝ ሱስ በጣም ጨመረ። ከዛም ነገሮች የበለጠ መጦዝ ጀመሩ። አንድ ቀን ስራ ቦታ እፅ ተጠቅሜ ጦዤ ነበር። በመልበሻ ክፍል ውስጥ ከቁጥጥር ውጪ ሆኜ አብረውኝ የሚሰሩ ሴቶች ይዘውኝ መርፌ በእጄ አስገብተው የሆነ ነገር ወጉኝ። እስከዛሬ ድረስ ምን እንደወጉኝ እና ለምን እንደወጉኝ አላውቅም። ለሳምንት በአዕምሮ ህሙማን ሆስፒታል ቆየሁኝ። የዛን ጊዜ ነበር እንደበቃኝ የወሰንኩት። በዚህ ጊዜ የምሬን ነበር። ከዛ በኋላ በህይወቴ ትልቅ ተፅዕኖ የፈጠሩ ሰዎችን ተዋወኩኝ። ወደ ቤተክርስቲያን ወሰዱኝ እና በማንነቴ ወደዱኝ። ወዲያው የእፅ ሱሴን ማቆም ቻልኩኝ እና ይህም ታላቅ ተአምር ነበር። ለአመታት በሱስ የሚማቅቁ ሰዎችን አውቃለሁ የእኔ ግን ከዚህ የተለየ ሆነብኝ። ሌላኛው ተአምር ስራ አገኘሁ። ለአራት አመት ስራ አልሰራሁም ነበር እና ማን ስራ ይሰጠኛል? ነገር ግን አንድ ቀን ታክሲ መጠበቂያ ቦታ ቁጭ ብዬ እያለ አንድ ሰው የስራ ጥሪ አቀረበልኝ። ከዛን ጊዜ ጀምሮ በአንድ የፒዛ መሸጫ እንደ አስተናጋጅ እሰራለሁ።

ባለፈው ህይወቴ በጣም እፍረት ይሰማኛል- የሚያሳፍር እና የሚያሸማቅቅ ነው። ስለዚህ ሴተኛ አዳሪ ብትሆኚም ብቻሽን እንዳልሆንሽ እወቂ። እኔም እንደዛ ነበርኩኝ። ሳይፈርዱብሽ የሚያዳምጡሽ፣ ያለቅድመ ሁኔታ የሚወዱሽ እና በመንገድሽ ከአጠገብሽ ለመራመድ ፍቃደኛ የሆኑ ኦንላይን አማካሪዎች አሉ። አድራሻሽን ብቻ ከስር አስቀምጪ እና አንድ ሰው ያገኝሻል።


ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡


እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡

የእርስዎ ፆታ:
የዕድሜ ክልል:

ተገቢውን አማካሪ እንዲመድብዎት የእርስዎ ፆታ እና ዕድሜ እንጠይቃለን። የአገልግሎት ውሎች & የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ.

እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!