መገፋት እና መተካት

ከአስር ዓመት በላይ በጋብቻ የቆየሁት ባለቤቴ እኔ ምንም ሳላውቅ የፖርኖግርፊ ሱሰኛ ሆኖ አገኘሁት፡፡ የኮምፒውተር ባለሙያ በመሆኑ የፖርኖግራፊ መረጃዎቹን በሙሉ በአጋጣሚ እንኳን እንዳላገኛቸው በአግባቡ ይደብቃቸዋል፡፡ ሰለዚህ ይህ ችግር እንዳለበት የምጠረጥርበት ምንም ምክንያት አልነበረኝም፡፡

በእርግጥ አንዳንድ የወሲባዊ ግኑኝነት ቅርበት ችግሮች በመካከላችን እንዳሉ ተረድቻሁ፡፡ ወሲብ ቀስቃሽ ንክኪዎችንም ሆነ ወሲብ ሳይፈልግ እና ሳያስፈልገው በጣም ለረዥም ጊዜ መቆየት ይችላል፡፡ ለምንድነው ብዬ ስጠይቀው ፍላጎት እንደሌለው ወይም ደግሞ በሆነ መንገድ እኔ የሚያስወቅስ ምክንያት ፈልጎ ምክንያት ይደረድርልኛል፡፡

አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በውይይታችን መሀል ምንም እንደማያውቅ ወደ ሌላ ሃሳብ ይገባል ለብቻው ያስብና ደግሞ ይበሳጫል፡፡ የሆነ ነገሩ የአልኮል እና የአደንዛዥ እፅ ሱሰኛ እንደሆኑት ጓደኞቼ ያደርገዋል፡፡ ሱስ እንዳለበት ባስብም የምን እንደሆነ ግን ምንም መረጃ ማግኘት አልቻልኩም ነበር፡፡ በዛን ጊዜ አንድ ሰው የፖርኖግራፊ ሱሰኛ መሆን እንደሚችል አላውቅም ነበር፡፡

በጣም የሚደንቀው ነገር የቀድሞው ባለቤቴ የፀረ-ፖርኖግራፊን ተሟጋች ነበር፡፡ አንድ ጓደኛችን ባለቤቴን ፖርኖግራፊ እንደሚያይ ሲጠይቀው አስታውሳለሁ፡፡ በቁጣ ነበር የመለሰለት ‹‹ያንን ነገር እየተመለከትኩ የሚስቴን እና የሴት ልጆቼን ክብር አልነካም›› ነበረ ያለው፤ እኔም አመንኩት፡፡

ስለዚህ የወሲብ ስሜት ቀስቃሽ የሆኑ ምስሎችን እንደሚጠቀም የነገረኝ ቀን እንደተካድኩ ተሰማኝ፡፡ የመሰለኝ በሆነ የኢንተርኔት አለም ውስጥ የማገጠብኝ ሳይሆን የሚኖረው ሁሉ ውሸት፣ ያልሆነውን ሆኖ የማስመሰል ህይወት የሚኖር መስሎ ተሰማኝ፡፡ ይህ በጣም አሰፈሪ ነው፡፡ እንደ እውነተኛ እና ወሲብን በሚመለከት ታመኝ ባል እንደሆነ አድርጎ ነበር እራሱን የሚያቀርበው፡፡ ነገር ግን እውነታው ከዚህ የራቀ ነበር፡፡

እውነተኛ ባህሪው በአንድ ቀን አልነበርም የተገለጠው፡፡ ቀስ በቀስ ነበር የወጣው፡፡ አንድ ቀን አንድ ነገር ያምንልኛል፤ ለምሳሌ፡- ምስሎቹን እንደሚያይ አመነልኝ ከዛ ያንን በሚመለከት ተነጋግርን መፈታት እንደምንችል ሳስብ ደግሞ ሌላ ከእርሱ በጣም የባሰ ነገር እንደሚያደርግ ያምናል፡፡ እርሱንም ስተው ከእርሱም የባሰ፤ ይህ ሁሌም የሚከሰት ነው፡፡

