ቆሜ ቀረሁ እንዴ?
ባለፈው አመት ከጓደኛዬ ጋር ወደ አንድ ሰርግ ሄጄ ሙሽራዋ አበባዋን ስትወረውር ቀለብኩት። አስደሳች ነበር። የቀለብኩትን አበባ ለማስቀመጥ ወደ ጠረጴዛው ስሄድ ወደ ሰርጉ አብሬው የመጣሁት ጓደኛዬ አብረውት ለነበሩ ሰዎች የፍቅር ጓደኛው እንዳልሆንኩኝ ባልተገባ መንገድ ሲገልፅ ሰማሁት። ይህም ለብቻው እንዳይሆን ይዞኝ እንደመጣ እንዳስብ አደረገኝ። እናም የማገባበት፤ ያንን ነጭ ቬሎ የምለብስበት ቀን ቅርብ እንዳልሆነ ታወቀኝ። ጓደኛ ብቻ ነን።
የሚገርመው ነገር ሰርግ በጣም እወዳለሁ። ሰርግም መሄድ እወዳለሁ። ለሰርግ ለብሶ እና አጊጦ ከምወዳቸው ሰዎች ጋር ለመደሰት መውጣት እንዲሁም ከሰርግ በፊት በሚዘጋጁ ዝግጅቶች ላይ ተጋብዤ ስገኝ ክብር ይሰማኝ ነበር። ነገር ግን እድሜዬ እየጨመረ ሲመጣ ስለሰርግ ማሰብም ሆነ ሰርግ መሄድ እየከበደኝ መጣ።
መልካም ነገር የሚታገሱ ሰዎችን እንደሚያገኛቸው በተደጋጋሚ ተነግሮኛል። ነገር ግን በጣም ብዙ ታገስኩኝ። የሆነ ደንዝዤ የቀረሁ እና ብቸኝነት የተመቸኝ እንዲሁም እንደጓደኞቼ ማግባት እና እነርሱን መቀላቀል በተከለከልኩበት አለም ታግቼ የቀረሁ ይመስለኛል። መቼ እንደነርሱ መሆን እንደሚፈቀድልኝ አላውቅም። በቃ ይህ እኔ ብቻዬን በምሆንበት ጊዜ ሁሉ የሚከብደኝ ነገር ነው።
ምንም እንኳን ማንም ሰው ብርድልብሴ እየገፈፈ ባያስቸግረኝም ትልቅ ከሆንኩ በኃላ፤ ወደ ቀዝቃዛው ትንሹ አልጋዬ ለብቻዬ መግባት በጣም ያሳምምኝ ነበረ፡፡.
በተሳሳተ መንገድ አትረዱኝ በእርግጥ ብቸኝነት ብዙ ጥቅሞች አሉት። የምፈልገውን ነገር ከማንም ጋር ሳልማከር በፈለኩት ሰዓት በማድረጌ ደስተኛ ነኝ፤ ለማንም ደስታ ስል እኔ ማየት ምፈልገው ፊልም ካለ ሳላይ ባለመቅረቴ፣ ከወንድ ጓደኞቼ ጋር ምንም የጥፋተኝነት ስሜት ሳይሰማኝ አብሬ ማሳለፍ በመቻሌ… ብቻ ብዙ ደስተኛ የሚያደርጉኝ ነገሮች አሉ።
የጓደኞቼን ልጆች ማቀፍ እወዳለሁ እና እናታቸውን ሲያዩ ‹እማዬ› እያሉ ከእኔ እቅፍ ውስጥ ወጥተው ሲሄዱ ብቸኝነቴን ያስታውሱኛል። ምንም እንኳን ማንም ሰው ብርድልብሴን እየገፈፈ ባያስቸግረኝም ትልቅ ከሆንኩ በኃላ ወደ ቀዝቃዛው ትንሹ አልጋዬ ለብቻዬ መግባት በጣም ያሳምምኝ ነበረ። ነገር ግን የእጮኝነት እና የትዳር ሃላፊነቶች ያጓጉኛልም፤ ያስፈሩኛልም።
እጮኝነትን ለመጀመር ለመጠናናት የማላውቃቸውን ሰዎች አግኝቼ አውቃለሁ በጣም ተግባቢ ስለሆንኩኝ የማላውቀውን ሰው ማናገር አይከብደኝም። አብዛኛዎቹ ጓደኞቼ የወደፊት ባሎቻቸውን ባገኙበት ዩንቨርስቲ ለአምስት አመታት አሳልፌለሁ፡፡ ብዙ ወንዶችን ለፍቅር ግንኙነት ቀርቤ አውቃለሁ ነገር ግን አብዛኛዎቹ እኔ ቀሪውን ህይወቴን አብሬ ለማሳለፍ የምፈልገውን አይነት ሰው አልነበሩም። ሆነው እንኳን ቢገኙ ሌላ ግንኙነት ውስጥ ያሉ ወይም የእኔ መሆን የማይችሉ ሰዎች ናቸው። እራሴን ብዙ ጊዜ ብቻዬን አገኘዋለሁ እና በቃ ይኸው ነው? ለዘላለም ለብቻዬ ነው የምሆነው? አምላኬ ምንድነው ያጠፋሁት?
በጣም ብቸኝነት በሚሰማኝ ለሊት ልቤ ቆሜ እንደቀረሁ እየነገረኝ ሲያለቅስ ይሰማኛል።
ቶሎ ካገቡ ጓደኞቼ እኔን ምን እንደሚለየኝ አላውቅም። በጣም ብቸኝነት በሚሰማኝ ለሊት ልቤ ቆሜ እንደቀረሁ እየነገረኝ ሲያለቅስ ይሰማኛል። እነርሱ ከእኔ የተሻለ አቋም አላቸው? ከእኔ የተሻለ ያምራሉ? ከእኔ በላይ ጥሩ ሰዎች ናቸው? ሁሌ ከእኔ የተሻለ ምርጫ ይመርጣሉ? ወይስ ቸኩለው የማይሆን ሰው ነው ያገቡት? ከሚገባቸው ያነሰ? ምርጫ አበዛሁ እንዴ?
እጮኛ ኖሮኝ አያውቅም ማለት አይደለም። እንደውም ከአንዱ ግንኙነት በስተቀር ሌሎቹን ያቆምኩት እኔው እራሴ ነኝ። ወደፊት አብረን እንደምንኖር በመግለፅ ፍቅር እና ተስፋ ተሰጥቶኝ ነበር ግን ፈራሁ ወይም ደግሞ ራስ ወዳድ ነበርኩኝ ወይም ውስጤ አልተዘጋጀም ነበር ወይም ትክክለኛውን ነገር ነበር ያደረኩት። ያደረኩት ነገር ትክክል ይሁን ጥፋት መቼም እንደማላውቅ ይሰማኛል።
ምንም ማድረግ ሳልችል ጊዜ እያለፈብኝ እንዳለ ይሰማኛል። በጥንዶች ተከብቤ እንኳን ብቻዬን እደሆኩኝ ይሰማኛል። ይገርማል ስለራሴ ብዙ ነገር እየተማርኩ ነው። በብቸኝነት እየተሰቃያችሁ ከሆነ አድራሻችሁ ከስር አስቀምጡ። ትክክለኛ ስማችሁን ማስቀመጥ ትችላላችሁ ወይም ደግሞ ሌላ ስም። ከእኛ ቡድን አንድ ሰው በአጭር ጊዜ ይመልስሎታል። ብቸኝነት ሊሰማዎት ይችላል ነገር ግን ብቻዎትን አይደሉም።
ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡
እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡
እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!