በፍርሃት መኖር

በታሪክ ክፍለ ጊዜ ወደ ጠረጴዛዬ ለመድረስ እየሞከርኩ ነበር እንደዚ ያለኝ፤ ከሃያ አመት በኋላ የዛን ቀን በርገንዲ ሸሚዝ ለብሶ እንደነበር ትዝ ይለኛል። ቃላቱ ከአፉ ከመውጣታቸው በፊት ለማሰብ ትንሽ ጊዜ የወሰደ ይመስላል፡- “ፊትሽን መቼም አልረሳውም። በጣም አስቀያሚ ነው።” አለኝ

ጉልበተኝነት ብዙ የተለያዩ መልኮችን ይይዛል። አንዳንድ ሰዎች በግዳጅ ተቆልፎባቸው ይቀመጣሉ። ሌሎች ደግሞ ይገፋሉ ወይም ይደበደባሉ። አንዳንድ ሰዎች ወደ ክፍል ውስጥ ሲገቡ እና ሁሉም ጀርባውን ይሰጣቸዋል። ለእኔ የቃላት ጥቃት ነበር ሚደርስብኝ “በጣም ደደብ ነሽ” እና “ማንም እንደማይወድሽ ታውቂያለሽ አይደል?” እባል ነበር። አንዳንድ ቀናት ምን እንደምመስል ስዕሎችን እየሳሉ ሲያወሩ እሰማለሁ።

ራስሽን ዝቅ አድርጊ። አንድ ቃል አትናገሪ የማይታይ ለመሆን ሞክሪ ምናልባት እዚህ መሆንሽን ከረሱት ሁሉ ነገር ይቆማል። ነገር ግን አላቆመም።

ምንም የማያቋርጥ ነበር። እነርሱ ስድስት ነበሩ እና እኔ ብቻዬን ስለነበርኩ የዝምታ ቋንቋን በፍጥነት ተማርኩ።ራስሽን ዝቅ አድርጊ። አንድ ቃል አትናገሪ የማይታይ ለመሆን ሞክሪ ምናልባት እዚህ መሆንሽን ከረሱት ሁሉ ነገር ይቆማል። ነገር ግን አላቆመም።

6 ኛ ክፍል ወይም 7ኛ ክፍል ወይም 8ኛክፍል ላይ አልቆመም። 1,200 ተማሪዎች ያሉብት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስገባ ማንም አይተናኮለኝም ብዬ ተስፋ አድርጌ ነበር ነገር ግን ያ ደግሞ አልሰራም። በዚያም ዓመት ወይም በሚቀጥለውም ዓመት ወይም ከዚያ በኋላም አላቆመም።

ከአውቶቡሱ ወርጄ በቻልኩትን ዝግታ ወደ ቤቴ እጓዝ ነበር። ወደ ቤት መድረስ ስለማልፈልግ ሳይሆን ወደ ት/ቤት እስክመለስ ድረስ 18 ሰአታት ብቻ እንደሚቀሩኝ ሳስብ ቀስ እላለው። የቀኑ ምርጥ ሰዓት ለኔ ያቺ ጊዜ ናት፤ ነገር ግን ሰዓቱ ሁል ጊዜ ይሄዳል።

ከተሞክሮ ልናገር የምችለው ፍርሃት ህይወትን የሚያደክም ነገር ነው። እኔ በማታ እንዲሁም ቅዳሜና እሁድ እረፍት ነበረኝ። አሁን ግን በበይነ መረብ አማካኝነት ውሸቶች ገና ከአልጋ ሳንወርድ በየማህበራዊ ገጹ ይደርሱናል እና በዚህ ጊዜ ት/ቤት ለሚማሩ ልጆች ደግሞ ምን ያህል ከባድ እንደሚሆን መገመት እችላለሁ።

አሁን የተረዳሁት ነገር፤ ያኔ እርዳታን ጠይቄ ቢሆን ኖሮ መልስ አግኝ ነበር። ከጉልበተኞች ርቄ ነው ያለሁት ነገር ግን ያኔ በእኔ ላይ ምን እየደረሰ እንዳለ ለአንድ ሰው ተናግሬ ቢሆን ኖሮ ከዓመታት በፊት እራሴን መታደግ እችል ነበር። ብናገር ነገሩ የከፋ ይሆናል ብዬ እሰጋ ነበር። አንድም ቃል ተናግሬ አላውቅም። ነገሩ ካበቃ ከዓመታት በኋላ ነው ለወላጆቼ የነገርኳቸው። ከምወዳቸው አስተማሪዎች አንዱ “እነዚያ ልጆች እያስቸገሩሽ ነው?” ሲል ሲጠይቀኝ አይደለም ብዬ ዋሸሁት።

ማስፈራራት የጉልበተኝነት እና የሌሎች የጥቃት ዓይነቶች አንዱ መገለጫ ነው።

ትልቅ ሰው እንደመሆኔ ማስፈራራት የጉልበተኝነት እንዲሁም የሌሎች አይነት ጥቃቶች አንዱ መገለጫ እንደሆነ ይገባኛል። ሃይል ያለው ተጠቂውን ያገላል። የሷ ሃሳብ ጥቅም እንደሌለው ያሳምናታል። ደግማ ደጋግማ ማንም እንደማይሰማት እሱ ላይ ማንም ሊደርስበት እንደማይችል ታስታውሰዋለች። ምንም እንደማትጠቅሙና ሰው ቢሰማ እንኳን ሊያድናችሁ እንደማይሞክር እንድታምኑ ያደርጉዋችኋል።ጉልበተኞች እና ጥቃት አድራሾች ብቻችሁን እንደሆናችሁና ያ ደግሞ በጣም አደገኛ ቦታ እንደሆነ እንድታምኑ ያደርጓችኋል።

