እንዴት ስኬት እና እርካታን ማግኘት እንደሚቻል

እንዴት ስኬት እና እርካታን ማግኘት እንደሚችል ስኬት ማለት “....…” ባዶ ቦታውን እንዴት ትሞሉታላችሁ?

ቀላል ነው ልትሉ ትችላላችሁ። “ስኬት ማለት ለአንድ አትሌት የኦሎምፒክ ውድድርን ማሸነፍ እና ወርቅ ማግኘት ሊሆን ይችላል፣ ለአንድ ተዋናይ እንደ ኦስካር እና ግራሚ ያሉ ሽልማቶችን ማሸነፍ ሊሆን ይችላል፣ ለአንድ የንግድ ድርጅት ባለቤት ደግሞ በአለም ላይ ካሉ ስኬታማ 500 ድርጅቶች ቀዳሚው ድርጅት መሆን ሊሆን ይችላል፣ እንዲሁም ለአንድ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ደግሞ የተማሪ መማክርት ወይም የተማሪ ፕሬዝዳንት ተደርጎ መመረጥ ሊሆን ይችላል። ሁልጊዜ በዚህ መልኩ ትርጉም መስጠት ይቻላል? አንዳንድ ጊዜ ለእኛ ስኬት የሆነ ነገር በሌላ ሰው ዘንድ እንደ ስኬት ላይቆጠር ይችላል። ምን አልባት እኔ በስራ ቦታዬ ከባለፈው ወር የበለጠ ውጤት በማምጣት አጥጋቢ ውጤት በማስመዝገቤ ስኬታማ እንደሆንኩኝ ላስብ እችላለሁ ነገር ግን የእኔ የስራ ባልደረባ ከእኔ የተሻለ ውጤት አስመዝግቦም ስኬታማ እንዳልሆነ በማሰብ ሊበሳጭ ይችላል። በመሆኑም ስኬት እንደየሰዉ፣ እንደባህሉ እና አኖኖሩ ትርጉም ሊለያይ ይችላል።

የስኬት ትርጉም ከሰው ሰው ይለያያል። አንድ መዝገበ ቃላት ስኬትን “የተፈለገውን ግብ ለመድረስ የተገኘ አጥጋቢ ውጤት” በማለት ይተረጉመዋል። ስኬታማ ለመሆን ግቡ ጋር መድረስ እና በግቡ ደግሞ መርካት አለባችሁ። በዚህ ትርጉም መሰረት የአንድ ሰው ስኬት እርካታን ካላስከተለ በእርግጥ እውነተኛ ስኬት ነው ተብሎ ሊጠይቅ ይችላል።

