የተፋቱ ወላጆች ልጅ

በአንድ ፀሃያማ ጠዋት ገና ፀሃይዋ መስታወቱ ላይ ስታንፀባርቅ ከእንቅልፌ ተነስቼ በቤት ውስጥ እናቴን መፈለግ ጀመርኩኝ፡፡ በኮሪደሩ ላይ ነጠላ ጫማዋን ባገኘውም እርሷን ግን ማግኘት አልቻልኩም፡፡ ግራ የመጋባት ስሜት ሲሰማኝ እንደነበር አስታውሳለሁ……ገና ከእንቅልፌ በአግባቡ እንኳ አልነቃሁም ነበር፡፡ በሳሎኑና በኮሪደሩ መሃል ቆሜ ሞግዚቴን ሰትጠዳደፍ አየኋት፥ አባቴ ደግሞ ሳሎን ከሚገኘው መደርደሪያ ፊትለፊት ቁጭ ብሎ ከቦርሳው ውስጥ ደብዳቤ መዝዞ በማውጣት ኮስተር ብሎ ሲያነብ ሰማሁት፡፡ ልቤ ቀጥ ስትል ተሰማኝ!! በጊዜው የተሰማኝን ስሜት ሊገልጽልኝ የሚችል የማስታውሰው ቃል የለም። እናቴ ትታን ሄዳለች! ቀጥሎ ያለውን ምንም ማስታወስ አልችልም፡፡ ለምንድነው ማንም ሰው እኔ ምን እንደተሰማኝ ለማወቅ ግድ የሌለው?!.... በጣም ብቸኛ እና ለጥቃት ተጋላጭ ሆንኩኝ፡፡ በዛው ቦታ ላይ በብቸኝነት ስሜት ቆሜ ቀረሁኝ።

በጣም ዝምተኛ ልጅ ሆንኩኝ፤እንደበፊቱ ተጫዋች እና ደስተኛ ልጅ ልሆን አልቻልኩም፤መልስ እፈልግ ነበር፤ “ለምንድነው እናቴ እኔን ጥላ የሄደቸው?” የሚለውን ብቻ ነበር ማሰብ የምችለው፡፡

በትምህርቴ ደካማ ሆንኩኝ፤ሁል ጊዜ እያለቀስኩ ነው የምተኛው፡፡ ያለምንም ተጨማሪ ምክንያት በማንነቴ ብቻ የሚወደኝን ሰው በጣም እፈልግ ነበር፡፡ ይህንን ሁሉ በትንሽዋ አእምሮዬ እንዴት ማሰላሰል እንዳለብኝ አላውቅም ነበር፤ እናም አንድ ቀን ከትምህርት ቤት በተሰጠን በጽሁፍ የሚቀርብ የቤት ስራ ላይ የራሴን ታሪክ እንደ ምንባብ ፃፍኩት፡፡ ጽሁፌን ያነበበችው አስተማሪዬ ለእኔ በጣም መልካም ሰው ነበረች እና ስለ እኔ በጣም በመጨነቅ ወደቤቷ ትጋብዘኝ ነበር፤ሁልጊዜ ፊቷ እስከ አሁን በማስታውሰው ፈገግታ የተሞላ ነው፤ከአመታት በኋላ እንደ እናት የምታስብልኝ ሌላ እናት ሆነችልኝ፡፡

አባቴ በስራው በጣም የሚጨናነቅና ለእኔ ምንም ጊዜ የሌለው ከመሆኑም ባሻገር የሚፈልገውን ነገር ካላደረኩኝ ወይም እርሱ ያልፈቀደልኝን ነገር ካደረኩኝ ግን ጊዜ መድቦ በተደጋጋሚ እየጮኸብኝ ተቀባይነት እንደሌለኝ ከመግለፅ እይቆጠብም፤በትምህርቴ መጥፎ ውጤት ካመጣሁ ደግሞ የከፋ ቅጣት እቀጣለሁ፡፡ አባቴ በተደጋጋሚ ስለሚቀጣኝ ፈሪ ሆንኩኝ ግን ደግሞ አንዳንድ ጊዜ በጣም ጥሩ ሰው ስለሚሆንልኝ ግራ ያጋባኛል፡፡ የምኖረው መኖር በማልፈልገው አይነት ቤት ውስጥ ስልሆነ እናቴ በጣም ትናፍቀኛለች፡፡

እናቴን በድጋሚ ያየኋት ከአባቴ ጋር ከተለያዩ ከአራት አመት በኋላ ነበር፤አንድ ቀን እንደምትመጣ ምንም ሳታሳውቀን በራችን ላይ በድንገት ተገኘች፡፡ ስላገኘኋት ደስ ብሎኝ ነበር፤ ሆኖም ግን በድጋሚ ትሄዳለች የሚል ፍርሃትም ነበረኝ፡፡ ልቤ ቆስሎ ነበር እና ቤተሰቦቼን በድጋሚ ለማመን በጣም ከብዶኝ ነበር፤ አሁንም ደስተኛ እንዳልሆኑ ያስታውቃሉ፤ የተለያየ ክፍል ነው የሚያድሩት፤ሁሌ ይጨቃጨቃሉ፤ አብረው የሆኑበት ምክንያትም እኔ ብቻ እንደሆኑኩኝ አስባለሁ፤ እናቴ ምንም ደስተኛ እንዳልሆነች ታስታውቃለች፡፡