እርሱ መተው ባልቻለው እኔም ለአመታት ለመልመድ ባልቻልኩት ባህሪው በጣም እየደነገጥኩኝ እና እየፈራሁ መጣሁ፡፡ ፖርኖግራፊ እንደሚያይ ካወኩኝ በኃላ በእኔ አካል ላይ የሆነ የተበላሸ ነገር እንዳለ ነበረ ያሰብኩት፡፡ እኔ ጋር ያጣውን ወይም የጎደለውን ነገር ለመሙላት የሚሄድ መሰለኝ፡፡ በእርግጥ ትክክል ነኝ በሁሉም ነገር ሙሉ አይደለሁም፡፡ ለእርሱ ስለማልመጥነው ይሁን? ቆንጆ ስላልሆንኩኝ ይሁን? አማላይ ስላልሆንኩኝ ይሁን? ወይም እንደሴት ሰለማልማርከው ይሁን? በተመሳሳይ ሰዓት ደግሞ በጣም የተሻልኩ እንደሆንኩኝ ይሰማኛል፡፡ በጣም እውነተኛ፣ በጣም ሰበዓዊ እና ከእርሱ የተለየ ሰሜት እና ፍላጎት ያለኝ ሰው ሰለሆንኩኝ ይመስለኛል፡፡ እንዲሁም በጣም ሰው የምፈልግ፣ በጣም ስስ፣ በጣም የምሳሳት ሰው ነኝ፡፡ ትልቅ ሀፍረት፣ መናቅ እና ብቸኝነት ተሰማኝ ፡፡

ይህ ብቻ አይደለም ምንም ዋጋ እንደሌለኝ ተሰማኝ፡፡ እኔ የተለየሁ እንደሆኩኝ፣ በምንም የማልተካ እንደሆንኩኝ እና ተፈላጊ እንደሆንኩኝ እንዲሰማኝ የሚያደርገኝ አንድ ሰው የወሲብ ፍላጎቱን ሀይል በእስክሪን ላይ ባለ አንድ ቻናል በማድረግ የሚያየው ምስል ከእኔ በልጦበታል፡፡ ሰው እንዳልሆንኩኝ ተሰማኝ፤ ሰበዓዊ ፍጡር እንዳልሆንኩኝ እና በቀላሉ በምስል ወይም በምናብ ውስጥ ባለች ሴት እንደተተካሁ ተሰማኝ፡፡

እውነቱን ስነግራችሁ በጣም አስቀያሚ እንደሆንኩኝ ተሰማኝ እውነተኛ እና እጅግ አሰቀያሚነት፡፡ ላሟላው የማልችለውን የውበት መስፈርት እንዳሟላ የተጠየኩኝ መሰለኝ ስለዚህ ሁሉንም ነገር አቆምኩኝ፡፡ ሀፍረት ተከናንቤ ተደበኩኝ፡፡

እኔ የተለየሁ እንደሆኩኝ፣ በምንም የማልተካ እንደሆንኩኝ እና ተፈላጊ እንደሆንኩኝ እንዲሰማኝ የሚያደርገኝ አንድ ሰው የወሲብ ፍላጎቱን ሀይል በእስክሪን ላይ ባለ አንድ ቻናል በማድረግ የሚያየው ምስል ከእኔ በልጦበታል፡፡