የስኬት ቁልፎች

በርካታ ምክንያቶች ለስኬት አስተዋፅኦ ያደርጋሉ። ለስኬት አስፈላጊ የሆኑ አራት ነገሮችን ተመልከቱ፡

1.አወንታዊ ግለ-እውቀት

አንድ ጠዋት ከእንቅልፋችሁ ስትነሱ አንድ ጎደኛችሁ የሆነ ነገር ሊነግራችሁ እየጠበቃችሁ እንደሆነ አስቡ። እሱ ወይም እሳ “እንዴት ያለ ምርጥ ጎደኛ እንደሆንክ ለመንገር እየጠበኩ ነበር። አንተ በጣም ደግ፣ አሳቢ እና መልካም ጎደኛዬ ነህ። ከአጠገብ መሆኔ በራሱ እኔም በጣም መልካም ሰው እንድሆን ያነሳሳኛል። አንተ መልካም ሰው ነህ” ይላችሀል። ከዛም ተነስታችሁ ወደ ትምህርት ክፍላችሁ ስታቀኑ የፍቅር ጎደኛችሁ ተከትላ ትደርስባችሁ እና “ስላገኘሁክ በጣም ደስ ብሎኛል። ባለፈ ካንተ ጋር እንዴት ደስ የሚል ጊዜ እድናሳለፍኩኝ ልነግርህ ፈልጌ ነበር። ጎደኞቼ ሁሉ በጣም ነው የቀኑብኝ። ካንተ ጋር አብሬ ማሳለፍ በመቻሌ ከሁሉም በላይ እደለኛ እንደሆንኩኝ ነገሩኝ እና እኔ አንተ የእኔ በመሆንህ እድለኛ ነኝ። በጣም ተግባቢ እና ጎበዝ ነህ፣ በጣም ቆንጆ እና የማትጠገብ ነህ። ካንተ ጋር ስሆን የህልም አለም ውስጥ በደስታ እንደተዘፈኩኝ ይስማኛል” ትልሀለች። ከዛ ወደምትማርበት ክፍል ትገባለህ። አስተማሪያችሁ “ባለፈው ሳምንት የተፈተናችሁትን ፈተና ከመመለሴ በፊት አንድ ማስታወቂያ አለኝ” ይላል። “ይህ ተማሪ በዚህ ፈተና እንዴት ያለ ጥሩ ስራ እንደሰራ ሁላችሁም እንድታውቁ እፈልጋለሁ።” ወደ አንተ እየጠቆመ “አንተ ማለት ለእኔ ለአስተማሪህ ንፁህ አየር እንደመማግ ነህ። ሁል ጊዜም የቤት ስራዎችህን በጊዜ ነው የምትሰራው። በአብዛኛው ከሚጠበቅብህ በላይ ነው የሚትሰራው። ሁሉም ተማሪዎች እንደአንተ ቢሆኑ ማስተማር እጅግ ደስታ ይሆን ነበር። አንተን ከማስተማሬ በፊት ማስተማር ለማቆም እያሰብኩኝ ነበር። አንተ ግን በማስተማር እንድቀጥል አቅም ሆነኸኝ አመስግናለሁ” ይልሀል። ይህ ስለራሳችሁ ጥሩ አመለካከት እንዲኖራችሁ አያደርጋችሁም? የተሻለ ጎደኛ፣ የሚወደድ ፍቅረኛ፣ የተሻለ ተማሪ እንድትሆኑ ይበልጥ አያነሳሳችሁም? ለራሳችሁ “ጎደኛዪም፣ ፍቅረኛዬም አስተማሪዬም በጣም ጥሩ ሰው መሆኔን ነግረውኛል ስለዚህ እኔ ጥሩ ሰው መሆን አለብኝ” ብላችሁ እንድታስቡ ያደርጋችሀል። ጥሩ ስለመሆናችሁ ምንም ጥያቄ የለውም። በእርግጥ አንዳንድ ሰዎች ለራሳቸው ያላቸው አመለካከት ከሆኑት በላይ የተጋነነ ይሆንና ችግር ይፈጠራል። ለራሳችን ያለን አመለካከት አወንታዊ እና ጠንካራ ሲሆን በህይወታችን ስኬታማ ለመሆን የተሻለው የዝግጅት መንገድ እንደሆነ ብዙዎች ያምናሉ።

