የሆነ ችግር አለብኝ እንዴ?

የእርግዝና ምርመራ ውጤቴ ነፍሰጡር መሆኔን ሲያረጋግጥ በደስታ ፈነደቅን። ሁሉም ነገር አስደሳች ነበር። ሆዴ ገፍቶ በማህፀኔ ውስጥ እያደገ ያለውን ትንሽ ልጅ ማሳየት ባይችልም የፈካው ፊቴ እና ደስተኛው ልቤ ግን እያሳበቁብኝ ነበር። ሁሉም ነገር ሙሉ እንደሆነ ተሰማኝ ፤ በተስፋ እና በደስታ ልቤ ተሞላ።

ነገር ግን ነገሮች በቅፅበት መቀየር ጀመሩ። እንደተለመደው ወደ መታጠቢያ ክፍል ሄድኩኝ ከዛ ትንሽ ጠብታ ደም አየሁ፡፡ በተደጋጋሚ አልትራሳወንድ ተነሳሁ ነገር ግን የልብ ምቱ ሊገኝ አልቻለም። ትንሽ እጅ እና እግር እያሰብኩ የነካሁት እየመሰለኝ ሆዴን በማሻሽበት ጊዜ ግራ መጋባት ወረሰኝ። ልባችን ተሰበረ። ትንሽ ልጅ በመጠበቅ ፋንታ በጥርጣሬ እና በባዶነት ልባችን ተሞላ።

ይመጣል ብዬ ተስፋ ያደረኩት እና የፀለይኩት ይህ ትንሽ ልጅ በማህፀኔ ውስጥ እያደገ እንዳልሆነ በምርመራ ተረጋገጠ። ልጄ በሆዴ ውስጥ ሞቷል። ቀጥሎ የተፈጠረው ነገር ይፈጠራል ብዬ ከፈራሁት ሁሉ የባሰ ነው። የሞተውን ልጄን በማማጥ፣ በዚያ አስቸጋሪ መንገድ በማለፍ መውለድ ነበረብኝ። ሃዘኔ ስሜት አልባ በሆኑ ባለሙያዎች ምክር የሚታገስ አልነበረም። "አታልቅሺ፣ ምንም ማለት አይደለም" የሚሉኝ ድምፃቸው ያስጠላኛል። ቤተሰቦቼ እና ጓደኞቼ የሚሰጡት "ጠንካራ ሁኚ"፣ "ደህና ነሽ"፣ "በቃ ተይው"፣ "በድጋሚ መሞከር ትችያለሽ"፣ "ልጅ እኮ አልነበረም" የሚሉ አስተያየቶች ምንም አይዋጡልኝም ነበር።

እንደሴትም ሆነ እንደእናት ምንም ጥቅም እንደሌለኝ ተሰማኝ፡፡

ሰዎች በአሽሙር የተናገሩኝ ይመስለኛል። ይህ ደግሞ ችግሬን አባባሰው። አዕምሮዬ በጥያቄ ይሞላል፤ የሆነ ችግር ይኖርብኝ ይሁን? መቼም መውለድ ባልችልስ?

ልጄን ማጣቴ ብቻ ሳይሆን ሀዘን ውስጥ የከተተኝ ከዚህ በኃላስ መውለድ ባልችልስ የሚለው ሀሳብ ቅስሜን ሰበረው። እንደሴትም ሆነ እንደእናት ምንም ጥቅም እንደሌለኝ ተሰማኝ። ሌሎችም ሰዎችም እንደዚህ እንደሚመለከቱኝ እርግጠኛ ሆንኩኝ። ልጄን በማጣቴ የደረሰብኝ የመንፈስ ስብራት በህይወቴ ከገጠሙኝ ሁሉ የከፋ ነበረ። ወቀሳ፣ ብቸኝነት፣ ጥርጣሬ፣ ውድቀት እና ፀፀት ወረረኝ።

ተስፋን እና ደስታን በድጋሚ ለማግኘት ጊዜ ወሰደብኝ ነገር ግን ለመዳን የወሰድኩት እርምጃ በጣም ጠቃሚ ነበር። ማዘኔ እና ልጄን እያሰብኩ ማልቀሴ ለእኔ ጥሩ እንደሆነ ተረዳሁ፤ ምንም እንዳልተፈጠረ መሆን እንደሌለብኝ ገባኝ። አንድ ከባድ ነገር ደርሶብኛል፤ የምወደው ልጄ ገና ከማህፀኔ ሳይወጣ ሞቶብኛል። ስለዚህ ማዘኔ ትክክል ነው። እንዲሁም ስላጣሁት ነገር ለሌሎች ሰዎች ማካፈሌ እና መናገር መቻሌ በረከት ሆነልኝ። ለካስ እንደእኔ በብዙ የልብ ስብራት አልፈው ዛሬ ግን የብዙ ልጆች እናት የሆኑ ብዙ ሰዎች አሉ። ለካስ ከእኔ በእድሜም በተሞክሮም የሚበልጡ ብዙ ሰዎች አሉ። በጣም ትልቁ እርዳታዬ ደግሞ ከገጠመኝ ባዶነት እና ጥርጣሬ በኃላ እግዚአብሔር ልቤን በመፈወስ እንደገና በተስፋ ሞላኝ።

ጤናማ በሆነ መንገድ ሀዘኖትን ለመግለፅ ከፈለጉ ሁሌም ጆሮዋችን ክፍት ነው። በዚህ ውስጥ ለብቻዎት መለፍ የለቦትም። ከስር ያለውን ፎርም በመሙላት አድራሻዎን ካስቀመጡልን ሚስጥር ጠባቂ የሆነ አማካሪ ይመደብሎታል። ትክክለኛ ስሞን መግለፅ አይጠበቅቦትም።

Author's Name changed for privacy.

ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡


እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡

የእርስዎ ፆታ:
የዕድሜ ክልል:

ተገቢውን አማካሪ እንዲመድብዎት የእርስዎ ፆታ እና ዕድሜ እንጠይቃለን። የአገልግሎት ውሎች & የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ.

እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!