ትክክል ይመስል ነበር

የክፍሉ ሌላኛው ጥግ ላይ ብቻውን ተቀምጧል፤ የመጨረሻ አመት ተማሪ እያለው ክፍላችን የገባው አዲሱ ልጅ። ላየው ዞር ስል አይኖቻችን ተገጣጠሙ እና ወዲያው የተሰማኝ ስሜት በጣም አስገረመኝ። አይኔን ጨፈንኩ እና ፊቴን አዞርኩ። ስለዚህ ጓደኞቼን ሰብስቤ ጥሩ መሆን እንዳለብን እና ሄደን ሰላም ማለት እንዳለብን ነገርኳቸው። ከእኛ ቡድን ጋር አብሮ መዋል ጀመረ እና ተቀበሉት። ግን አብረን የእግር ጉዞ የምናደርገው ወይም ክፍላችን ጥግ ላይ ተቀምጠን የምናወራው ሁለታችን ብቻ እንሆናለን። በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ቆንጆ እንደሆንኩ ተሰማኝ። የፀሀይ ብርሃን አለሜን ሸፈነው።

በመጀመሪያ በደንብ ይንከባከበኝ ነበር። ሁሉም ጓደኞቼ አብረን እንዴት እንደምናምር ይነግሩን ነበር። ይወደኝ ነበር እና የምወዳቸውን ነገሮች ማድረግ ይፈልግ ነበር። ትናንሽ ስጦታዎችን ይገዛልኝ ነበር እና ጊዜ ጠብቆ የሚስመኝ ልቤን ያቀልጠው ነበር። በእርግጥ መቼም የማላዳርጋቸውን ነገሮች እንዳደርግ ያሳምነኝ ነበር ግን እሱን ለማስደሰት ስል አደርጋቸው ነበር። ከእሱ ጋር መሆን ደስታን ይፈጠርልኛል። ሁሉም አብረን እንደሆንን ያውቁ ነበር። አብረን የማንሆንባቸው ጊዜያት በጣም ጥቂት ነበሩ።

ከዛ የሚያስፈራው ጥያቄ መጣ - ብቻዬን መሆን ፈልጋለሁ።

ከዛ ነገሮች መለወጥ ጀመሩ። በመጀመሪያ አልታወቀኝም ነበር ወይም ምልክቶቹን ላለማስተዋል ፈልጌ ነበር ማለት ይቻላል። አንዳንዴ አንድ ሰዓት አርፍዶ ይመጣ እና ይቅርታ እየጠየቀ ያመሻል። አይኑ ስር ያሉት ጥቁር መስመሮች በትምህርት ጫና ነው ይለኛል። ሌላ ጊዜ ደግሞ በሃሳብ ሌላ ቦታ ይሄድና ሃሳቡን ወደ እኔ እንዲመልስ አደርገዋለሁ። ከዛ የሚያስፈራው ጥያቄ መጣ - ብቻዬን መሆን ፈልጋለሁ። ሰጠሁት። ለጊዜው ነው ብዬ አስቤ ነበር። ሁላችንም በጭንቀት ውስጥ እናልፋለን እና ልረዳው ብፈልግም፣ ብቻዬን መሆን ፈልጋለሁ ስላለኝ ልጫነው አልፈለኩም። ያ እንዳያስጨንቀኝ ለማድረግ ሞከርኩ ግን ሃሳቤን ያዘው። ሌሊት ላይ ለእኔ ያለውን ስሜት ምን እንደለወጠው ምን ብዬ መጠየቅ እንዳለብኝ ባለማወቅ ውስጥ ሆኜ ትራሴን አቅፌ ሳለቅስ ራሴን አገኘኋለሁ።

ብዙ ጊዜ ጎኔ አልነበረም። በመጀመሪያ ቀስ እያለ ከህይወቴ ሲወጣ አየሁ፤ ከዛ ልክ ሸርተቴ ወደ መጨረሻው ላይ ሲደረስ በፍጥነት ተወርዶ እንደሚያልቀው ተጨነቄ እያለሁ ጠፋ። ግራ ገብቶኛል። ተጠልቻለሁ። በጭንቀት ውስጥ ነኝ። ምንድን ነው ያደረኩት? ጓደኞቼ ከሌላ ሴት ጋር እንዳዩት ይነግሩኝ ጀመረ። ሲነግሩኝ መልካም አስበው እንደሆነ አውቃለሁ ግን በእውነት ማወቅ አልፈልግም ነበር።

ከሁለት ወር በኋላ ብቻዬን መሆን ስፈልግ የምቀመጥበት ቦታ ጋር መጣ እና ማውራት እንችል እንደሆነ ጠየቀኝ። አላወኩትም ነበር። ቆዳው ነጥቷል እና አይኑ ጎድጉዷል። በጣም መቀራረባችን እንዳስፈራው ግን ያለ እኔ መሆን ከባድ እንደሆነ ነገረኝ። ተመልሰን አንድ ላይ ሆንን እና ነገሮች መጀመሪያ ላይ ስንገናኝ እንደነበሩት ሆኑ። ለተወሰነ ጊዜ። ከዛ የበፊት ነገሮች መፈጠር ጀመሩ። አሁን ጊዜው ነበር፤ እኔ ነኝ ትቼው የሄድኩት። አንድ ታዋቂ የሀገር መሪ እንዲህ አለ “አንዴ አሞኘኝ፤ እፍረቱ ለአንተ ነው። ለሁለተኛ ጊዜ አሞኘኝ፤ እፍረቱ ለእኔ ነው።”

