በውርደቴ ውስጥ ብቻዬን

የጀመረው አንድ ምሽት “ሙድ ለመያዝ” ብለን ከሴት ጓደኞቼ ጋር ተሰብስበን የወሲብ ፊልም ያየን ጊዜ ነው። አስታውሳለሁ የዛን ቀን ከጓደኛዬ ቤት ከወጣሁ በኋላ ደግሜ ደጋግሜ እያሰብኩት ነበር። ስለዚህ ድህረ-ገፆችን እና ግልፅ የሆኑ ፎቶዎችን እና ቪድዮዎችን ለማየት መፈለግ ጀመርኩኝ እና እነዚህ አዕምሮዬ እንዳያርፍ አደረጉት። በጊዜው የወሲብ ፊልም ሳይ ይሰማኝ የነበረውን ስሜት ወደድኩት። ወሲብ አለማድረጌ ግን ጓደኞቼ የሚኖሩትን ወይም ይኖሩታል ብዬ ያሰብኩትን አለም ማየት ስለቻልኩ ወድጄዋለሁ። ሁሌም የወሲብ ፊልምን የማየት ፍላጎት ነበረኝ። የተወጣጠረ ሰዓት ያለኝ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ነበርኩ፥ ውጤቶቼን በደንብ የምከታተል ነኝ እና አመቱን ሙሉ ስፖርት ቡድን ውስጥ ነበርኩ። ስለዚህ ብዙ ትርፍ ጊዜ አልነበረኝም ግን ለወሲብ ፊልም ጊዜ አዘጋጅ ነበር።

ማታ ላይ ኮቴዬ ሳይሰማ ወደ እታች ከፍል መሄድ ወይም ወላጆቼ ከመምጣታቸው በፊት ኦንላይን ገብቼ መጠቀም ላይ ተካንኩበት።

ላፕቶፕ አልነበረኝም ግን እታች ክፍል ወላጆቼ ኮምፒውተር ነበራቸው። ብቻዬን አምስት ደቂቃ ማግኘት እንደምችል ባወኩ ቁጥር ራሴን እታች ክፍል ስሄድ አገኘዋለሁ። ማታ ላይ ኮቴዬ ሳይሰማ ወደ እታች ከፍል መሄድ ወይም ወላጆቼ ከመምጣታቸው በፊት ኦንላይን ገብቼ መጠቀም ላይ ተካንኩበት። ሱሴ ለሁለት አመት አብሮኝ ቆየ። እስከዛሬ የምሰማው የወሲብ ፊልም የወንዶች ችግር እንደሆነ ብቻ ነበር። በዚህ የሚቸገሩ ሴቶች ይኖሩ ይሆን? እኔ ብቻ ነኝ? ምንድን ነው ችግሬ? በጣም አፀያፊ ነኝ ብዬ አስብ ነበር።

በሱስ ስትያዙ፤ አዕምሯችሁ በውሸቶች ይሞላል። ጓደኞችሽ ወሲብ እየፈፀሙ ነው እና አንቺ ግን አይደለሽም - ስለዚህ ማየትሽን ቀጥዪ። አታስቢ አሁንም ድንግል ነሽ። ከዛም አልፎ ለማወቅ ብቻ ነው። አንድ ቀን ባልሽ በጣም እድለኛ ይሆናል ስለ ወሲብ በደንብ በማወቅሽ።

ውሸቶች፣ ውሸቶች እና ብዙ ውሸቶች። እና ውሸቶች ባሉበት እፍረትም ይኖራል።

በጊዜው የወሲብ ፊልም ማየት በጣም ደስ የሚል ስሜት ነበረው። ግን እንዳለቀ፣ በፀፀት እሞላለሁ፣ በራሴ እናደዳለሁ። ድርጊቴን እፀየፈዋለሁ። ስለዚህ ከመጀመሬ በፊት ለማቆም እንዲረዱኝ መንገዴን የሚዘጉ ነገሮችን አዘጋጃለሁ። ልክ እንደ ኮምፒውተሩን እስከ ወዲያኛው ማጥፋት (የድሮ ኮምፒውተሮች ከመክፈት 10 ደቂቃ ያህል ይፈጅባቸው ነበር) ወይም “በሚስጥራዊ ፅሁፍ” ማስታወሻ እጽፍ ነበር። ግን ምንም አልጠቀመኝም። ሁሌ ከሆነ በኋላ ራሴን በንዴት ተሞልቼ እና ተፀፅቼ አገኘዋለሁ። በድጋሜ በራሴ አፍራለሁ እና የተገፋሁ ስሜት ይሰማኛል።

በወሲብ ፊልም የተቸገረች አንድ የማውቃት ሴት የለችም። ወንዶችን ግን አውቃለሁ። ግን ሴቶችስ? በግል ባውቅ፣ ወይም የማላቃት አንድ ሴት ተቸግራለች ተብዬ ብሰማ ብዬ እመኛለሁ። ግን ለሙሉው ሁለት አመት በሚያጠፋው ሱስ ተጠምጄ ነበር። ግራ የሚያጋባ ነበር።

አንድ ምሽት ከዚህ በኋላ እንደዚህ መኖር የለብኝም ብዬ ወሰንኩ። በአንድ ምሽት አልተቀየርኩም እና በእርግጥም ቀላል አልነበረም። የመጀመሪያዎቹ ጥቂት ወራት ስቃይ ነበሩ - እያንዳንዱ ነገር ኮምፒውተሩ ወዳለበት ክፍል ሄጄ የምፈልገው ስሜት እንዳገኝ የሚያነሳሱ ነበሩ። በተከታታይ ለወራት ክፍት ቁስል እንዳለኝ ነበር የሚሰማኝ። ግን ከዛ በሚገርም ሁኔታ ቁስሉ መዳን ጀመረ። አሁንም በወሲብ ፊልም ውጤቶች ጋር ነው የምኖረው። በባል እና ሚስት መካከል ያለው የወሲብ እና ፍቅር እይታዬ ተበላሽቷል። ግን እየተማርኩ ያለሁት የወሲብ ፊልም እውነት አልነበረም እና አይደለም - የቁም ቅዠት ነው። እና ወሲብን ካስቀመጥኩበት ትልቅ መደብ እያወረድድኩት ነው።

በወሲብ ፊልም የምትቸገሩ ከሆነ፤ ብቻችሁን እንዳልሆናችሁ እወቁ። እና ስለምታልፉበት ነገር የምታወሩት ሰው ቢኖር በእውነት ይረዳል። ዛሬውን ከታች ያለው መጠይቅ ይሙሉ ነፃ እና ሚስጥር ጠባቂ የሆኑትን አማካሪዎቻችን ጋር ለመገናኘት። እውነተኛ ስሞት ወይም ሌላ ስም መጠቀም ይችላሉ፡ የእናንተ ምርጫ ነው።


ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡


እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡

የእርስዎ ፆታ:
የዕድሜ ክልል:

ተገቢውን አማካሪ እንዲመድብዎት የእርስዎ ፆታ እና ዕድሜ እንጠይቃለን። የአገልግሎት ውሎች & የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ.

እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!