የእዳ መክፈያ ጊዜ ደረሰ

እኔና ባለቤቴ የተዋወቅነው ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችንን እየተከታተልን ባለንበት ሰአት ነበር፤ ከዩኒቨርሲቲ እንደተመረቅን እና ስራ እንደያዝን ለመጋባት ስንወስን በእጃችን ላይ ለሰርጋችን የሚሆን በቂ ገንዘብ አልነበረንም፤ በመሆኑም እቁብ በመሰብሰብና ከምናውቃቸው ሰዎች ብድር ተበድረን ወደ አምስት መቶ ሺ ብር ያህል አግኝተን የስርግ ስነ ስርአታችንን ፈጽመን ተጋባን። በጣም የሚያሳዝነው ነገር ግን በሰርጋችን ማግስት ብራችንን አሟጠን ጨርሰን ስለነበር ወጣ ብለን እንኳን የጫጉላ ጊዜአችንን ማሳለፍ አልቻልንም ነበር።

በወጥመድ እንደተያዝኩኝ እና ገንዘቤን መቆጣጠር እንዳልቻልኩኝ ተሰማኝ፤

አንድ ቀን ቤት ውስጥ አስቤዛ አልቆ ስለነበር ወደ ገበያ ወጥቼ የሚያስፈልጉንን ቁሳቁስ ለመግዛት ፍለጌ ነበር ፤ በጣም የሚያስገርመው ደግሞ እዳችንንም የምንክፍልበት ጊዜው ደርሶ ነበር፤ ይሁን እንጂ አካውንታችን ውስጥ ምንም ቤሳ ቤስቲን አልነበረንም፤ ከዛም ለባሌ ነግሬው ማልቀስ ጀመርኩኝ፤ ቀድሞ የተበደርነውን ብድር ስላልከፈልን ሌላ ብድር እንኳን ማግኘት አልቻልንም፤ ሌላው ቀርቶ የበላነውን እቁብ እንኳን መክፈል አልቻልንም በወጥመድ እንደተያዝኩኝ እና ገንዘቤን መቆጣጠር እንዳልቻልኩኝ ተሰማኝ፤ በዚያን ሰዓት ችግር ውስጥ እንዳለን አወኩኝ፡፡

ከዚህ ችግር መውጣት አለብን፤የእስከ አሁኑ ይበቃል፤ ከዚህ ሁሉ በኋላ የብድር አማራጮችንን ላለመጠቀም ወሰንን፤ በምትኩ ወጪያችንን ለመቀነስና በወር ክምናገኘው ገቢ መቆጠብ እንዳለብን ተስማማን፤ በጣም ከባድ ነበር፤ ነገር ግን ቀስ በቀስ እዳችንን መክፈል ጀመርን፡፡ ትንሽ ብር ለመክፈል ረዥም ጊዜ ይወስድብናል፤ ግን መክፈላችንን አላቆምንም፡፡ ለራሳችንን ከቆፈርነው ጉድጓድ ቀስ በቀስ መውጣት ጀምረናል፤ ግን አሁንም ወጥተን አልጨረስንም፡፡ ስለብድራችን ሳስብ መቼም ከፍለን የምንጨርሰው አይመስለኝም ነበር፤ ለአራት አመታት በወጥመድ ውስጥ ከቆየን በኋላ ያገኘነውን ገንዘብ ሁሉ እዳ ለመክፈል አውለን በስተመጨረሻም እዳው ከላያችንን ላይ ሲነሳ የተሰማኝን ነፃነት ልነግራችሁ አልችልም፡፡

በገንዘብ ወጥመድ እንደተያዛችሁ ካሰባችሁ እና እንዴት እንደምትወጡት የማታውቁ ከሆነ እኛን ያናግሩን፡፡ ለብቻዎት አይደሉም፡፡ ለማውራት ከፈለጉ እኛ እዚህ አለን፡፡ ይህንን ሸክም ለብቻዎት መሸከም የለቦትም፡፡ይህንን ለብቻዎት መጋፈጥ የለቦትም፡፡ ከታች ያለውን ፎርም ይሙሉ እና ከእኛ አንድ ሰው በተቻለ ፍጥነት መልስ ይሰጦታል፡፡ ሚስጥርዎ የተጠበቀ እና ሁልጊዜም በነፃ የሚሰጥ አገልግሎት ነው፡፡ አማካሪዎቻችንን ባለሙያዎች አይደሉም፤ሰዎችን በመንገዳቸው በሀዘኔታ እና በማክበር ለማገዝ ፍቃደኛ የሆኑ ተራ ሰዎች ናቸው፡፡እባክዎ ከእርሶ ጋር ግኑኝነታችን እንዲቀጥል ከስር ያለውን ፎርም ይሞሉ? ካልተጠቀሰ በስተቀር ሁሉንም መሙላት አለቦት፡፡

ፎቶ በ: Thomas Leuthard

ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡


እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡

የእርስዎ ፆታ:
የዕድሜ ክልል:

ተገቢውን አማካሪ እንዲመድብዎት የእርስዎ ፆታ እና ዕድሜ እንጠይቃለን። የአገልግሎት ውሎች & የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ.

እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!