ለእኔ፣ እነዚህ የተናገሯቸው አሰቃቂ ነገሮች ሁሉ እውነት ናቸው ብዬ ማመኔ ራሴን ለማጥፋት እንዳስብ አድርጎኛል። ሰዎች "ራስን ማጥፋት ለጊዜያዊ ችግር ዘላቂ መፍትሄ መስጠት ነው።" ሲሉ እሰማለሁ እኔ ግን ከአክብሮት ጋር በዚህ ቆሻሻ ሃሳብ አልስማማም።

ራሴን ለማጥፋት በተዘጋጀሁበት ጊዜ ከስድስት ዓመታት በላይ በየቀኑ የቃላት እና የስሜት ጥቃት ይደርስብኝ ነበር። ይህ “ጊዜያዊ” ነገር አልነበረም። በዚያን ጊዜ 16 ዓመቴ ነበር፤ ያ ማለት የሕይወቴን ግማሽ ያህል ነበር።

“ምርጥ አባባሎች” ጉልበተኝነት እና ራስን ማጥፋት የመሰሉ ከባድ እና አስፈሪ የሆኑ ነገሮችን ለመጋፈጥ አይረዱሽም። አንድ የሚረዳ ትርጉም ራስን ከማጥፋት ጋር ተያይዞ ከሚታወቀው ድረ-ገጽ ላይ ያገኘሁት ነው፡ “ራስን ማጥፋት ምርጫ አይደለም፤ ነገር ግን ህመማችንን ለመቋቋም የሚረዳ አቅም ሲያልቅ አማራጭ ይሆናል።

የሸክማችን ክብደት በዝቶ ከምንሸከመው አቅም በላይ ሲሆን ያኔ ራስን ለማጥፋት እናስባለን። ያራስ ወዳድ ስለሆንን፤ ቀላል ስለሆነ፤ ወይም ማምለጫ ስለሆነ የምንመርጠው አማራጭ አይደለም። ያ ከመጀመሪያውም አግባብነት በሌለው ትግል የምናሳየው የመጨረሻ ትዕይንት ነው።

አሁን ትልቅ ከሆንኩ በኋላ ሌላ የተማርኩት ነገር አለ። ያኔ እነዛ ጉልበተኛ ልጆች የሰደቡኝን ስድብ እና ድምጻቸውን ከአዕምሮዬ ለማስወጣት በጣም ረጅም ጊዜ እንደሚወስድ ተምሬያለው። ምክኒያቱም አንድን ነገር ተደጋግሞ ስትሰሚው በሃሳብሽ ውስጥ ይቀረጽና ይቀራል። ነገር ግን ጊዜ ቢወስድም ራስን ከዚህ ሃሳብ ነጻ ማድረግ ይቻላል።

የሸክማችን ክብደት በዝቶ ከምንሸከመው አቅም በላይ ሲሆን ያኔ ራስን ለማጥፋት እናስባለን። ያ ራስ ወዳድ ስለሆንን፤ ቀላል ስለሆነ፤ ወይም ማምለጫ ሰለሆነ የምንመርጠው አማራጭ አይደለም።ያ ከመጀመሪያውም አግባብነት በሌለው ትግል የምናሳየው የመጨረሻ ትይዕንት ነው።

ለመጀመሪያ ጊዜ በእኔ ላይ የደረሰውን ይህን እውነተኛውን ታሪክ ለሰው የተናገርኩት በመጨረሻ አመት የዩኒቨርሲቲ ቆይታዬ ነበር። ለአንድ በጣም ጥሩ ጓደኛዬ ስነግረው እየተንቀጠቀጥኩ ስለነበር እጆቼን ይዞ ነው ያደመጠኝ። እስከ ዛሬ ድረስ ሁሉንም የሚያውቀው እርሱ ብቻ ነው።

እነዚያ መጥፎ ሃሳቦች ወደ ጭንቅላቴ በመጡ ቁጥር የማነበው ደብዳቤ ጻፈልኝ። ሌላውን ሁሉ ነገር ስጠራጠር በእጄ መያዝ የምችለው ጠንካራ ነገር የሱ ደብዳቤ ነበር። ለረጅም ጊዜ የእኔ የሕይወት መስመር ነበር። አሁን አሁን ግን ብዙ ጊዜ እንደበፊቱ አውጥቼ ማንበብ እንደሌለብኝ ሳስብ ደስተኛ ነኝ።

እናንተም እንደኔ አይነት ህይወት አሳልፋችሁ ከሆነ የጻፈልኝን ጽሁፍ ላውሳችሁ እችላለው፥ እንዲህ ይላል፥

ድምጾቹን አትስሚያቸው። አንቺ ቆንጆ ነሽ። ጎበዝ ነሽ። ተወዳጅ ነሽ። ብቻሽን አይደለሽም።

እናንተም ተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ አልፋችሁ ከሆነ ወይም ትምህርት ቤት ውስጥ የተናገሩዋችሁ መጥፎ ንግግሮች አሁንም የሚሰማችሁ ከሆነ ብቻችሁን አይደላችሁም። እነርሱ የተናገሩዋችሁን አይደላችሁም። ስለእሱ ማውራት ከፈለጋችሁ እኛ አለን። ከዚህ በታች ባለው ቦታ የመገኛ አድራሻዎትን ብቻ ይሙሉ፣ እና የሆነ ሰው በቅርቡ ያነጋግርዎታል።


ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡


እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡

የእርስዎ ፆታ:
የዕድሜ ክልል:

ተገቢውን አማካሪ እንዲመድብዎት የእርስዎ ፆታ እና ዕድሜ እንጠይቃለን። የአገልግሎት ውሎች & የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ.

እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!