የማይወራላቸው ጀግኖች

የቤተሰቡ የመጨረሻ ልጅ ነኝ። ያ የምታውቁት የመጨረሻ ልጅ ስስት እና እንክብካቤ ያለልክ ሲፈስብኝ ነው ያደኩት። የእኔን ለየት የሚያደረገው የመጨረሻ ልጅ መሆኔ ብቻ ሳይሆን ለሶስት ወንድሞቼም ብቸኛ እህታቸው መሆኔ ነው። ለአባቴና ለእናቴ ደግሞ የእኔ ትርጉም ምን እንደሆነ የሚያውቅ ያውቀዋል። የቤተሰቡ ማድመቂያ የስለት ፍፃሜ እንደሆንኩኝ እየተነገረኝ ነው ያደኩት። ፈጣሪም አንዳች አላጎደለብኝም የወንድሞቼን ትምህርት ጠልነት መበቀያም ነበርኩኝ። በጣም ትምህርት የምወድ ጎበዝ ተማሪ ነኝ። ወደ ኮሌጅ እስከምገባ ሳልሽለም ቀርቼ አላውቅም። ታዲያ ቤተሰቦቼ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ነው የሚያወድሱኝ።

ባለቤቴን ያገኘሁት ህክምና የመጀመሪያ አመት ተማሪ ሆኜ ነው። እሱ ከእኔ አንድ አመት የሚቀድም የህክምና ተማሪ ነበር። በጣም ተዋደን ከአንድም ሁለት ሶስት ጊዜ ቤስት ካፕል አዋርድ አሸንፈን ነው እኔ ስመረቅ የተጋባነው። አቤት የጊቢ ፍቅር ግን እንዴት ነው ደስ የሚለው? ስንጋባ እኔ ጥሩ የሚባል ስራ ነበረኝ። ምን እንኳን እሱ ከእኔ በፊት ተመርቆ ስራ የነበረው ቢሆንም እሱ የሚሰራው ሆስፒታል ውስጥ በመሆኑ እኔ ከእሱ የተሻለ ገቢ ነበረኝ። እኔ ስመረቅ ከፍተኛ ውጤት ስለነበረኝ በቀጥታ አንድ አለም አቀፍ ድርጅት ውስጥ ነው ስራ ያገኘሁት። በገንዘብ ደረጃ ከባለቤቴ የተሻለውን ገቢ የማገኘው እኔ ብሆንም አንድም ቀን ይህ አናንቆን አያውቅም። ቤታችን ትንሽዬ ነገር ግን በደስታ የተሞላች ነበረች። ሁለታችንም ኑሯችንን ለመለወጥ ተግተን ስለምንሰራ እና ሰላማዊ ቤተሰብን ስለምንመራ በረከታችን ከሰራነው በላይ ነበር። እኔም የሚረዳኝ እና ያን ከመሰለ የተንደላቀቀ የቤተሰቤ ቤት አውጥቶ የሚያሞላቅቀኝ በማግኘቴ ፈጣሪ የተለየ እንደሚወደኝ ይሰማኝ ነበር።

የተወሰኑ አመታትን በጣፋጭ ትዳር ከዘለቅን በኋላ ልጅ ለመውለድ አሰብን። ልጅ ለመውለድ ስናስብ ግን እንደ ማንኛውም ቤተሰብ ወልደን ለሰራተኛ ጥለን የምንወጣውን ልጅ መውለድ አልፈለኩም። ስለዚህ ቁጭ ብለን አወራን። እኔ ስራ አቁሜ ልጆቼን ማሳደግ እንደምፈለግ ነገር ግን የኑሮው ጫና በእሱ ላይ ብቻ ስለሚሆን እንዳይከብደን እንደምፈራ ነገርኩት። በዛ ላይም የምወደውን ስራዬን ማቆሜ ወደፊት እንዳይቆጨኝ እንደምፈራ አጫወትኩት። አወጣን አወረድን ከዛም እኔ ስራ ላቆም እና ልጆች ላሳድግ እሱ ደግሞ እኔ ስራ በማቆሜ የሚፈጠረውን የገንዘብ ጫና ለመወጣት ተጨማሪ ስራዎችን እንዲስራ ተስማማን። ከዛም የመጀመሪያ ልጄን አረገዝኩ።

በእርግዝናዬ ወቅት ስራዬን አላቆምኩም። ስወልድ ግን ስራዬን እንደማቆም ለቤተሰቦቼ ሳሳውቅ በጣም አዘኑ። እናቴ ምን አይነት አለማወቅ እንደሆነ በልመና ሁሉ ነገረችኝ። ጓደኞቼም ኋላ ቀር አስተሳሰብ እንደያዝኩኝ እና ወደ ፊት እንደሚቆጨኝ ነገሩኝ። እኔ ልቤ ፈራ ተባ ቢልም ልጆች ማለት ከፈጣሪ በታች ሆኜ መንገድ የማሳያቸው እኔ ስለሆንኩኝ ይህንን ዋጋ መክፈል ለዘላቂ ህይወታቸው ወሳኝ መሆኑን በማመን ልቤ እንዳይከፈል እራሴን አበረታሁ። በእርግጥ ስራ አልነበረም። እንደነገርኳችሁ ቤተሰቦቼ ለእኔ የተለየ ትኩረት ስለነበራቸው ነው እኔም ከወንድሞቼ የተለየሁ የነበርኩት የሚል አመለካከት ስለነበረኝ እኔም ልጆቼን የተለዩ አድርጌ ማሳደግ ህልሜ ሆነ። ገና ማረገዜን ስሰማ ነው ልጅ የማሳደግ ዝግጅት የጀመርኩት።