2.በግልፅ የተቀመጡ ግቦች

ስኬትን የሚፈልግ ሰው ግልፅ የሆነ ግብ ያስቀምጣል።

ምንም አላማ የሌለው ሰው በእርግጠኝነት አላማውን ያሳካል። አላማ የለውም ስለዚህ የማይሳካ ነገርም የለውም። አንድ ግብ ላይ ስታነጣጥሩ ግቡ ላይ መድረስ ባትችሉ እንኮን ሳታነጣጥሩ ከምትደርሱበት የተሻለ ነገር የማግኘታችሁ እድል ሰፊ ነው። የአሜሪካን የህዋ ምርምር ማዕከል ብዙ ስኬቶች ቢኖሩትም በሚያሳዝን ሁኔታ አሳዛኝ ውድቀቶችም ነበሩት። የናሳ ስኬት ግብ የማስቀመጥን ጥቅም የሚያሳይ ነው። በአፖሎ ስፔስክራፈት እየሰሩ የነበሩ ሶስት የኤሌክትሪክ ሰራተኞችን ታሪክ ስምታችሁ ይሆናል። አንድ ዘጋቢ ሶስቱንም ምን እየሰሩ እንደነበር ጠየቃቸው። የመጀመሪያው “እኔ በስርኪውቱ ውስጥ ትራንዚስተር እየከተትኩኝ ነው” አለ። ሁለተኛው “ገመዶቹን ባንድነት እያሰርኩኝ ነው” አለ። ሶስተኛው ደግሞ “ሰውን ወደ ጨረቃ ለመላክ እየረዳሁ ነው” አለ። የትኛ የበለጠ የተነሳሳ እና በስራው የረካ ይመስላችሀል? እንዴት ስራው ከአጠቃላይ ግቡ ጋር የተገናኘ እንደሆነ ማየት የቻለው ይመስለልኛ። ግልፅ የሆነ የህይወት ግብ ከሌለን የየእለት ሀላፊነቶቻችን ደባሪ ይሆናሉ። የህይወት ግባችንን ማወቃችን የየእለት ስራችን ትልቁን ግብ ለማሳካት መርዳቱን ማወቃችን መነሳሳታችንን እና እርካታችንን ይጨምራል። በ1960 የመጀመሪያዎቹ አመት ፕሪዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኒዲይ በ1960 በመጨረሻው አስርት አመት አንድን አሜሪካዊ ወደ ጨረቃ ለመላክ ግብ አስቀመጡ። በ1969 ኔል አርምስትሮንግ የመጀመሪያውን ትንሽ እርምጃ አደረገ። ግልፅ የሆነ ግብ ማስቀመጡ ናሳ በታሪክ የመጀመሪያውን ዋና ስኬት እንዲጎናፀፉ አደረገ። ስኬትን የሚፈልግ ሰው ግልፅ የሆነ ግብ ያስቀምጣል።

  1. ጠንካራ ስራ

ስኬት ጠንካራ ስራን ይፈልጋል።

ማንኛውም ስኬታማ አትሌት በልምምድ ሜዳው ጠንካራ ስራ ካልሰራ በውድድር ሜዳው ክብር እንደማይኖር ያውቃሉ። የባህሪም መለክያ ህዝብ በተሰበሰበበት የምናሳየው ሳይሆን ማንም ሳያየን ያለን ጠንካራ የስራ ባህሪይ ነው፡ በቢሮ፣ በቤተ መፅሀፍት፣ በተግባር የምናሳያቸው። ፕሬዝዳንት ካልቨን ኮሊድግ “በዚህ አለም ማንኛውም ነገር የፅናትን ቦታ ሊውስድ አይችልም። ተስጦ አይችልም፣ ጉብዝናም አይችልም፣ ትምህርትም አይችልም። ፅናት፣ ቁርጠኝነት እና ጠንካራ የስራ ባህል ለውጥ ያመጣል” ይላል። የቀድሞው የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስተር ማርጋሬት ታቸር “ስኬት ምንድነው?” በማለት ጠየቁ። “ለምትሰሩት ነገር ጥሩ ስሜት መኖር እና በአላማ ጠንክሮ የመስራት … የእነዚህ ውህድ ይመስለኛል። እኔም በስራዬ ችሎታ ነበረኝ ብዬ አስባለሁ ግን ተፈጥሮአዊ ስሜቶች ብቻ በቂ አይደሉም። እነዚህን የተፈጥሮ ስሜቶች ከጠንካራ የስራ ባህል ጋር ማጋባትን ይጠይቃል። የከባድ ሚዛን ቦክስ አሽናፊው ጄምስ ጄ. ኮርቤት “አሽናፊ የምትሆኑት ተጨማሪ አንድ ዙር ስታሽንፉ ነው። ነገሮች ከባድ ሲሆኑ ተጨማሪ አንድ ዙር ትታገላላችሁ” ይላል። ስኬት ጠንካራ ስራን ይፈልጋል። በእርግጥ ከሚገባው በላይ በመስራት የስራ ሱስ ውስጥ ልትገቡ ትችላላችሁ። አንድ የስራ ሱስ ያለበት ነጋዴ በቢሮው ውስጥ እንደዚህ የሚል ፅሁፍ አለ “እግዚአሒሔር ይመስገን ሰኞ ነው” ይላል። ሁላችንም ስራን እና እረፍትን ማመጣጠን አለብን ይሁንና ጠንካራ ስራ ለስኬት መሰረታዊ ነው።

4.ውድቀት ቢያጋጥም ለመቀበል ፍቃደኝነት

“ወደ ግቤ ለመድረስ አንዳንድ ሊያጋጥሙኝ የሚችሉ ውድቀቶችን ለመጋፈጥ ፍቃደኛ ነኝ?

