የማንነት ቀውስ

ፀሀፊ፣ ኮሜዲያን፣ ዳንሰኛ ነኝ። ግን በእውነት እኔ ማን ነኝ? ገና እየፈለኩ ነው ያለሁት። ለአሁኑ ትዝታ ልትሉኝ ትችላላችሁ።

የማንነታችን ስሜት የሚያስቅ ነገር ሊሆን ይችላል። ሁሉም ሰው የሆነ ጊዜ ላይ “እኔ ማን ነኝ?” ብሎ ጠይቋል። ማን ናችሁ ተብላችሁ ብትጠየቁ፤ ምንድን ነው የምትመልሱት?

በግሌ ተማሪ ነበርኩ እና አሁን ፀሀፊ ነኝ። ብዙ ጊዜ ግን ራሴን የምገልፀው እንደ ጥቁር ፀጉር ያላት ሴት ወይም በራሴ ባህላዊ እምነት ነው።ግን ለብዙ አመታት መልሴ በማያጠራጥር እና ብቸኛ በሆነ መልኩ ደናሽ ነኝ የሚል ነበር። ትንሽ እየነበርኩ በማህበራዊ ሁኔታ ውስጥ በጣም አይናፋር ነበርኩ እና ከዚህ ፀባዬ እንድድን ወላጅቼ አቅራቢያችን ያለ ዳንስ የሚያስተምሩ ማዕከል ውስጥ አስገቡኝ። ወዲያው ነው የወደድኩት እና ህልሜን መኖር ጀመርኩ።ወዲያው በሳምንት ለ20 ሰዓት መደነስ ጀመርኩ። የ ”ያለልፋት ማሸነፍ የለም” የሚለው አባባል ትርጉም ገባኝ፤ ግን ያለጥርጥር ደስተኛ ነበርኩ እና እንደ ዳንሰኛ በነበረኝ ማንነት እተማመን ነበር።

ግን አደኩ እና በጣም ረዥም ሆንኩኝ፤ ቆዳ እና አጥንት ብቻ ሆንኩ። አስተማሪዬ አካላዊ ችግሬ ይጦቅም እና ለቀረው ተማሪ እንዲስቁብኝ ያበረታታል። በጣም ያስጨንቅ ነበር ፀጉሬ ሁላ መርገፍ ጀመረ።

ከውብ እና ሰልከክ ያለ ቁመና እንዳለኝ ከማመን ወደ የተፈጥሮ ችግር እንዳለብኝ ወደ ማሰብ በአንዴ ተቀየርኩ።

ከውብ እና ሰልከክ ያለ ቁመና እንዳለኝ ከማመን ወደ የተፈጥሮ ችግር እንዳለብኝ ወደ ማሰብ በአንዴ ተቀየርኩ። ለመጀመሪያ ጊዜ፤ በጣም እርግጠኛ የሆንኩበት ነገር - ስጦታ፣ ሞገስ፣ ዋጋ እንዳለኝ ማመን - ወደ ጥያቄ ገቡ። እንደ ሌሎቹ ዳንሰኞች ካልመሰልኩ እኔ አሁን በእውነት ዳንሰኛ ነኝ? ከውብ እና ሰልከክ ያለ ቁመና እንዳለኝ ከማመን ወደ የተፈጥሮ ችግር እንዳለብኝ ወደ ማሰብ በአንዴ ተቀየርኩ። እያጋጠመኝ ያለውን የስሜት ጉዳት እኔ እና ወላጆቼ ካጤንን በኋላ፤ በቃላት የሚያጠቃ አሰልጣኝ ካለበት ስቱዲዮ ወደ ሌላ መቀየር የተሻለ አማራጭ መስሎ ታየን። ግን ትምህርት ቤት ወይም ስራ ቀይራችሁ የምታውቁ ከሆነ ምን ያህል አዲስ ቦታ መልመድ ከባድ እንደሆነ ታውቃላችሁ፤ ለስኬት የሚሆን ተሰጥዖ እንኳን ቢኖራችሁ። ረዥም ጊዜ ወሰደብኝ ትንሹን ስቱዲዮ ለመልመድ እና አስተማሪውም ቀለል ያለ ነው። ክፍሌ ውስጥ ያሉት ሁሉም ሴቶች ቅርፅ አውጥተዋል እና እኔ አሁንም እንደ ጣውላ ልሙጥ ነኝ እና ከሌሎቹ ሴቶች እረዝማለሁ ስለዚህ ልምምድ ላይ አስተማሪዬ የወንዱን ገፀ ባህሪ ይሰጠኝ ነበር። ግልጽ የሆነ ተዋረድ እንዳለ ያስታውቅ ነበር እና እኔ ያለሁት መጨረሻ አካባቢ እንደሆነ አውቅ ነበር። በጊዜ ሂደት እየተመቸኝ መጣ እና በድጋሜ በራስ መተማመኔ እየጨመረ መጣ።

