አሁንም ተፈላጊ ለመሆን በመጣር ላይ
በህይወቴ ብዙ ከራሴ ጋር የመሆንና የማሳለፍ ልምምዶች አሉኝ። ለረዥም ጊዜያት ከቤተሰቦቼ እና ጓደኞቼ በመለየት ወደ ሶስት በሚሆኑ ከተሞች ኖሬያለሁ። ከተመረኩኝ በኋላም ትምህርቴን እና ስራዬን በግብርና መጀመር ደስተኛና ስኬታማ የሚደርገኝ ህይወቴን ቀያሪ እድል እንደሆነ አስቤ ነበር። በጥቂት ጊዜያት ውስጥ ግን ብቸኝነት ከአቅሜ በላይ ሆነ።
በህይወቴ ነገሮችን በራሴ መወሰንና ማድረግ የምችል ነጻ ሰው ነኝ። ይህ ማለት ግን በህይወቴ ውስጥ ሰዎች አያስፈልጉኝም ማለት አይደለም። ታውቃላችሁ በህይወቴ ውስጥ መቼም እለምደዋለሁ ብዬ ማላስበው ነገር ቢኖር ብቻዬን ሬስቶራንት ውስጥ ተቀምጬ መብላት ነው። በባህሪዬ ብዙም ተግባቢ እና ደፋር የምባል ሰው አይደለሁም ፤ በዚህም ምክንያት ብቻዬን ሬስቶራንት ውስጥ ገብቶ መመገብ ለኔ በጣም አስቸጋሪ ነገር ነው። ብገባ እንኳን ብዙ ጊዜ ትኩረት ላለመስጠትና ምንም እንዳልመሰለው ለመሆን በጣም እጣጣራለሁ። ስልኬ ላይም ትኩረቴን ለማድረግ እሞክራለሁ፡፡ ግን በመጨረሻ ስልኬን አስቀምጥና ብቻዬን ሬስቶራንት ውስጥ አጠገቤ ማንም በሌለበት እየተመገብኩ እንደሆነ እውነታውን ለማሰብ እገደዳለሁ።
ይህን ስሜት ሬስቶራንት ውስጥ ብቻ አይደለም የማስተናግደው። በአንድ ወቅት አንድ የቅርብ ጓደኛዬ አየር ማረፊያ ውስጥ ሆና “በአጠገቤ ብዙ ሰዎች አሉ እርስ በእርሳቸው ያወራሉ፣ ይጨዋወታሉ፣ ይሳሳቃሉ ፤ እኔ ግን እዚህ ብቻዬን ኩርምት ብዬ ተቀምጫለሁ! ብቻዬን!” ብላ በዛ ሁሉ ግርግር ውስጥ ብቸኝነት እንደተሰማት እና ስሜቱም ምን ያህል ያልተለመደ እና እንግዳ እንደሆነባት መልዕክት ልካልኝ ነበር። በሰዓቱ ለርሷ መንገሬ ትዝ ባይለኝም ግን በሰዓቱ ምን ያህል ጊዜ ይህ ስሜት እኔንም እንደተሰማኝ አስታውሳለሁ።
በአጠገቤ ብዙ ሰዎች አሉ እርስ በእርሳቸው ያወራሉ፣ ይጨዋወታሉ፣ ይሳሳቃሉ ፤ እኔ ግን እዚህ ብቻዬን ኩርምት ብዬ ተቀምጫለሁ! ብቻዬን!
አንዳንድ ጊዜ አንዳንድ ብቸኝነቶቼ ከእድሜዬ እንደመጡ እስባለሁ። እንደ እውነቱ ሙሉ በሙሉ ራሴን የቻልኩበት ደረጃ ላይ አይደለሁም ቢሆንም ግን ነገሮችን በራሴ ለማድረግ፣ ብቻዬን ከሆነ ቦታ የሆነ ቦታ ለመንቀሳቀስ፣ በግሌ ለመኖር አዎ ነጻ ነኝ ፤ ራሴንም ችያለሁ። ታውቃላችሁ አንዳንድ ጊዜ በጣም በፍጥነት እንዳደኩ ይሰማኛል። እናም ለዛ ይመስለኛል በዚህ በማይመችና ግራ በገባው ቦታ ላይ መሃል ላይ ተጣብቄ የቀረሁት።
እንደ እውነቱ ከሄድን በህይወቴ ውስጥ ብዙ ጓደኛ እና ቤተሰብ አለኝ ፤ አዎ ከብዙዎች የበለጠ በጣም እድለኛ ነኝ። ነገር ግን በአንድ ወቅት ከነበሩኝ ሰዎች ጋር ጥልቅ የሆነ የጠበቀ መተሳሰር አልነበረኝም። በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በነበርኩበት ጊዜ በአጠገቤ ብዙ ጓደኞች በነበሩኝ ሰዓት ሁልጊዜም ቢሆን ቢያንስ አንድ ከአጠገቤ ተቀምጦ የማወራው ጓደኛ ነበርኝ። እያደኩ ስሄድና ህይወቴን ለመቀጠል ስጣጣር ግን እነዚህ ሰዎች ይበልጥ እየራቁ ሄዱ። እየተሰማኝ የነበረውንም ባዶነት ፍጹም ሊሞሉት አልቻሉም።
በህይወቴ ውስጥ በሰዎች ብቻ ሊሞላ እንደሚችል የማስበው የህይወት ቀዳዳ ነበረኝ። ታዲያ ግን በተቃራኒው ከሰዎች ጋር ይበልጥ በተቀራረብኩ ቁጥር ይበልጥ ብቸኝነት ይሰማኝ ጀመረ። ታዲያ ይህ ብቸኝነት ከቀን ወደ ቀን ከንቱ እንደሆንኩ እንዲሰማኝ ያደርገኝ ጀመር። በህይወቴ እርካታ ማጣት እና ለድብርት ተጋላጭ ሆንኩ። ራስን የማጥፋት ሃሳቦች ወደ አዕምሮዬም ይመላለሱ ጀመር። ምንም መፍትሄ ማግኘት አልተቻልኩም ነበር።
አንዳንድ የህይወት ውስብስብና አስቸጋሪ ፈተናዎችን እስካልፍ ድረስ በህይወቴ ውስጥ ያለውን ባዶነት ሙሉ በሙሉ በሰዎች ሊሞላ እንደማይችል አልተገነዘብኩኝም ነበር። አሁንም ፈተናዎቼ እና ትግሎቼ ብን ብለው አልጠፉም። በተቃራኒው አሁንም ብቸኝነት ይሰማኛል። ጥልቅ የሆኑ ግንኙነቶች ቢኖሩኝ ብዬ እጓጓለሁ። ምንም እንኳን እንዲህ ቢሰማኝም ግን አንድ ነገር አሁን ላይ ተረድቻለሁ። ምንም አይነት ስሜት ቢሰማኝም እንኳ ብቻዬን አይደለሁም። በእነዚህ ስሜቶቼ ላይ ፍጹም ብቻዬን አይደለሁም! አንተም ወይም አንቺም በብቸኝነት ስሜት እየተሰቃህ ወይም እየተሰቃየሽ ከሆነ ብቻችሁን አይደላችሁም። ከዚህ በታች መረጃዎትን ይተዉልን፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከቡድናችን የሆነ ሰው ያገኞታል። ይህንን አብረን መጋፈጥ እንችላለን!!!
ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡
እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡
እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!