የገንዘብ ማጣት

የአለማችን ደሀው ሰው እኔ አይደለሁም፤ መቼም አልሆንም፡፡ ቤተሰቤ ሳይበላ የሚያልፈው ምግብ የለም፤ ጥሩ ቤት አለን እና አልፎ አልፎ ለመዝናናት የሚያስችለን ገንዘብም አለን፡፡ በሀገራችንን ሁኔታ መካከለኛ ገቢ ከሚያገኘው የህብረተሰብ ክፍል እንመደባለን፡፡ ነገር ግን ለብዙ ወራት የገንዘብ ሁኔታችን አሳስቦኝ ብዙ የጨለሙ ለሊቶችን አሳልፌለሁ፡፡የጭንቀቴ ትልቁ ክፍል ገና እየተቋቋመ ባለ ለትርፍ ባልተቋቋመ ድርጅት ውስጥ መስራቴ እና ደሞዜ ድርጅቱ በሚያገኘው ገቢ ላይ የተንጠለጠለ መሆኑ ነው፡፡ የዚያን ጊዜ ገንዘብ የምንጠይቀው ለመልካም ስራ ቢሆንም የእኔ ደሞዜ ተገማች አይደለም፡፡ በተጨማሪም ባለቤቴ አራት ልጆቻችንን የምታሳድግ የቤት እመቤት ናት፡፡ ያለምንም ጥያቄ ያለንበት ሁኔታ ከመረጥነው ምርጫ የመነጨ ነው፡፡ ስለምርጫችን ሁለታችንም በደንብ እንስማማለን እና ማድረግ ያለብንን ሁሉ እናደርጋለን፡፡ ነገር ግን ይህ ጭንቀታችንን ሊያስወግድልን አልቻለም ነበር፡፡

በወራት ውስጥ የቁጠባ ሂሳባችን ውስጥ ያለውን ገንዘብ ጨርሰን ከባንክ ባገኘነው ብድር መተዳደር ጀመርን፡፡ አንድ ቀን ሁኔታው በጣም ገባኝ እና ብድራችንን ማስላት ጀመርኩኝ (ቤት ለመግዛት ከተበደርነው ውጪ) በብዙ መቶ ሺህዎች ሚገመት እዳ ነበረብን፡፡ ቀዝቃዛ ውሃ ፊቴ ላይ የተቸለሰብኝ ይመሰል አስበረገገኝ፤ማለፍ የሌለብንን መስመር አልፈናል፡፡ ቁጥሮቹን እያሰላሁ መጨነቅ ጀመርኩኝ፤ገቢያችንን እና ወጪያችንን በወረቀት ላይ እያሰፈርኩ በተደጋጋሚ ለማስማማት እሞክራለሁ፡፡ የመጨረሻውን ትንሽ ወጪ በማውጣት እንዴት ወጪያችንን ማሻሻል እንደምንችል አሰላለሁ፤የዚህ ወር ወጪያችን ስንት ነው? በሚቀጥለው ወር ይቀንስልን ይሆን? በሆነ ተዓምር ትርፍ ገቢ ካገኘን የትኛውን ብድር ነው ቀድመን መክፈል ያለብን?

ቁጥሮቹን እያሰላሁ መጨነቄን ቀጠልኩኝ፤ ገቢያችንን እና ወጪያችንን በወረቀት ላይ እያሰፈርኩኝ በተደጋጋሚ ለማስማማት እሞክራለሁኝ፤ የመጨረሻውን ትንሽ ወጪ በማውጣት እንዴት ወጪያችንን ማሻሻል እንደምንችል አሰላለሁ፤

ገንዘብ ነክ በሆነ ነገር ሌሎች ሰዎች ላይ መደገፍን እጠላለሁ፤እኔ እራሴን የቻልኩ ሰው ነኝ፤ ቤተሰቤን ማስተዳደር በመቻሌ የምኮራ ሰው ነኝ፡፡ በዚያን አመት ግን የምፈልገውን ያህል ለቤተሰቤ ማድረግ ስላልቻልኩኝ ከፍተኛ ጫና ይሰማኝ ነበር፤ያ ጊዜ ለእኔ አሳፋሪ እና አስቸጋሪ ወቅት ነበር፡፡ ቁጥሮቹን እያሰላሁ መጨነቄን ቀጠልኩኝ፤ ገቢያችንን እና ወጪያችንን በወረቀት ላይ እያሰፈርኩኝ በተደጋጋሚ ለማስማማት እሞክራለሁኝ፤ የመጨረሻውን ትንሽ ወጪ በማውጣት እንዴት ወጪያችንን ማሻሻል እንደምንችል አሰላለሁ፤እናም ከልጆቼም ጋር ባለኝ ግኑኝነት ይገለጥ ጀመር፡፡ እኔ በጣም የነፃነት ሰው ነኝ፤ መዝናናት እና መቀለድ የምወድድ፣ እንዲሁም ከልጆቼ ጋር ባለኝ ግኑኝነት ቀለል ያልኩኝ አባት ነበርኩኝ፤ አሁን ግን ትንሽ ነገር በጣም ያበሳጨኝ ጀምሯል፡፡ከእነርሱ ጋር ባለኝ ግኑኝነት ምንም ትዕግስት የለኝም፤ምንም ሳያጠፉ ዝም ብዬ እጮህባቸዋለሁ፤አንዳንዴ ባለቤቴ ወደሌላ ክፍል ወስዳቸው “ዛሬ አባታችሁን አታስጨንቁት እርሱ ጥሩ ስሜት ውስጥ አይደለም ብላ ስትመክራቸው እሰማለሁ”፡፡