ልቤ ቆስሎ ነበር እና ቤተሰቦቼን በድጋሚ ለማመን በጣም ከብዶኝ ነበር፡፡

ልጅ ሆኜ እናቴ ጥላን እንዳትሄድ ለማድረግ እኔ ብቁ ባለመሆኔ እራሴን እወቅሳለሁ፤በዛን ጊዜ አንድ ሰው አጠገቤ ሆኖ ምን እየተፈጠረ እንዳለ እንድረዳ ቢረዳኝ ኖሮ ጥሩ ነበር ብዬ ተመኘሁ፤ እናቴን ይቅር ማለት በጣም ከበደኝ፤ እንዴት ትታኝ ትሄዳለች? የሚለው ጥያቄ በውስጤ ተብላላ። ልቤ ቆስሎ ነበር እና ቤተሰቦቼን በድጋሚ ለማመን በጣም ከብዶኝ ነበር፡፡

በመበሳጨት እና ለራሴ በማዘን ፈንታ አሁን የማዝነው በእድገቴ ውስጥ ሰላጣኋቸው ነገሮች ነው፡፡

ሳድግ ግን በልጅነቴ ምን እንደተፈጠረ ቀስ በቀስ ይገባኝ ጀመር ፤ በመሆኑም የራሴን የማገገሚያ መንገድ ጀመርኩኝ፡፡ የቤተሰቦቼን የትዳር ህይወት እኔ ማስተካከል እንደማልችል ገባኝ፤አሁን እኔም እናት ነኝ፤ እናም ልጆቼን ትቶ የመሄድን ሃሳብ መቋቋም አልችልም፡፡ እናቴ ለልጇ ያላትን ሰብዓዊ ምላሽ መስጠት ትታ ቆርጣ ጥላኝ እስክትሄድ ድረስ የጨከነቸው በጣም ያንገበገባት ነገር ቢኖር ነው፤ይህንን ማለፍ በጣም ከብዷት እንደነበር አስባለሁ፡፡ ላሳለፍኩት ከባድ የልጅነት ጊዜ ሁሉ እናቴን እወቅሳት ነበር፤አሁን ግን ሁኔታውን የማየው በተለየ መንገድ ነው፡፡ በመበሳጨት እና ለራሴ በማዘን ፈንታ አሁን የማዝነው በእድገቴ ውስጥ ሰላጣኋቸው ነገሮች ነው፡፡ እናቴ ከጎኔ ሆና ያኔ በዚያ በከባድ ወቅት ብትረዳኝ፣ ስፈራ ብታበረታኝ እና አባቴ ሲናደድብኝ አብራኝ ብትሆን ኖሮ ብዬ እመኛለሁ፤ ስምምነት ከሌለበት ቤተሰብ ባልተፈጠርኩ ኖሮ ብዬ እመኛለሁ፡፡ በመበሳጨት እና ለራሴ በማዘን ፈንታ አሁን የማዝነው በእድገቴ ውስጥ ሰላጣኋቸው ነገሮች ነው፡፡

ከወቀሳ ወደ ሀዘኔታ የመሻገሩ ምዕራፍ ክብዙ የምክር ቀጠሮዎች በኋላ እና ያለፈውን ከባድ ሁኔታ ለመጋፈጥ ከመወሰን የመጣ ነው። ብዙ የስነ ልቦና አማካሪዎችን እና ማህበራዊ ሰራተኞችን አግኝቻለሁ፤በእኔ የማገገም ጉዞ ውስጥ ብዙ ሰዎች ጠቃሚ ሚና ተጫውተዋል፡፡ በተለያየ የህይወት ወቅት አዳዲስ እና ከባድ ነገሮች አሉ፤ በመሆኑም በቤተሰቤ ውስጥ ያንን ለመወጣት ነገሮች ተቀያያሪ ሲሆኑ አስተውያለሁ፤ የማገገሚያ መንገዴ ገና እንዳልተጠናቀቀም አውቃለሁ፡፡ በአብዛኛው የማገገሚያ መንገድ የሚጀምረው የምናልፍበትን መንገድ ሁሉ በሀዘኔታ እና በጥበብ ሊያዳምጠን ፍቃደኛ የሆነ ሰው ከማግኘት ነው፤ይህ ነበር በእኔ ህይወት የሆነው እናም ለእናንተም ይህ ሊሰራ ይችላል፤ እዛ ቦታ ላይ ለብቻችሁ መቆም እንደሌለባችሁ እወቁ፡፡

ይህንን ለብቻቹ መጋፈጥ የለባችሁም፥ ከታች ያለውን ፎርም ይሙሉና ከእኛ አንድ ሰው በተቻለ ፍጥነት መልስ ይሰጣችኋል፤ሚስጥርዎ የተጠበቀ እና ሁልጊዜም በነፃ የሚሰጥ አገልግሎት ነው፤ አማካሪዎቻችን ሰዎችን በመንገዳቸው በሀዘኔታ እና በማክበር ለማገዝ ፍቃደኛ የሆኑ መልካም ሰዎች ናቸው፡፡ እባክዎ ከእርሶ ጋር ግኑኝነታችን እንዲቀጥል ከስር ያለውን ፎርም ይሞሉ? ካልተጠቀሰ በስተቀር ሁሉንም መሙሏት ይጠበቃል፡፡


ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡


እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡

የእርስዎ ፆታ:
የዕድሜ ክልል:

ተገቢውን አማካሪ እንዲመድብዎት የእርስዎ ፆታ እና ዕድሜ እንጠይቃለን። የአገልግሎት ውሎች & የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ.

እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!