ከሶስት ወራት በኋላ ቤቴ መጣ። በመጨረሻ ተናዘዘ። ሱስ ውስጥ እንደነበረ እና ይሄን ሁሉ ጊዜ ሁለተኛዋ ሴት እኔ እንደሆንኩ ነገረኝ። እኔ ጥሩ ስነ ምግባር ስላለኝ እና መልካም ስለሆንኩ ላድነው እንደምችል አስቦ ነበር። ግን የእሷ ጫና እና ሱሶቹ በጣም ጠንካራ ነበሩ። አሁን እርጉዝ ናት። ባይወዳትም ለልጁ ሲባል አብረው መሆን ሊሞክሩ እና አብረው ማገገሚያ ሊገቡ ነው። ለግልጽነቱ እና ጽናቱ የተወሰነ አደነቅኩት።

ትክክል ያልሆነው ወንድ ብዙ ትክክል የሆኑ ነገሮችን አስተማረኝ። ስሜት ለግንኙነት መሰረት ሊሆን አይችልም። ሴክስም እንደዛው። ቀስ ብለው ነው ነገሮች መሄድ ያለባቸው እና አንድ ለመሆን የትኛውንም ውሳኔ ወስኖ ቃል ከመግባት በፊት እርስ በርስ መተዋወቅ አለብን። እንዴት ከራሳቸው እና ከእናንተ ቤተሰብ ጋር እንደሚግባቡ ማየት። እና እውነተኛ እና የቅርብ ጓደኞቻችሁን ስለ እሱ በእውነት የሚሰማቸውን በግልጽ እንዲነግሯችሁ መጠየቅ።

ማንንም ለመቀየር መሞከር አይጠበቅባችሁም። እነሱም ሊቀይሯችሁ አይገባም።

የወደዳችሁት ሰው እንዳይደብረው ብላችሁ እውነተኛ ማንነታችሁን አትደብቁ እና ሁሌም ያኛውን ሰው የሚያስደስተውን ነገር ለማድረግ ወይም ለመናገር ብቻ አይሞክሩ። ይሄ አስመሳይነት ነው። በእውነተኛ ማንነታችሁ ካልወደዷችሁ፤ አይሰራም። ዝም ከማለታችሁ እና ከእንግዳ ባህሪያችሁ አልፈው ማየት ካልቻሉ፤ በእውነት አያስቡላችሁም ማለት ነው። ማንንም ለመቀየር መሞከር አይጠበቅባችሁም። እነሱም ሊቀይሯችሁ አይገባም። ልባችሁ ወደ አንድ ሰው ስለተሳበ ብቻ ከሆናችሁት ውጪ ሌላ ሰው መሆን አትችሉም። ስለ ራሳችሁ መቀየር የምትፈልጉት ነገር ካለ ለራሳችሁ ነው ማድረግ ያለባችሁ። ይሄንን ጫና ሌላ ሰው ላይ ማሳደር አግባብ አይደለም። ከዛም አልፎ ከስንት አንዴ ነው የሚሳካው።

ስለ ራሳችሁ ጥሩ ስሜት የማይሰማችሁ ከሆነ፤ ራሳችሁ ናችሁ መጨረስ ያለባችሁ እንጂ የተሻለ ስሜት እንዲሰማችሁ ሌላ ሰው ላይ መደገፍ የለባችሁም። ለዛም ሰው ሆነ ለራሳችሁ ትክክል አይደለም እና ትክክለኛ ማንነታችሁ የተገለጠ ጊዜ በእርግጠኝነት ሊወዳችሁ አይችልም። የራሱን አመለካከት ለማሻሻል እንደ ጨዋታ ወይም እንደ ቀላል ኢላማ ሊያያችሁ ይችላል። ውጤቱ? አንዳችሁ ምናልባትም ሁለታችሁም መጨረሻችሁ መጎዳት ይሆናል።

ከግንኙነት መቋረጥ ልባችሁ ተሰብሮ ከሆነ ያላችሁት፤ ምን ያህል እንደሚያስጨንቅ እናውቃል። ንዴቱን፣ ከባዱን ብቸኝነት እና ጥርጣሬውን እንረዳችኋለን። ምናልባት አሁን አብራችሁት ያላችሁት ሰው የእኔ አይደለም ብላችሁ ታስቡ ይሆናል። ስለዚህ ማውራት የምትፈልጉት ሰው ካለ፤ ከእኛ መሀል አንድ ምስጢራዊ አማካሪ እዚህ አለሎት። ከታች ያለው ቅጽ ይሙሉ እና በቅርቡ ከቡድናችን አንድ ሰው ያናግሮታል።


ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡


እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡

የእርስዎ ፆታ:
የዕድሜ ክልል:

ተገቢውን አማካሪ እንዲመድብዎት የእርስዎ ፆታ እና ዕድሜ እንጠይቃለን። የአገልግሎት ውሎች & የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ.

እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!