በዚህ መልኩ የገንዘብ ችግር እኔና ቤተሰቤ ላይ ተፅዕኖ እንዲፈጥር መፍቀድ አስፈላጊ አልነበረም፤ ማለቴ ገንዘብ አሁን ተፅዕኖ የፈጠረብኝን ያህል ተፅዕኖ ይፈጥርብኛል ብዬ አስቤ አላውቅም ነበር፡፡ ገንዘብ አለቃዬ ወይም የሚቆጣጠረኝ ነገር መሆን አልነበረበትም፡፡ እኔ ነኝ አለቃው፤ለልጆቼም ማስተማር የምፈልገው ይህንን ትምህርት ነው፡፡ ነገር ግን አሁን እዩኝ ገንዘብ አለቃዬ ሆኗል፤ ቢያንስ ሀሳቤን፣ መንፈሴን እና አስተሳሰቤን ተቆጣጥሮታል፤ በዚህም ምክንያት ለልጆቼም ሊከተሉት የሚገባ መልካም ትምህርት እያስተማርኳቸው አይደለም፡፡

ባለቤቴ እኔን የሚያስጨንቀኝን ያህል እንዳያስጨንቃት በማሰብ አንዳንድ ያለንበትን የገንዘብ ችግር ጡዘት አልነግራትም፤ እኔን በጣም እያስደነገጠኝ ያለ በመሆኑ ለምን ሁለታችንም እንደንግጥ ብዬ ትቼዋለሁ፤ ይሁን እንጂ በምን ምክንያት እንደምጨነቅ እና ሰላም እንደማጣ ታውቃለች፡፡

ለትርፍ ባልተቋቋመው ድርጅት ውስጥ በመስራት መቀጠል እንዳለብኝ እና እንደሌለብኝ ጠየቀችኝ፤በእርግጥ ሌላ ቦታ ብሰራ የተሻለ እና የማያቋርጥ ገቢ እንደማገኝ አውቃለሁ፡፡ የሚያጋጥመን የገንዘብ ችግር ቢኖርም ግን በዚህ ድርጅት የመስራት ቁርጠኝነት እንዳለኝ ታውቃለች፤ስለዚህ ጭንቀቴን ከእርሷ መደበቅ ነበረብኝ ምክንያቱም እሷን ማስጨነቁ እኔን የበለጠ ያስጨንቀኛል፤ምንም እንዳልተፈጠረ ለማስመሰል እሞክራለሁ፤ገር ግን ምንም ደህና እንዳልሆንኩኝ በሂደት ይታወቃል፤ ምንም ደህና አልነበርኩም፡፡ ፈጠነም ዘገየም ምንም ትርፍ በሌለው ምክንያት አንዱ ልጄ ላይ እጮሀለሁ ወይም በጣም ስሜቴ ተረብሾ እቀመጣለሁ፡፡

ከዛ በኋላ ግን የገንዘብ ችግራችን እየተሻሻለ መጣ፤ለትርፍ ያልተቋቋመው ድርጅት በገንዘብ ረገድ ራሱን እየቻለ እና የተሻለ እየሆነ መጣ፡፡ ከጨለማው ባሻገር የብርሃን ጭላንጭል ይታየን ጀምሯል፤ ይሁን እንጂ እስከ አሁን ጨለማውን አልተሻገርንም፤አሁንም መክፈል ያለብን ሂሳብ እና ብድር አለብን እና አንዳንዴ በየወሩ የምንከፍለውን እዳ በጊዜው መክፈል አንችል ይሆን ብዬ እፈራለሁ፡፡

ያ አመት በጣም ከባዱ አመቴ ነበር፤ ግን ባህሪዬን በጥሩ ሁኔታ ቀርፆልኛል፤ ለማወጣው ወጪ በጣም እንድጠነቀቅ እና ሀላፊነት እንዲሰማኝ አድርጎኛል፡፡ ምን ያህል ጭንቀትን ጤነኛ ባልሆነ መልኩ እየተጋፈጥኩት እንደነበር አስተውያለሁ፤እና የሰዎች ልግስና ልክ አጠገባቸው ሆኜ ስላየሁ እኔም በጣም ለጋስ ሰው ሆኛለሁ፡፡ ስለገንዘብ ጭንቀት ተውጣችሁ ከሆነ እኛን ያናግሩን፤የገንዘብ ጭንቀት በሁሉም ቦታ አብሯችሁ የሚሄድ ጥላችሁ ሊመስላችሁ ይችላል፤ነገር ግን ለብቻዎት መጋፈጥ የለቦትም፡፡ አድራሻችሁን ከስር ብታስቀምጡልን ከእኛ መሀል አንድ ሰው ወዲያው ያገኞታል፡፡ይህንን ለብቻዎት መጋፈጥ የለቦትም፡፡ ከታች ያለውን ፎርም ይሙሉ እና ከእኛ አንድ ሰው በተቻለ ፍጥነት መልስ ይሰጦታል፡፡ ሚስጥርዎ የተጠበቀ እና ሁልጊዜም በነፃ የሚሰጥ አገልግሎት ነው፡፡ አማካሪዎቻችንን ባለሙያዎች አይደሉም፤ሰዎችን በመንገዳቸው በሀዘኔታ እና በማክበር ለማገዝ ፍቃደኛ የሆኑ ተራ ሰዎች ናቸው፡፡ እባክዎ ከእርሶ ጋር ግኑኝነታችን እንዲቀጥል ከስር ያለውን ፎርም ይሞሉ?ካልተጠቀሰ በስተቀር ሁሉንም መሙላት አለቦት።

ፎቶ በ: Fraser West

ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡


እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡

የእርስዎ ፆታ:
የዕድሜ ክልል:

ተገቢውን አማካሪ እንዲመድብዎት የእርስዎ ፆታ እና ዕድሜ እንጠይቃለን። የአገልግሎት ውሎች & የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ.

እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!