የቀድሞው ባለቤቴ ወሲብ በጣም የምፈልግ እንደሆንኩኝ ነው የሚያስበው፤ እንደዛ ሰለሆንኩኝ አይደለም ነገር ግን እርሱ የእኔን ጤናማ ፍላጎት ማሟላት የማይችል በመሆኑ ነው፡፡ እኔ የማልፈለግ አይደለሁም፡፡ እርሱ እራሱን እውነት ባልሆነ ስጋዊ መሻቱ መርካትን ሰላስለመደ ነው፡፡ እና ምንም አይነት እውነተኛ ሰው ከምናብ አለም ካለ እውነተኛ ካልሆነ ነገር ጋር መወዳደር የለበትም፡፡ ሲኤስ ሉዊስ እንዳለው ‹ውሽማ ሁሌም የምትገኝ ናት ሁሌም የበታች ናት፡፡ ምንም መሰዋዕትነትን የማትከፈል እና ወሲባዊ ወይም ሳይኮሎጂያዊ አማላይነት የተላበሰች ስትሆን የትኛዋም ሴት ከእርሷ ጋር ልትወዳደር አይገባም፡፡ ከእነዚያ ከተደበቁ ሁሌ ከሚማረክባቸው፣ ሁሌ ንፁህ የሆነ ፍቅር ከሚሰጣቸው፣ ሁሉም ነገር በእርሱ ራስ ውዳድነት ላይ ሳይመሰርት ከሚደረግላቸው፣ ምንም አይነት ሀፍረት በእርሱ ኩራት ላይ ሳይጫን ከሚሰጣቸው ውብ እንደሆኑት ሙሽሮች›፡፡

እንደእድል ሆኖ ባለቤቴ ብቻ አልነበረም የሀፈረት ሰሜት እንዲሰማኝ የሚያደርገኝ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ለሱ ሱሰኝነት እኔም ተጠያቂ እንደሆንኩኝ እንዲሰማኝ የሚያደርጉኝ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ እኔ ለወሲብ ፈቃደኛ ባለመሆኔ የሄደው መንገድ ነው ብለው በማሰባቸው፡፡ ነገር ግን ከእኔ ጋር ወሲብ የማይፈልገው ባለቤቴ እራሱ መሆኑን አልተረዱም፡፡ አንዳንዶች ደግሞ በጣም እንድቆጣጠረው ይነግሩኛል በጣም ቀዝቃዛ እና በጣም እንዳላፈቀርኩት በመግለፅ በጣም አማላይ እንዳልሆንኩ ወይም ለእርሱ እንደሚያስፈልገው እንደማልገዛ ይነግሩኛል፡፡ በድጋሚ በጣም የተሻልኩኝ እንደሆንኩኝ በዛው ቅፅበት ደግሞ ለእርሱ በቂ እንዳልሆንኩኝ ይሰማኛል፡፡

በዚህ ሁሉ ግን አስደናቂው እውነታ እኔ ደህና መሆኔ ነው፡፡ ችግር የነበረብኝ እኔ አልነበርኩም፡፡ እርሱ ለመረጠው ነገር እኔ ተጠያቂ አይደለሁም፡፡ እኔ ፍፁም አይደለሁም እንዲሁም ለማንም የማልመጥን አይደለሁም፡፡ በትክክል መሆን ያለብኝን አይነት ሰው ነኝ ልክ እግዚአብሔር እንድሆን ፈልጎ የፈጠረኝ አይነት ሰው ነኝ፡፡ እንዲሁም ሰው በመሆን የሚገኝ ሁሉም አይነት ምኞት እና ፍላጎት ያለኝ ሰው ነኝ፡፡

የትዳር ጓደኛዎ የፖርኖግራፊ ምስሎችን ሱስ ካለበት ፣ እርስዎ ብቻዎን እንዳልሆኑ ይወቁ ፡፡ በዚህ መንገድ ከእርስዎ ጋር መጓዝ እንወዳለን ፡፡ ከዚህ በታች መረጃዎን ብቻ ይሙሉ ፣ እናም በአማካሪ ቡድናችን ላይ ያለ አንድ ሰው በቅርቡ ይፅፍሎታል። የእኛ የማማከር አገልግሎት ሚስጥራዊ እና ሁል ጊዜም ነፃ ነው።


ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡


እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡

የእርስዎ ፆታ:
የዕድሜ ክልል:

ተገቢውን አማካሪ እንዲመድብዎት የእርስዎ ፆታ እና ዕድሜ እንጠይቃለን። የአገልግሎት ውሎች & የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ.

እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!