ወሲባዊ ፊልም መድሀኒት አይደለም
እያገገምኩ ያለው የወሲብ ፊልም ሱሰኛ ነኝ። ለአመታት ነበርኩ። የዘጠነኛ ክፍል ተማሪ እያለሁ ነው የጀመርኩት፤ በጊዜው ያሰብኩት ለመዝናናት ብቻ እንደነበር ነው። ነገር ግን እንደ መድሀኒት ሆነ ወይም እንደዛ ነበር ያሰብኩት።
ወሲባዊ ፊልም መርዝ ነው። መፍትሄ ወይም የሚረዳ ነገር አይደለም። ራስን በወሲባዊ ፊልም ማከም በአደንዛዥ ዕፅ ራስን እንደማደንዘዝ ነው። በአብዛኛው የጉርምስና ጊዜዬ መገፋትን እና ብቸኝነትን ጠንቅቄ አውቃለሁ። ይሄን ህመም ነው ለማደንዘዝ ብዬ ነበር ወደ እዚ ሱስ ውስጥ የገባሁት። ለማምለጥ የምፈልገው ህመም ይሄ ነበር። ጉዳታችሁን ለመሸፈን ህመሙን ያስወገዳችሁ እየመሰላችሁ ብዙ አደንዛዥ ዕፅ ትጠቀማላችሁ፤ ግን በምትኩ ራሳችሁን በጣም ወደ ምትጎዱበት የጥፋት መንገድ እየተሽከረከራችሁ ታገኙታላችሁ። ብታምኑም ባታምኑም የእኔ ወደታች መሽከርከር የጀመረው በጣም ቪዲዮ ጌሞችን ሳበዛ ነው። አዎ በትክክል። የወሲብ ፊልም ሱሰኛ ከመሆኔ በፊት በቀን ረዥም ሰዓቴን ካለሁበት ብቸኝነት ለመውጣት እንዲረዳኝ በጥልቀት ወደ ቪዲዩ ጌም አለም እየገባሁ ነበር ማሳልፈው። ሳስበው ወደ ባሰው የወሲብ ፊልም ሱስ መግቢያ መንገዱን የከፈተ ሱስ ይመስለኛል።
ኮሌጅ ስገባ ቪድዮ ጌሞች ደባሪ ሆኑብኝ እና ብዙ ትርፍ ጊዜ ነበረኝ። እንደመዝናናት የቆጠርኩት የወሲብ ፊልም ወዲያው ልማድ ሆነብኝ፤ በየቀኑ የማደርገው፤ ከዛ መቼም ወደ ማይሞላ ጥልቅ ፍላጎት ተቀየረ። ራስን በስራ መያዝ በሚወድ ማህበረሰብ ውስጥ መሆን ወደ ጥፋት መንገድ ከመውረድ ያድናል። ልክ አልኮል እና አደንዛዥ ዕፅ ሰውን እንደሚቀይሩት የወሲብ ፊልም እንደሌላ መጥፎ ተግባር ነው። በእርግጥ የሚቀይረው ከውስጥ ወደ ውጭ ነው። ለረዥም ጊዜ ትክክለኛ ጤነኛው ራሴን አልነበርኩም። ሱስ ውስጥ ከመግባቴ በፊት ከነበረኝ ጥንካሬ ሰውነቴ ደክሟል እና አዕምሮዬ ዝግ ብሏል።
በሚያሳዝን ሁኔታ ጎጂ ዕፆች ለአጭር ጊዜ ደስታ ይሰጡናል ግን በረዥም ሂደት ይጎዱናል ፤ የሚያጠፋ ማንነታቸውን ሸፍነው - ልክ እንደ አዳኝ አውሬ በመጀመሪያ አድብቶ ታዳኙን እንደሚበላው።
የወሲብ ፊልም እና ሌሎች መጥፎ ተግባሮችን ጠላቸዋለሁ። ሌባ፣ ውሸታም እና የእግዚአብሔርን ፍጥረት ለማበላሸት ክፉ የሚጠቀምባቸው መሳሪያዎች ናቸው። ደስ በሚል ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ ከወሲብ ፊልም እስራት ነጻ እየወጣው ነው። አያችሁ ተስፋ አለ። ማየት ካቆምኩ ረዥም ጊዜ ሆነኝ። መላው ጤንነቴ ተሻሽሏል፤ ከሰው ጋር ያለኝ ግንኙነትን ጨምሮ። ይሄ ማለት መዛባት የለብኝም ማለት አይደለም። ፍጹም ከመሆን በጣም ሩቅ ነኝ። ግን ስወድቅ ከበፊት ይልቅ ጠንክሬ እነሳለሁ። የማይካድ የሚታይ መልካም ለውጦችን እያስተዋልኩ ነው።
ሙሉ ለሙሉ ለማገገም እና ከወሲብ ፊልም ነፃ ለመሆን ያለ ትግል ላይ ነኝ እናም ያለ ምንም ራስ ወዳድነት ያለውን ስጦታ ለዓለም የሚያካፍል እና የተሻለ ራሱን ሆኖ ለማቅረብ የሚታገል ሰው ነኝ። ግን ምንም ያህል ብታገል በራሴ ማሸነፍ አልችልም። ጠንካራ የሚረዱኝ የሚያወሩኝ ህብረቶች ስላሉ እንዲሁም በእግዚአብሄር ያለኝ እምነት በጣም ረድቶኛል። ብዙ ጊዜ ከወደኩበት አንስተውኛል እና እንድሄድ ረድተውኛል። እንድፈወስ ረድተውኛል እና እየረዱኝ ነው። እነዚህ እውነተኛ መድሀኒቶች ናቸው።
በወሲብ ፊልም ወይም በሌላ ነገር እየተቸገራችሁ ከሆነ እባካችሁን ብቻችሁን እንዳልሆናችሁ እወቁ። ከስር ያለውን መጠይቅ ሙሉ እና ልምድ ያለው አማካሪ ያናግራችኋል እና ወደ ነጻነት በምታደርጉት ጉዞ ላይ ይረዳችኋል።
ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡
እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡
እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!