በዚህ ውሳኔዬ ባለቤቴ በጣም ደስተኛ ነበር። እንደዘመኑ ሴቶች ከአከዳሚክ አቺቭመንቴ የቤተሰቤን አቺቭመንት በማስበለጤ አደነቀኝ። እውነት ለማውራት ትምህርቴን እና ስራዬን በዚህ መልኩ ማቆሜ አንዳንዴ እኔንም ያስደነግጠኛል። አንድ ቀን እናቴ ልትጠይቀኝ መጥታ “እኔ ምልሽ ገና ለገና ባሌ ያኖረኛል ብለሽ ነው የት ትደርሳለች እያልን ዋጋ የከፈልንበትን ትምህርትሽ የሰጠሽን ይህንን ስራ የምታቆሚው? ባል እኮ ባዳ ነው። አንድ ነገር የተፈጠረ ቀን አልመከረችኝም እንዳትይ” አለችኝ። ሀሳቡ ቢያስደነግጠኝም እኔ እና ባሌ ግን የተለየን እንደሆንን አስቤ ተውኩት።

ገና ከጅምሩ ልጆቼን በእውቀት ማሳደግ እንዳለብኝ በማመን ስለልጆች አስተዳደግ የተፃፉ መፃፍትን፣ የእናቶች ፕሮግራሞችን፣ የልጆች አመጋገብ እና ምግብ አስራሮችን ሁሉ ሳነብ እውላለሁ። አይደክመኝም። እንደውም የበለጠ ለማወቅ እጓጓለሁ። እኔም ገና ከልጅነታቸው ጀምሮ ልጆቼን እራሴ ላሳድጋቸው በመሆኑ በጣም ደስ አለኝ። የሚገርማችሁ ከመውለዴ በፊት ጀምሮ አጋዥ ስለነበረችን አንድም ቀን ምግብ አብስዬ አላውቅም ነበር። ነገር ግን እንዳረገዝኩኝ ሳውቅ ለልጆቼማ እራሴ ነኝ የማበስለው ብዬ የምግብ ሙያን ሀ ብዬ ተማርኩኝ። ልጄን ለመቀበል ሁሉንም አይነት ዝግጅት አድርጌ በደስታ ታቀፍኳት። ደስታችን ወደር አልነበረውም። የሚያውቀን ሁሉ ተደሰተ። ስጦታው ደስታው ወደ ቤታችን ጎረፈ። በረከታችን ተትረፈረፍ።

ከዛም የአራስ ቤት ግርግር አበቃ እና ኑሮ ተጀመረ። ከልጄ ጋር ስደሰት ውዬ ስደሰት አመሻለሁ። ማታም ባለቤቴ ከስራ በጉጉት ይመጣል በቃ ልጃችንን እየተቀባበለን እየሳቅን እንተኛለን። እኔም ኑሮውን ለመድኩት በቃ ምርጥ እናት ሆንኩኝ። የምታግዘኝ ልጅ ብትኖርም እኔ ልጄ ከብዳኝ አታውቅም። በቃ ስስት እንዳልኩኝ ይነጋል ይመሻል። ከዛ ሁለተኛ ልጅ ከዛ ሶስተኛም መጣ። አሁን ውሎዬም ትንሽ ጠጠር እያለ መጣ።

አሁን ላይ እራሴን ዞር ብዬ ስመለከት ምንም ጓደኛ የሌለኝ፣ ቤተሰቦቼንም ልጆቼን ልጆቼን ስል ያራኩኝ ብቸኛ እንደሆንኩኝ ይሰማኛል።

አሁን ላይ እራሴን ዞር ብዬ ስመለከት ምንም ጓደኛ የሌለኝ፣ ቤተሰቦቼንም ልጆቼን ልጆቼን ስል ያራኩኝ ብቸኛ እንደሆንኩኝ ይሰማኛል። ባሌም የተሻለ ገንዘብ በመስራት ሰበብ ቤት የሚውልበት ጊዜ የለውም። እኔ ልጆቼ ተቀራራቢ እድሜ ላይ ስላሉ እነሱን ትቼ መውጣት አልችልም። ባሌም አምሽቶ ደክሞ ስለሚመጣ በመካከላችን ክፍተቶች በዝተው ጭቅጭቅ ሁሉ ጀምረናል። እሱም የእኔ ጭቅጭቅ ስለሚያስጠላው ስራው ከሚጠይቀው በላይ እያመሽ ስለሚመጣ በትዳሬ ተስፋ ቆርጫለሁ።

