ተራርቀው ለሚኖሩ ባለትዳሮች 5 ጠቃሚ ምክሮች፡

ለረዥም ጊዜ ከሚያፈቅሩት ሰው ተለይቶ መቆየት በጣም ከባድ ነው። ከትዳር አጋር ጋር አንድ ላይ አለመሆን መታቀፍ፣ መሳም ወይም መነካካት ሲፈልጉ ማጣት በጣም ስሜትን የሚጎዳ ነገር ነው። ትንንሽ የሚባሉ የማበረታቻ ቃላት እንኳን በጣም አስፈላጊ ናቸው። ለመገናኘት እንኳን የደርሶ መልስ የትራስፖርት ገንዘብ ቀላል አይሆንም አንዳንዴም ለጉዞ አመቺ አይሆንም። ፍቅር በሁለት ግለሰቦች መካከል የሚፈጠር ሲሆን በቦታ መራራቅ የተነሳ ግንኙነቱ እንዳይቋረጥ ሁለቱም የበኩላቸውን ሀላፊነት ሊወጡ ይገባል። የትዳር ጎደኛዎን እንዴት በርቀት በእንክብካቤ እንደሚይዙ ሀሳብ ከገባዎት የፍቅር እሳቱ እየተቀጣጠለ እንዲቆይ የሚያደርጉ አምስት ምክሮች እነሆ፡

  1. እርስ በእርስ ሊኖራችሁ የሚገባውን ግንኙነት ገንቡ

ምን ያህል ግንኙነት እንዲኖራችሁ ትፈልጋላችሁ? ምን አይነት ግንኙነቶች ታደረጋላችሁ? አንዳችሁ ለሌላችሁ ቃል በመግባት ውሳኔ አድርጉ እና በአመት ስንት ጊዜ እንደምትገናኙ አስሉ። ማን ጉዞውን እንደሚያደርግ እና የጉዞ ወጪን እንዴት እንደምትሸፍኑም አስቡበት።

  1. ግንኙነታችሁ አይቋረጥ

አንድም ቀን እንኳን ሳትነጋገሩ እንዲያልፍ አታድርጉ። በተለያየ መንገድ ልታደርጉት ትችላላችሁ። መልዕክት መላላክ ከወጪም አንፃር በጣም ወጪ ቆጣቢ እና ጥሩ አማራጭ ነው። መደዋዋል ወይም የቪዲዮ ጥሪ ማድረግም ምርጫው ካለ እጅግ ተመራጭ መንገድ ነው።

  1. የጋራ ፍላጎቶችን መከተል

ግንኙነቶች ማደግ እንዲችሉ ፍቅረኛሞች አንዳንድ ነገሮችን በአንድነት ማድረግ ይኖርባቸዋል። ሁልጊዜ ከፍቅረኛችሁ ጋር አብራችሁ ባትሆኑ እንኳን አንዳንድ ነገሮችን በአንድነት ማድረግ ትችላላችሁ። አንዳንድ የቴሌቭዥን ፕሮግራሞችን በአንድነት በማየት በጉዳዩ ላይ ተወያዩበት። በልታችሁ የወደዳችሁትን ምግብ ንገሩት እና እሱም ምግቡን እንዲሞክረው አድርጉ። አንድ አይነት ፅሑፍ ወይም መጽሐፍም ማንበብ ይቻላል።

  1. ስለወደፊት ተነጋገሩ

ስለወደፊት ያላችሁን እቅድ ተነጋገሩ። ግንኙነቱ ወዴት እየሄደ ነው? መለያየቱ ጊዜያዊ ነው ወይስ ዘላቂ? ይህ ግንኙነቱ እንዲጠነክር ያግዛል። ምክንያቱም ዝም ብላችሁ ጊዜያችሁን እያቃጠላችሁ እንዳልሆነ ነገር ግን የምትጋሩት አንድ የጋራ ግብ እንዳላችሁ በመረዳት ግንኙነታችሁ እንዲጠነክር ይረዳል። የምታስቡትን፣ የምታልሙትን በሙሉ ለአጋራችሁ አጋሩ።

  1. እንዲያስታውሳችሁ የሚያደርግ ነገር ስጡት/ላኩለት

የራሳችሁ የሆነ ነገር ተለዋወጡ፤ የሆነ ከእናንተ ጋር የተገናኘ እና ፍቅረኛችሁ እንዲኖረው የምትፈልጉት። ይህ ነገር ማንኛውም ነገር ሊሆን ይችላል፡ የፍቅር ደብዳቤ፣ መደረቢያ ልብስ፣ የምትወዱት ሽቶ ወይም ቶሎ የማይበላሹ የሚበሉ ነገሮች። እናንተን የሚያስታውሳቸው ማንኛውም ነገር።

በግንኙነት ውስጥ እጅግ ጠቃሚ ነገር ግንኙነታችሁን መቀጠል እና እርስ በእርስ በግልፅ መነጋገር ነው። እነዚህ ከሌሉ በቅርበት የሚደረግ ግንኙነት እንኳን ይሞታል። ስለዚህ በእርግጥ አፍቃሪያችሁን የምትወዱ ከሆነ ርቀት ሊገድባችሁ ወይም ሊያስቆማችሁ አይገባም። ቴክኖሎጂም ለእናንተ ነገሮችን ቀለል ለማድረግ እራሱን እያዘመነ ይገኛል። የፍቅር አጋራችሁ ከእናንተ ርቆ ስለሚኖር ብቻ በፍቅር ተስፋ አትቁረጡ። ሁለታችሁም አንዳችሁን ለአንዳችሁ የምትሰጡ እና ቁርጠኛ ከሆናችሁ፤ ግንኙነቱ ፍሬ ያፈራል።

በግንኙነትዎት ውስጥ በሚፈጠር ችግር ለብቻዎት መሰቃየት የለቦትም። ሚስጥር ጠበቂ ከሆኑ እና በነፃ ከሚያማክሩ አማካሪዎቻችን ጋር መገናኘት ይችላሉ።


ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡


እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡

የእርስዎ ፆታ:
የዕድሜ ክልል:

ተገቢውን አማካሪ እንዲመድብዎት የእርስዎ ፆታ እና ዕድሜ እንጠይቃለን። የአገልግሎት ውሎች & የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ.

እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!