ከስራ መባረር እና በራስ መተማመን

በአንድ ድርጅት ውስጥ ተቀጥሬ ባይሆንም ከሀያ አመት በላይ ስራ ስርቻለሁ፡፡ ባለፉት ሁለት አስርት አመታት ወደ 7 ወይም 8 የሚሆኑ ድርጅቶች ውስጥ አገልግያለሁ እና ከአንዳንዶቹ ስባረር ከሌሎቹ ደግሞ በራሴ ፍቃድ ለቅቄለሁ፡፡ አሁን በአርባዎቹ መጀመሪያ እድሜ ላይ ሆኜ ለእኔ ተስማሚ እና ቋሚ የሆነ ስራ እየፈለኩ እገኛለሁ፡፡

ከቀድሞው መስሪያ ቤቴ እንድሰራ ሲደወልልኝ ወዲያው ነበረ እድሉን የተቀበልኩት፡፡ በጣም ጥሩ በጀት አግኝተው በፊት እኔ ለዘጠኝ አመታት ከስራሁበት ቢሮ ሌላ አዲስ እና ትልቅ ቢሮ ቀይረው ገብተዋል፡፡ ሁሉም ነገር ጥሩ ይመስላል፡፡ ብዙ ገንዘብ እና የሚደርሱበትን ሚያውቁበት የረዥም ጊዜ እቅድ ነበራቸው፡፡ አንድንድ የቀድሞ የስራ ባደረባዎቼን እና ሀለቃዎቼን አገኘሁኝ፡፡ ያሰብኩት ሁሉ እንደተሳካ ነበር የተሰማኝ፡፡ ወደ ለመድኩት የስራ አከባቢ እና ወደ ቀድሞ የስራ ባደረቦቼ መመለሴ ምቾትን ፈጠረልኝ፡፡

ልክ ምኞቴ ሁሉ እውነት የሆነ ያህል ነው የተሰማኝ፡፡

ስራ ተጀመረ እና አስቀድሜ በማውቀው የስራ ሂደት ውስጥ ተመደብኩኝ፡፡ አብዛኛዎቹ የቡድኑ አባላት አዳዲስ ሰራተኞች ናቸው ግን ደግሞ አንዳንድ ቀድሞ በሌላ ስራ ሂደት ውስጥ የነበሩ ነባር ስራተኞችም ነበሩ፡፡ በጣም ደስ ይል ነበረ፡፡ ልክ ምኞቴ ሁሉ እውነት የሆነ ያህል ነው የተሰማኝ፡፡ ስራውን ከጠበኩት በላይ ቶሎ ነበር የለመድኩት፡፡ ነገር ግን ከውጪ ድርጅቱ የተረጋጋ ቢመስልም ብዙ ገንዘብ ለማስታወቂያ ይፈስ እንደነበር አስተውያለሁ፡፡

ከስድስት ወር በኃላ ነገሮች መበላሸት ጀመሩ፡፡ የድርጅቱ ባለቤት ወንድ ልጁን በድርጅቱ ወሳኝ ቦታ ላይ አስቀመጠው፡፡ ይህ ሰው ለስራው አስፈላጊ የሆነ ችሎታም ሆነ ተሞክሮ አልነበረውም፡፡ በመሆኑም የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቱ አቅም የሌለው ሆነ፡፡ የገንዘብ እጥረት ተከሰተ፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ ደሞዛችንም መዘግየት ጀመር፡፡

ስራውን ከጀመርኩኝ አመት እንደሆነኝ የድርጅቱ አስተዳደር አስደንጋጭ ነገር ይፋ አደረገ፡፡.

