የሚያዘግም ጨለማ
ከዚህ በፊት የድብርት ህክምና ክትትል አድርጌ አውቃለሁ፡፡ ህይወቴ ምንም ለውጥ የለውም፡፡ በስራዬም ሆነ በቤተሰቦቼ ላይ ትኩረት ማድረግ አልቻልኩም፡፡ አዕምሮዬ በጥቁር ደመና እንደታጠረ ይሰማኛል፡፡ በቃ የየእለት ተግባሬ መብላት፣ መተኛት፣ ማውራት እና መስራት ብቻ መሆኑ ትልቁ ተግዳሮቴ ነበር፡፡
የድብርት አስፈሪው ገፅታ ጭንቅላትን ቀስ በቀስ መቆጣጠሩ ነው፡፡ የሚታዩብኝን ምልክቶች አላስተውልም ነበር፤ ያለምንም ምክንያት ይደክመኛል ፣ ቶሎ እናደዳለሁ፣ መተኛት አልችልም፣ ሁሉን አቀፍ ግራ መጋባት ይሰማኛል እና በሀሳብ እሰጥማለሁ፤ እኚ ሁሉ በድብርት የመያዝ ምልክቶች ናቸው፡፡
አንድ የማውቀው ነገር በአዲሱን ስራዬ የእኔ ሀላፊነት ምን እንደሆነ ስላልተረዳሁኝ ወደ ቢሮዬ መሄድ በጣም እንደምጠላ ነው፡፡ በተደጋጋሚ በፍርሃት ስሜት እዋጣለሁ፡፡ ወደ ቤት ስመለስ ከስራዬ የምባረር እና የቤተሰቤን የገቢ ምንጭ የማጣ ስለሚመስለኝ እጨነቃለሁ፡፡ ይህ ድብርቴ እንዲባባስ አድርጎታል፡፡ በአብዛኛው ለሊት አልጋ ላይ ሆኜ አልተኛም፤ ጭንቅላቴ እርፍት በማጣት ውስጥ ነው፤ እውነት ያልሆኑ የፈጠራ ሃሳቦችን አስባለሁ፡፡ እንቅልፍ ማጣቴ ደግሞ የሚቀጥለው ቀን የባሰ መጥፎ እንዲሆንብኝ ያደርጋል፡፡ ይህ ነበር የሚደጋገምብኝ፡፡
የሚሰማኝ ሀዘን መውጫ የሌለው ነው፡፡
የድብርቴ ምክንያት በሰዓቱ ግልፅ አልነበረም፡፡ አሁን ግን ነገሮችን ተመልሼ ሳይ በተለያዩ ሰበቦች ምክንያት ይመስለኛል፣ በጣም የምቀርባቸው አጎቴ እና ልጁ ድንገተኛ ሞት ምክንያት ጭምር ይመስኛል፡፡ የሚሰማኝ ሀዘን መውጫ የሌለው ነው፡፡ እራሱን የቻለ ሰው በመሆኔ ፣ ባል በመሆኔ ፣ አባት በመሆኔ፣ እና ለቤተሰቦቼ ብቸኛ ልጅ በመሆኔ ለቤተሰቤ ስል ጠንካራ በመሆን ወደ ስራ መመለስ ነበረብኝ፡፡
በተመሳሳይ ጊዜ በቤተሰቤ ላይ ሌላም ተግዳሮቶች ነበሩ፡፡ እናቴ ከእድሜዋ አንፃር ህይወቷን ሊያሳጣት የሚችል በሽታ ነበረባት፡፡ በተመሳሳይ ሰዓት የባለቤቴ እናት ሁለት የቀዶ ጥገና ህክምና ሊደረግላት ወደ ሆስፒታል ገብታ ነበር፡፡ ከሁሉም በላይ እኔ አዲስ ስራ ጀምሬ ነበር እና ስራውን የመልመድ ጫናው በጣም አስጨንቆኝ ነበር፡፡
እራሴን ለማጥፋት መዘጋጀት ጀመርኩኝ ነገር ግን ያለእኔ ቤተሰቤ ምን ይሆናል የሚለው ሀሳብ ወደኃላ ያዘኝ፡፡ የቤተሰቤ የቅርብ ዘመድ ሃኪም ነበርች እና የህክምና ክትትል እንዳደርግ መከረችኝ፡፡ ወደ አንድ የህክምና ባለሙያ ሄጄ የሰጠኝ የመድሀኒት መደራረብ ችግሬን አባባሰብኝ፡፡ ይህ የበለጠ ግራ እንዲገባኝ አደረገ፡፡ ሊሻለኝ ሲገባ ለምንድነው እየባሰብኝ ያለው?
ሌላም ሀኪም ሳይካትሪስት እንዳማክር ነገረኝ፡፡ ሳይካትሪስቱም በደንብ አዳምጦኝ ሌላ መድሀኒት እንድጀምር አደረገኝ፡፡ ይህ ሀኪም በጣም ታጋሽ ነው እና ሁሉም የሚሰማኝን ነገር አውጥቼ ነገርኩት፡፡ ቀስ በቀስ ደህና ስሆን ተሰማኝ፡፡ የህክምና ክትትሉ ለጥቂት ወራት ቀጠለ፤ እኔም ሀኪሙም ህክምናው እንደሚበቃኝ እስከምናረጋግጥ ድረስ፡፡
በብዛት የማይሰማኝን ነገር ሲሰማኝ ተሰማኝ፤ ተቀባይነት፡፡
በዚህ ጊዜ ባለቤቴ በመንፈሳዊ ህብረት ውስጥ ገብታ ነበር እና አብሬት እንድሄድ ትጋብዘኝ ነበር፡፡ በቸልተኝነት እርሷን ለማስደሰት በተከታታይ እሄድ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች እኔን እንዴት መረዳት እንደሚችሉ አልታየኝም ነበር፡፡ ነገር ግን የተወሰነ ጊዜ ከተከታተልኩኝ በኃላ በብዛት የማይሰማኝን ነገር ሲሰማኝ ተሰማኝ፤ ተቀባይነት፡፡ በሚቀበሉኝ ሰዎች ቡድን ውስጥ ስሆን ትክክለኛውን ዋጋዬን አገኘሁት፤ እንደ ሰው፣ እንደ ባል፣ እና እንደ አባት፡፡ አሁን ልጆቼ እና ባለቤቴ በእኔ ውስጥ ያላቸውን ዋጋ እንዲያውቁ እተጋለሁ፡፡
በድብርት ውስጥ እንደሆናችሁ ከተሰማችሁ ብቻችሁን መንገዱን መራመድ የለባችሁም፡፡ድብርት ሁሌም ወደ ብቸኝነት ይመራል ነገር ግን ተስፋ መቁረጥን ትተን የብቸኝነትን ተቃራኒ ማድረግ አለብን ፡፡ ወደሚሰሙን ሰዎች ሄድን ስለህመማችን መናገር አለብን፡፡ የዛን ጊዜ ሰዎች ሲቀበሉን ትክክለኛውን ዋጋችንን እናውቃለን፡፡
Through this website, there are free and confidential mentors ready to listen to your story and to support you without judgement. If you fill in your info below, you'll hear back from a mentor soon. You can use your real name or a fake one. It's completely up to you.
ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡
እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡
እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!