ልጅ ማሳደግ እንደዚህ ይከብደኛል ብዬ አስቤ አላውቅም። እራሴን እስካጣ ድረስ ከበደኝ። ያነበብኳቸት መፅሀፍ እስከአሁን ያሳደኳቸው ህይወት ሁሉ ጠፋብኝ። አንዳንዴ ስራዬን ትቼ ልጆቼን ማሳደጌ ልክ እንዳልነበር ሁሉ አስባለሁ። የእኔ ጓደኞች ትምህርት ቤት ስንማር አስጠናቸው የነበሩ ሁሉ አሁን በደረጃም በማዕረግም ከእኔ የተሻሉ ሆነዋል። በቃ አላውቅም የሆነ ነገር ደስታዬን ከህይወቴ ነጥቆኛል። በተለይማ አንዳንድ ቀን አለ ሶስቱም እኩል ማልቀስ ይጀምራሉ። ታዲያ የዛኔ ጥፊ ጥፊ ነው የሚለኝ። የገዛ ልጆቼን እንኳን ማስደስት የማልችል ጥቅም የሌለኝ እንደሆንኩኝ ይሰማኛል።

አንድ ቀን ማታ ባለቤቴ ከስራ ሲመጣ ጠብቄ ስራ መጀመር እንዳሰብኩኝ ነገርኩት። እሱ በቅጡም አያናግረኝም። ጉዳዩ ወደ ጭቅጭቅ ከማምራቱ በፊት ብሎ መሰለኝ አልተቃወመኝም። የስራ ልምዴን እና ማስረጃዎቼን አሰባሰብኩኝ ሳያቸው ስምንት አመት የት ነበርሽ ይሉኛል። ያቺ የት ትደርሳለች የተባለችው ጎበዝ ተማሪ፣ ያቺ ማንም የማይከፈለው ደሞዝ ይከፈላት የነበረች ትጉ ሰራተኛ ዛሬ ተራ የቤት እመቤት እንደሆነች እና ጥሩ የቤት እመቤት እንኳን መሆነ እንዳቃታት ታወቀኝ። በህይወቴ እርካታ አጣሁ። ስራዬን ያቆምኩበትን እለት ረገምኩት። ስንት እናት አለ አይደል እንዴ ስራውን እየሰራ አራት አምስት የወለደ ብዬ እራሴን ወቀስኩኝ። ይህንን የትምህርት ማስረጃ ይዤ ማንም አይቀጥረኝም ብዬ ተስፋ ቆረጥኩ። ደስተኛ ሚስት እና እናት የነበርኩት ሚስትም እናትም መሆን አቃተኝ። የእናቴ እና የጓደኞቼን ምክር ችላ ማለቴ ዋጋ እንዳስከፈለኝ ተሰማኝ።

ከባለቤቴም ጋር ተነጋግረን መስማማት እያቃተን መጣ። በልጆቼ ደስተኛ ብሆንም እነዛ ስራቸውን ሳያቆሙ ልጆቻቸውን ባሳደጉ እናቶች መቅናት ጀመርኩኝ። አሁን ወጥቼ ስራ ልስራ ብል ማን ይፈልገኛል የሚል ስሜት የማልፈለግ እንደሆንኩኝ እንዲሰማኝ ያደርገኝ እና ተስፋ እቆርጣለሁ። ባለቤቴም ለእኔ የማያስብ ራስ ወዳድ እንደሆነ ይሰማኛል። ለሱ ብዬ ሁሉን ጥዬ የእሱን ልጆች ለማሳደግ በከፍልኩት ዋጋ ምክንያት በእሱም የተናቅኩኝ እንደሆንኩኝ ይሰማኝ እና ምን አይነት ሰው ነው ያገባሁት ብዬ በውሳኔዬ እፀፀታለሁ። ሁሉንም ነገር ጥዬ ለመሄድ አስብና ደግሞ ወደ ልቤ እመለሳለሁ። ያን ከመሰለ የተንደላቀቀ ህይወት ውሳኔዎቼ ቁልቁል የፈጠፈጡኝ ያህል ይሰማኛል። ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም። አንዱ ልቤ ልጆችሽን ለሚያግዙሽ ትተሽ ወጥተሽ ትምህርትሽን ቀጥለሽ ተማሪ እና ስራ ፈልገሽ ተፈላጊነትሽን አረጋግጪ ይለኛል። ሌላኛው ልቤ ደግሞ ከህፃናት ልጆችሽ የሚበልጥብሽ የለም አንቺ ወጥተሽ ሰርተሽ የምታመጪው ገንዘብ የተለየ የሚፈጥርልሽ ነገር የለም አርፈሽ ልጆችሽን አሳድጊ ይለኛል። እኔ ግን ለወተት እና ለዳይፐር እንኳን ሳይቀር የባለቤቴን እጅ መጠበቅ ሰልችቶኛል።


ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡


እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡

የእርስዎ ፆታ:
የዕድሜ ክልል:

ተገቢውን አማካሪ እንዲመድብዎት የእርስዎ ፆታ እና ዕድሜ እንጠይቃለን። የአገልግሎት ውሎች & የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ.

እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!