አባቴ የአንተን ሀላፊነት እንድሸከም አታድርገኝ
ልጅ እያለሁ አባቴ ትንሽ እንድናወራ እኛ ሰፈር ወዳለ አንድ መናፈሻ ወሰደኝ። የንግግሩ ዝርዝር አሁንም ግልፅ አልሆነልኝም ነገር ግን ስለሁኔታው ሳስብ የነበረው ስሜት እና ድባቡ ዛሬም ከብዙ አመታት በኋላ እንደገና ሊያስፈራራኝ እና ሊያፍነኝ ይሞክራል። አባቴ ሊያዋራኝ ሲጠራኝ ምን ሊያወራኝ እንደሆነ መገመት አልቻልኩም ነበር። ምን አጥፍቼ እንደሆነ እያሰብኩኝ ነበር። አባቴ ለጉዳዩ ትኩረት እንደ ሰጠው ያስታውቃል። ከዚያም የምንኖርበትን አካባቢ እስከመጨረሻው ትተን እንደምንሄድ እና ከአያቴ ጋር በትንሿ ከተማ እንደምንቆይ ነገረኝ። ሀሳቡ ቢያስከፋኝም አዲስ ነገር እንደሚገጥመኝ ሳስብ ግን ጥሩ ስሜት ተሰማኝ። ይህ የሆነው በልጅነት አለሜ አስከፊውን ቦንብ እስከሚጥልብኝ ድረስ ነበር። ቀጠለና ከእናቴ ጋር እንደተለያዩ እና እኛን ጥሎ ሊሄድ እንደሆነ ነገረኝ። ምንም ያልጠበኩት ነገር ነበር እና በጣም ነበር ያስደነገጠኝ።
አባቴ የራሱን ሀላፊነት ጥሎ ሊሄድ ይችላል ነገር ግን ለእኔ የማስተላለፍ መብት የለውም!
አባቴ፤ የቤተሰባችን አባወራ፣ እኛን ትቶ የመሄዱን እውነት እያጠነጠንኩኝ እያለ እስከዛሬ ቁስለኛ ያደረገኝን ሁለተኛውን ቦንብ አባቴ በድጋሚ ጣለብኝ። እኔ ትንሹ ልጅ የእሱን ሀላፊነት እንድረከብ ጠየቀኝ። ከእኔ የሚጠብቀውን ሲገልፅ የተጠቀማቸውን ቃላት በሙሉ አላስታውስም ነገር ግን የወረረኝን የፍርሃት ስሜት እስከ ህይወቴ ፍፃሜ አልረሳውም። ሽባ የሚያደረግ ፍርሃት ብቻ ሳይሆን ንዴት እና እንቢተኝነት የወጣትነት ልቤን አጥለቀለቀው። በውስጤ የሰጠኝን ሀላፊነት መቀበል ስላልፈለኩኝ የትንሽ ልጅ ነፍስ ስትፀየፍ የምታለቅሰውን ለቅሶ አለቀስኩኝ። ይህ ፍትሃዊ አይደለም! ይህ የእኔ ስራ ሊሆን አይገባም! ይህንን እንድሰራ መጠየቄ አግባብ አይደለም! በዚያን ጊዜ ሀላፊነቱን እንደማልቀበል ነበር የማውቀው። አባቴ የራሱን ሀላፊነት ጥሎ ሊሄድ ይችላል ነገር ግን ለእኔ የማስተላለፍ መብት የለውም! አንዳንዴ መልሼ ሳስብ ለምን ፍርሃቴን ወደ ኋላ በመተው ፈተናውን መቀበል እንዳልቻልኩ አስባለሁ። አባቶቻቸው ወደ ጦርነት ትተዋቸው የሄዱ ወይም የሞቱባቸው እና የቤተሰባቸውን ሃላፊነት በልጅነታቸው እንዲወጡ የተገደዱ ብዙ የወጣት ወንዶች ታሪክ አለ። የእኔ ችግር ምን ነበር? እኔ ደካማ ስለሆንኩ ነው? አሁን ተመልሼ ሳየው ደካማ ሆኜ አይመስለኝም። እነዚያ ልጆች ቤተሰብ ማስተዳደር እንዲችሉ አባቶቻቸው በቅርበት ሆነው ያሳደጓቸው ናቸው። ችግሩ ሲመጣ ሊያስፈራ የሚችል ቢሆንም በተወሰነ መጠን ግን አስቀድመው ዝግጅት ያደረጉ ናቸው። የእኔ አባት ግን ሁልጊዜም ከእኔ የራቀ፣ ትዕግስት የሌለው እና የራሱን አባወራነት እና ቤተሰብ የማስተዳደር ሀላፊነት እንኳን በአግባቡ የማይወጣ ነበር። እኔንም አላዘጋጀኝም ስለዚህ ምንም የማውቀው ነገር አልነበረም። ያስተማረኝ ከሀላፊነት መሸሽ ነበር እና በውስጤ እኔም ሸሸሁት።
እንደኔ ላለ ሮጦ ለሚደበቅ ሰው መፍትሄ አለ?
ይህ ውሳኔዬ የቅርብ ጓደኛም ሆነ የፍቅር ጓደኛ ማፍራት እንዳልችል ገድቦኝ ነበር። በውስጤ ትክክለኛ እና ሰዎች ሊተማመኑት የሚችሉት ሰው መሆን እፈልጋለሁ። ነገር ግን ከባድ ተግዳሮት ይገጥመኛል በተለይም በፍቅር ግንኙነቶቼ በጣም ድብቅ ነበርኩኝ። ባለቤቴ በእኔ መተማመን ስትፈልግ ተነስቼ እንደአባወራ መቆም አለመቻሌ እስከዛሬም ድረስ እያገገምንበት ያለ እጅግ የሚጎዳን ነገር ነው። እንደኔ ላለ ሮጦ ለሚደበቅ ሰው መፍትሄ አለ? አዎ፤ አለ ማለት እችላለሁ ነገር ግን ለውጥ የሚመጣው በዝግታ እና በህመም እንዲሁም የምንፈራውን ነገር በየእለቱ በመጋፈጥ እና ጥሎ ከመሸሽ ይልቅ በውስጣቸው በማለፍ ነው። ለብዙ አመታት እየሸሸሁ እና እየተደበኩኝ ስለኖርኩ ይህ ለእኔ ቀላል አልነበረም። ድክመቴን ለተረዱኝ፣ ይቅርታዬን ለተቀበሉ እና በዘገምተኛው የፈውስ ሂደቴ ከጎኔ ለነበሩ ጓደኞቼ እና ቤተሰቦቼ ያለኝ አክብሮት የተለየ ነው። አሁን ከቀድሞው ይልቅ ወንድ እንደሆንኩኝ አባወራ እንደሆንኩኝ ይሰማኛል ነገር ግን ይህ ብዙ አመታት እና ከሚወዱኝ ብዙ ይቅርታን ጠይቋል። በተለያዩ እናት እና አባት በማደግዎ በሚፈጠሩ አንዳንድ ችግሮች እየተሰቃዩ ነው? ለእናንተም ተስፋ አለ። ጊዜ ሊወስድ ይችላል ነገር ግን እናንተን ለመስማት እና ለመርዳት የፈውሱን መንገድ አብረዋችሁ ለመጓዝ ፍቃደኛ የሆኑ አማካሪዎች አሉ። ከስር ያለውን ቅፅ ይሙሉ እና ወዲያው ከእኛ መልስ ያገኛሉ።
ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡
እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡
እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!