በጣም የበዛ መልካምነት

አዲስ ነገሮችን መሞከር ወዳለሁ ስለዚህ ሁሌ የማደርገው ነገር አለ። ከብዙ ወራት በፊት ጊዜ ማጣቴ (የምሰራው ነገር መብዛቱ) አስጊ ሁኔታ ላይ ደረሰ። የሙሉ ጊዜ ስራ ከሌላ የትርፍ ጊዜ ቢዝነስ ጋር እሰራ ነበር። በማገገሚያ ፕሮግራም ውስጥ በበጎ ፈቃደኝነት እሳተፋለሁ እና የራሴም ግንኙነቶች አሉ እና ቅዳሜ እና እሁድ ላይ ከቤተሰቦቼ ጋር ለመገናኘት ሞክራለሁ፤ እነዚህ ሁሉ ነገሮች የምወዳቸው ናቸው ግን ሁል ጊዜ የምሰራው ነገር የመኖሩን ጭንቀት ማዳመጥ ጀመርኩ። ከዚያ እንቅልፍ ማጣት ውስጥ ገባሁ። መስራቴን ቀጠልኩ። ሌላ ምን አማራጭ ነበረኝ? ማቆም አልቻልኩም። መስራት ነበረብኝ። ሰዎች ይፈልጉኝ ነበር። ቤተሰቦቼን እና ጓደኞቼን ማግኘትም አለብኝ። አንዳንድ ጊዜ በመድሀኒት እገዛ ነበር የምተኛው ቀን ላይ ደግሞ ተጨማሪ መድሀኒቶች እንድንቀሳቀስ ይረዱኝ ነበር። ሁሌ ማታ ላይ መተኛት አልችልም በሚል ፍርሃት ነው አልጋ ላይ የምወጣው፤ ይሄ ደግሞ ተጨማሪ ጭንቀትን የተጨናነቀው አዕምሮዬ ላይ ጨመረ።

ለእኔ በስራ መወጠር የተለመደ ነገር ነው፤ ስለዚህ ሁሉም ነገር መልካም እንደሆነ በማሰብ፤ ያሉኝን ነገሮች ማድረግ ቀጠልኩ። በጣም ይደክመኝ ነበር። አብረውኝ የነበሩት ሁሉንም ነገር በትክክለኛ መንገድ ለማስኬድ እየሞከርኩ እንደሆነ ያዩ ነበር። ነገሮችን እረሳ ስለነበር ይቅርታ በጣም ጠይቃለሁ። ግን ማንም ጭንቀቴ የቱ ጋር እንደደረሰ አያውቅም ነበር። ወደ ኋላ ዞር ብዬ ሳየው ከቤተሰቦቼ እና ጓደኞቼ ጋር የነበረኝ ቆይታ ብዙ ትዝ አይለኝም። አብዛኛው የህይወቴ ወራት የማያቋርጥ ጭጋግ ሆነው ነው የሚታዩኝ። በጣም ትንሽ እረፍት ብቻ አድርጌ አንዱ ቀን በሌላው ይተካል።

ማቆም አልቻልኩም። መስራት ነበረብኝ። ሰዎች ይፈልጉኝ ነበር።

አይገርምም፤ በጣም ዛልኩኝ። ለብዙ ቀናት በሁለት ሰዓታት እንቅልፍ ብቻ ከርሜ፤ አንድ ቀን ጠዋት ስነሳ ማድረግ የምችለው ማልቀስ ብቻ ሆነ። በጣም ደክሞኝ ነበር። ሌላ ቀን መዋሉን ሳስበው በጣም ደከመኝ። መተኛት ብቻ ነበር የምፈልገው እና አዕምሮዬ ሊፈቅድልኝ አልቻለም።

አማካሪ የሆነች ጓደኛዬን ለማግኘት ሄድኩኝ። አንዳንድ ምርመራዎችን ካደረገችልኝ በኋላ ጭንቀት እንዳለብኝ እና በጣም ከባድ ወደሆነ ጭንቀት ውስጥ ለመግባት ትንሽ እንደቀረኝ ነገረችኝ። አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ ነበረብኝ። ከስራ እረፍት ወሰድኩ። ሁለተኛ ስራዬን በትህትና ተውኩት። ከአለቃዬ ጋር አወራሁ እና የተወሰነ ሀላፊነት ሊቀንስልኝ ተነጋገርን። ሀኪሜ ድብርትን ሊቀንሱ የሚችሉ መድሀኒቶችን አዘዘችልኝ በተጨማሪም የምክር አገልግሎት መውሰድ ጀመርኩ።

ራሴን ወደ እዚህ የወሰድኩበትን ምክንያት ለማወቅ የሚረዳኝ ሰው ያስፈልገኝ ነበር። አንድ ሰው እንደሆንኩ እና ራሴን መጠበቅ አለብኝ የሚለውን እውነት ወደ ማመን መጣሁ። በጊዜው በጣም ራስ ወዳድነት ይመስላል ግን እውነት እንደሆነ ገባኝ። እኖርበት የነበረውን እረፍት አልባ ህይወት እንድኖር አይደለም የተፈጠርኩት።

እውነት ለመናገር በህይወቴ የነበሩት እንቅስቃሴዎች ዋጋ ያለኝ እና የተፈለኩ አይነት ስሜት እንዲሰማኝ ያደርጉኝ ነበር። ነገር ግን ዋጋዬ በማደርጋቸው ነገሮች ሁሉ እንዳልሆነ ይልቁንም ባለኝ ማንነት እንደሆነ ተምሬያለሁ። ቀስ ብሎ መንቀሳቀስ እና ራሴን መውደድ እንዳለብኝ መማር ያለብኝ ሰዓት ነበር። አንዴ እንዲህ ሲባል ሰምቻለሁ “ሰዎች ነን እንጂ፤ የሰው ስራዎች አይደለንም።” ድምፆቹን ወይም ስራ መብዛቱን ገትቶ መረጋጋት ቀላል አይደለም። ግን አሁን እንዴት ጠቃሚ እንደሆነ ገብቶኛል። የህይወት ጉዞ ለመቀጠል መሮጥ መቀጠል እንዳለባችሁ ከተሰማችሁ ብቻችሁን አይደላችሁም። ልናወራችሁ እንፈልጋለን። ከታች ያለውን ፎርም በመሙላት ከእኛ ጋር ይገናኙ።


ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡


እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡

የእርስዎ ፆታ:
የዕድሜ ክልል:

ተገቢውን አማካሪ እንዲመድብዎት የእርስዎ ፆታ እና ዕድሜ እንጠይቃለን። የአገልግሎት ውሎች & የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ.

እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!