ጊዜ ወሰደብኝ ማንነቴ ከችሎታዬ ወይም ከአቋሜ በላይ እንደሆነ ለማወቅ።

አንድ ቀን በደንብ ሳላስብበት አንድ ጓደኛዬ ሳይክል እንዲያስተምረኝ ፈቀድኩ እና እግሬ ተሰበረ።ከሁለት ቀዶ ጥገና እና ከአንድ አመት ፊዚዮ ቴራፒ በኋላ ወደ ዳንሴ ተመለስኩ ግን በጣም ወደኋላ ቀርቼ ስለነበር እነሱ ያሉበት ጋር መድረስ የሚሆን አልመሰለኝም። በግልፅነት አሰልጣኜ ድጋሜ ለመወዳደር ብሞክር ጓደኞቼን ወደ ኋላ እንደማስቀራቸው ነገርኝ። ግራ ገባኝ። ትንሽ ምርጫ ነበር የነበረኝ ከ14 የስቃይ ግን የተሳኩ አመታት በኋላ ዳንስ ለማቆም። ልቤ እና ተስፋዬ ነው የተሰበረው እና ማን ነኝ እና እነዛን ስብርባሪዎች እንዴት ነው የማነሳው የሚለው ውስጥ ነው በሃሳብ የተተውኩት። ከዛ በኋላ ልክ እንደ እስስት ነው የሆንኩት፥ በዙሪያዬ ያሉትን ተቀባይነት እና የሚያጋጥሙኝ የትኛውም ቡድን ውስጥ ለመግባት የበለጠ ለማግኘት መሞከር ጀመርኩ። ችግሮቼን መደበቅ ጀመርኩ፤ አካላዊም ሆነ የውስጤን፤ ምንም ነገር አደርጋለሁ እንዲቀበሉኝ እና እንዲያመሰግኑኝ። ዳንስ የሰጠኝ ፍቅር በጣም ረዥም በመሆን፣ ወንዳ ወንድ በመሆን ወይም በጣም ለስሜት ቅርብ በመሆን እንደ ጣልኩት ነው የተሰማኝ። የቀን ቅዠት እንደሚባለው የሆነ ሰው ችግሮቼን ሁሉ አውቆ ሲወደኝ አያለሁ ግን እውነት ይሆናል ብዬ አምኜ አላውቅም። ጊዜ ወሰደብኝ ማንነቴ ከችሎታዬ ወይም ከአቋሜ በላይ እንደሆነ ለማወቅ።

በጣም ቆንጆ ወይም በራሳችሁ ነገሮችን ማድረግ የምትችሉ፤ ወላጅ ወይም አትሌት፤ ምሁር ወይም የሽያጭ ሰራተኛ ብትሆኑ፤ እነዚህ ነገሮች ይቀየራሉ። ሁላችንም የሆነ ዋጋ እንዳለን ማወቅ እንፈልጋለን፤ ከአየሩ ጋር የማይቀየር የሆነ ወሳኝ ሰዎች ሆነን እንድንታውቅ እንፈልጋለን። የተጋፈጡት ችግር ማንነቶን መፈለግ እና በማንነቶ ላይ መተማመን ከሆነ፤ ከቡድናችን አንድ ሰው ቢያናግሮት ደስ ይለዋል። ከታች አድራሻዎን ይተዉልን። ብቻዎን አይደሉም።


ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡


እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡

የእርስዎ ፆታ:
የዕድሜ ክልል:

ተገቢውን አማካሪ እንዲመድብዎት የእርስዎ ፆታ እና ዕድሜ እንጠይቃለን። የአገልግሎት ውሎች & የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ.

እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!