ስራውን ከጀመርኩኝ አመት እንደሆነኝ የድርጅቱ አስተዳደር አስንጋጭ ነገር ይፋ አደረገ፡፡ ይህም ድርጅቱን ለመታደግ አንዳንድ ስራተኞችን መቀነስ አስፋላጊ መሆኑን ነበረ፡፡ እኔም ለቡድኔ እንዲሁም ለእኔ ትንሽ ስጋት ተሰማኝ፡፡ ነገር ግን እኔን ስራ ከለቀኩኝ በኃላ መልሰው ስለጠሩኝ እና የእኔ ቡድን አባላት ቁጥር ትንሽ ስለሆነ መፍለጫ እኛ ላይ እንደማይወድቅ አሰብኩኝ፡፡ በተጨማሪም የስራተኞች ቅነሳ ይፋ ከመደረጉ ጥቂት ቀናት በፊት የድርጅቱ አስተዳደር እኔ ወደ ቢሮው ጠርቶኝ እንዴት የእኔን የስራ ሂደት ማጠናከር እንደምንችል እና ቡድኑን ማነቃቃት እንደምንችል ስንወያይ ነበረ፡፡

አንድ ቀን የሰው ሀብት አስተዳደሩን እነዳገኘው ተነገረኝ፡፡ በእርግጠኝነት እና በራስ በመተማመን ወደ ቢሮው ገባሁኝ፡፡ ውይይቱ በመልካም ነገር ቢጀመርም ወዲያው ከዚህ በኃላ እንደማላስፈልግ ተነገረኝ፡፡ ከልቤ ድንግጪ እና ማመን እያቃተኝ ከሁለት ቀናት በፊት ከድርጅቱ አስተዳደር ጋር ቡድኑን ስለማጠናከር እና ማነቃቃት እያወረራን እንደነበረ ነገርኩት፡፡ በ48 ሰዓት ውስጥ ምን ተቀየረ? ምንም አይነት ምክንያታዊ መልስ ማግኘት አልቻልኩም፡፡

በጣም ተናድጄ ከቢሮው ወጥቼ ከቡድኔ አባላት ጋር ተገናኝቼ ዜናውን ነገርኳቸው፡፡ ልክ እንደኔው በጣም ነበር የተገረሙት፡፡ ወዲያው ቢሮውን ትቼ ወደቤቴ ሄድኩኝ፡፡ ‹ምንድነው የተፈጠረው?› የሚሉ እና ‹ለምንድነው ይህ የተፈጠረው?› የሚሉ ብዙ ጥያቄዎች ሀሳቤን ተቆጣጥረውታል፡፡ ማመን አልቻልኩም፡፡ ለቤተሰቦቼ ምን ብዬ ነው የምነግራቸው? እንደተዋረድኩኝ እና በጣም መጥፎ በሆነ መንገድ እምነት እንደታጣብኝ ተሰማኝ፡፡

ከስራ ከተባረርኩኝ አንድ አመት ሆነኝ ነገር ግን አሁንም እንደተናደድኩኝ፣ እንደተጎዳሁኝ እና እንደተዋረድኩኝ አለሁ፡፡ ስራ መፈልጌን ቀጥያሁ ነገር ግን ከስራ የተባረርኩበት መርዶ በጭንቅቴ ውስጥ አሁንም ያንቃጭልብኛል፡፡ ጊዜ ሁሉንም ቁስል ይፈውሳል አይደል የሚባለው፤ ይህንን ተስፋ አደርጋሁ፡፡ አሁን ስራ የለኝም ነገር ግን ተስፋ አልቆረጥኩም፡፡

ተመሳሳይ ችግሮች እያጋጠሙዎት ከሆነ ብቻዎን እንዳልሆኑ ያስታውሱ እርስዎ ባለፉበት ያለፈ ሰው አለ፡፡ እባክዎን ስለዚህ ጉዳይ ለማዋየት ወደኋላ አይበሉ ፡፡ ከዚህ በታች መረጃዎን ከሞሉ ከአማካሪዎቻችን አንዱ ይመልስልዎታል ፡፡ ሙሉ በሙሉ ነፃ እና ሚስጥራዊ ነው። እውነተኛ ስምዎን ወይም የሐሰት ስም ሊሰጡት ይችላሉ። ሙሉ በሙሉ የእርስዎ ምርጫ ነው ፡፡


ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡


እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡

የእርስዎ ፆታ:
የዕድሜ ክልል:

ተገቢውን አማካሪ እንዲመድብዎት የእርስዎ ፆታ እና ዕድሜ እንጠይቃለን። የአገልግሎት ውሎች & የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ.

እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!