ቴዎዶር ሮዝቬልት በጣም ዝነኛ በሆኑት ንግግሮቹ በአንዱ የዚህ ጉዳይ ዋጋ ግልፆል “ድል እና ሽንፈትን የማያውቁ ስዎች በድንግዝግዝ ውስጥ ስለሚኖሩ ብዙም ከማይዝናኑ እና ብዙም ከማይሰቃዩ ከመመደብ ይልቅ ሀያል የሆኑ ነገሮችን በመድፈር የከበሩ ድሎችን መቀናጀት ባይቻል እንኮን በውድቀት ቢጠናቀቀም እርሱ ይሻላል” ይላል።

ታላቁ የኦሎምፒክ የበረዶ ተንሸራታች ኢንግማር ስተንማርክ እንዲህ ይላል “ለማሸነፍ የመሸነፍ አደጋ ውስጥ መግባት አለብን”። ይህንን ጥያቄ አስተውሉ ‘እንደማትሽነፉ እርግጠኛ ከሆናችሁ ምን ታደርጋላችሁ?”። ይህ ጥያቄ እይታችሁን በማስፋት ህልማቹን ያገዝፈዋል። ምን አልባት ፍላጎታችሁ ታላቅ የፖለቲካ መሪ፣ ተዋናይ፣ ዋና የንግድ ሰው ወይም ምሁር፣ ኮከብ አትሌት መሆን ሊሆን ይችላል። ውድቀት እንደማያጋጥማችሁ ካወቃችሁ ምን ታደርጋላችሁ? ወደ ግባችሁ ትሄዳላችሁ ወይስ ታንገራግራላችሁ?

አሁን እራሳችሁን ጠይቁ “ወደ ግቤ ለመድረስ አንዳንድ ሊያጋጥሙኝ የሚችሉ ውድቀቶችን ለመጋፈጥ ፍቃደኛ ነኝ? ስኬት ሁልጊዜም ሊያጋጥሙ በሚችሉ ውድቀቶች የታጀበ ነው።

  • የስኬት እና የእርካታ ተግዳሮቶች

አውንታዊ ግለ ምልከታ፣ ግልፅ ግብ፣ ጠንካራ ስራ እና ውድቀት ቢያጋጥም ለመቀበል ፍቃደኘነት ሁሉም ለስኬት አስተዋፅኦ ያደርጋሉ። ነገር ግን ስኬትን እና እርካታን በህይወታችን እንዳንለማመድ ሌላ ታላቅ ተግዳሮ አለ። እርሱም የፈለግነውን ግብ ውዲያው ማግኘታችን እርካታን ይፈጥራል ብለን ማሰባችን።

የማህበራዊ ጉዳይ ተንታኝ ዳንኤል ያንክሎቪች እንዲህ ይይላል “በአንድ የህዝብ ግኑኝነት ውስጥ በአመት የ100000 ሺህ ዶላር አጋር ነኝ፣ በሌሎች ትርጉሜ የስኬት ማማ ላይ ወጥቻለሁ እኔ ግን ሙሉነት አይሰማኝም። ስታይ ስኬታማ ነኝ… አሳትሜለሁ፣ አስተምሬለሁ፣ የገቢ ግቤን አልፌለሁ፣ የብዙ ነገሮች ባለቤት ሆኛለሁ እና ብዙ ስዎች በእኔ ገቢ ይተዳደራሉ። ስለዚህ በበቂ ሁኔታ ውጫዊ ግቦቼን አሳክቻለሁ ግን ለእኔ ባዶ ናቸው።

