የሁለት አለም ሰውማንነት
እናቴ ካሜሩናዊ ናት፡፡ አባቴ ደግሞ ጣሊያናዊ፡፡ እኔ የተወለድኩት ፈረንሳይ ሲሆን ያደኩት ደግሞ ካናዳ ነው፡፡ በትምህርት ቤቴም ሆነ በሰፈሬ ብቸኛው ክልስ በመሆኔ ጓደኞቼም ስለማይረዱኝ ሁልጊዜ ልዩ እንደሆንኩኝ ይሰማኛል፡፡ ህብረተሰቡ በሚያስቀምጠው የትኛውም የማህበረሰቡ ጎራ ውስጥ አልመደብም፡፡ በትምህርት ቤቴ ውስጥ ያሉት ነጮች ጥቁር እንደሆንኩ እንዲሰማኝ ያደርጉኛል እና ከጥቁሮቹ ጋር ደግሞ ስሆን ነጭ እንደሆንኩኝ ይሰማኛል፡፡ በተለየ ክፍል ውስጥ ለብቻዬ እንዳለሁ ይሰማኝ እና እጨነቃለሁ፡፡ እንደዚህ አይነት አስቀያሚ ሰሜት እንዳለው ማንም አልነገረኝም፡፡ እንደተጠላሁ ተሰማኝ፡፡ ተፈላጊ እንዳልሆንኩ እና ከሌሎች ጋር እኩል እንደማልታይ አስባለሁ፡፡
ተፈላጊ እንዳልሆንኩ እና ከሌሎች ጋር እኩል እንደማልታይ አስባለሁ፡፡
በዚህ አስተሳሰቤ ምክንያት ትምህርት ቤት ውስጥ በጣም ነበር የምረበሸው ምክንያቱም ቦታዬን ማግኘት አልችልም፡፡ የክፍል ጓደኞቼም እኔ የተለየሁ እንደሆንኩ እለት እለት እኔን ከማስታወስ አይቆጠቡም፡፡ አንዳንዴ በፀጉሬ፣ አንዳንዴ በስሜ ወይም በማንነቴ ብቻ ምን አለፋችሁ እኔን ላይ መሳቅ ይወዳሉ፡፡ ማንነቴ ሁሌም ጥቃት ላይ ነበር፡፡ “ለምን እኔ? ምን ስላደረኩ?” ብዬ እራሴን ስጠይቅ አስታውሳለሁ፡፡
ልጅ ሆኜ ይደርስብኝ የነበረው ማብሸቅ እና ኢፍትሀዊነት ማንም ሳያርመው ከመቅረቱም በላይ አንዳንዴም በሳቅ አጀብ በአንዳንዶች ዘንድ ይወደሳል፡፡ “ለምን እኔ? ምን ስላደረኩ?” ብዬ እራሴን ስጠይቅ አስታውሳለሁ፡፡ እጅግ የከፋ ብቸኝነት ይሰማኛል እና ስለ ህልውናዬ እራሱ እጠራጠራለሁ፡፡ “ለስቃይ ብቻ ከሆነ የምኖረው ለምን እኖራለሁ?” ብዬ አስባለሁ፡፡ በሂደት ጥላቻ በልቤ ውስጥ አደገ፡፡ ጥላቻ እና ጭካኔ በሰው ልጅ የተለመዱ የመከላከያ ዘዴዎች ናቸው፡፡ ተፈጥሮአዊ ነው፡፡ ሰበዓዊም ነው፡፡ ነገር ግን ፍቅር ከጥላቻ ይልቅ ጠንካራ መሆኑን እና “ተጠቂ” መሆን እንደሌለብኝ የተረዳሁ ቀን ነገሮች መቀየር ጀመሩ፡፡ ቆንጆ የሚያደርገኝን ልዩነቴን መቀበል ቻልኩኝ ነገር ግን ይህንን ማድረግ እንድችል ከቤተሰቦቼ እና ከጓደኞቼ ጥንካሬን እና ድጋፍን እፈልግ ነበር፡፡
ከተለያዩ ማህበረሰቦች እና የተለየ አስተዳደግ ካላቸው ሰዎች ጋር ሃሳብ መጋራት እና ማውራት ስጀመር በልዩነት ውስጥ ምን ያህል መልካም እሴት እንዳለ ስገነዘብ እራሴን መቀበል እንድችል አስተማረኝ፡፡ ይህ ተሞክሮ እኔን በመቀየር ስብዕናዬን ማጎልበት እንድችል ረዳኝ፡፡ የሚያጋጥመን እያንዳንዱ ፈተና ለአላማችን እያዘጋጀን እንደሆነ እረዳለሁ፡፡ ሁሉም ነገር የሚሆነው በምክንያት ነው፡፡
ልዩ እንደሆናችሁ የሚሰማችሁ ከሆነ ወይም በማንነታችሁ ሰዎች እንደማይቀበሏችሁ የምታስቡ ከሆነ እኛን ለማናገር ጊዜ አይወሰዱ፡፡ ይህንን ለብቻዎት መጋፈጥ የለቦትም፡፡ ከታች ያለውን ፎርም ይሙሉ እና ከእኛ አንድ ሰው በተቻለ ፍጥነት መልስ ይሰጦታል፡፡ ሚስጥርዎ የተጠበቀ እና ሁልጊዜም በነፃ የሚሰጥ አገልግሎት ነው፡፡ አማካሪዎቻችንን ባለሙያዎች አይደሉም፡፡ ሰዎችን በመንገዳቸው በሀዘኔታ እና በማክበር ለማገዝ ፍቃደኛ የሆኑ ተራ ሰዎች ናቸው፡፡ እባክዎ ከእርሶ ጋር ግኑኝነታችን እንዲቀጥል ከስር ያለውን ፎርም ይሙሉ፡፡ ካልተጠቀሰ በስተቀር ሁሉም መምሏት ይጠበቃል፡፡
ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡
እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡
እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!