ደስቲን ሆፍማን በጣም ስኬታማ የፊልም ተዋናይ ነው። የፊልም ህይወቱ አስደናቂ ነው እና ካርመር ቨርስ ካርመር በተሰኝ ፊልሙ ባሳየው ብቃት ለኦስካር ቀርቦ ነበር። ስለ ደስታ እና እርካታ ያለውን ተመልከቱ “ደስታ ምን እንደሆነ አላውቅም ..ህይወት፣ ነፃነት እና ደስታን ማሳደድ? ደስታን እፈልጋልሁ.. በመንገድ ላይ እየሄድኩ የሰዎችን ፊቶች እመለከታለሁ። ደስታን ስትሹ ግን የማይጨበጥ ነገር እየፈለጋችሁ አይደለም?” ስኬት አንዱ ክፍል ነው ግን ለህይወት እርካታ ዋስትና አይደለም። ሁሉንም ግቦቻችሁን አሳክታችሁም ከራሳችሁ ጋር ስላም ላትሆኑ ትችላላችሁ። እንዴት ነው ግቦቻችሁ አሳክታችሁ እርካታ የማይሰማችሁ? በተወሰነ መጠን እርካታ ቢሰማችሁም ግን “የበለጠ ሊኖር ይችላል?” ብላችሁ ታስባላችሁ።

  • ስኬታማ እና የረካ?

አብዛኛዎቹ ሳይኮሎጂስቶች እና ሳይካትሪስቶች ሙሉ ሰውን የማሳደግን አስፈላጊነት እያዩ ናቸው፡ አካላዊ፣ ሳይኮሎጂያዎ እና መንፈሳዊ፡ እውነተኛ እርካታን ለማግኘት። በአብዛኛው ለስኬት በምናደርገው ትግል መንፈሳዊ እድገታችንን ወደ ጎን በመተው በአካላዊ እና ሳይኮሎጂያዊ እድገታችን ላይ ትኩረት እናደርጋለን።

በቅርብ ጊዜ አንድ የአማካሪዎች ህብርት በጣም ስኬታማ የሆኑ መሪዎችን ቃለ መጠይቅ በማድረግ ለእነዚህ መሪዎች የስኬት ትርጉም ምን እንደሆነ ለማወቅ ጥረት አድርገው ነበር። የጠየቆቸው ጥያቄዎች መንፈሳዊ ክፍልንም የሚመለከቱ ናቸው፡ “እምነት እና መንፈሳዊ እሴቶች በህይወታችሁ ምን አይነት ቦታ አላቸው?” በምላሹም 75% የሚሆኑት መንፈሳዊ እሴቶች ለግል እድገት እና ሙያዊ እድገት “ጠቃሚ” ወይም “በጣም ጠቃሚ” ናቸው የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። አንድ ጥቆማ “እነዚህን ማጠናከር ካልተቻለ አብዛኛዎቹ ሌሎች ነገሮች አይሳኩም”። በሚያስደንቅ ሁኔታ ጥቂት መሪዎች በመንፈሳዊው መስክ ግልፅ የሆነ እምነት ነበራቸው። አንድ የሬድዮ ጋዜጠኛም ለፈገግታ “እኔ ቶሎ የምነቃቃ ነኝ ግን የሚያነቃቃኝን ማግኘት አልቻልኩም” ብሎል። እናንተስ? የስኬት ትርጉማችሁ የግል እርካታን ይጨምራል? ስኬትን አግኝታችሀል? ስኬታችሁ ወደ ፊት የሚያጋጥማችሁ አስቸጋሪ ጊዜ መሻገር እንድትችሉ አቅም የሚሆን ነው? የግል እርካታን አግኝታችሀል?

የስኬት መሰላል ላይ ለመውጣት እድሜ ልክ ወደላይ እየወጡ በሚያሳዝን ሁኔታ መሰላሉ የተሳሳት መስላል ሆኖ ማግኘት እንዴት የሚያሳዝን ነገር ነው።

ንፁህ የሆነ እርካታን እንዴት ማግኘት እንደሚቻል የበለጠ መነጋገር ትፈልጋላችሁ? ይህንን ሳይት የሚቆጣጠሩ ሰዎች ከእናንተ ጋር በኢሜል መነጋገር ይፈልጋሉ። ከታች እንደተመለከተው እንድትገናኙዎቸው አበረታታለሁ። ወይም እዚህ ጋር ከአማካሪዎች ጋር መገናኘት ትችላላችሁ። በጣም እንደሚያበረቱቱችሁ እርግጠኛ ነኝ።


ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡


እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡

የእርስዎ ፆታ:
የዕድሜ ክልል:

ተገቢውን አማካሪ እንዲመድብዎት የእርስዎ ፆታ እና ዕድሜ እንጠይቃለን። የአገልግሎት ውሎች & የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ.

እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!