ትንሽ ኪሎ ብቻ. . . .

5 ኪሎ ብቻ ልቀንስ ብላችሁ አስባችሁ ታውቃላችሁ? እኔ አውቃለሁ ፤ እናም 5ኪሎ እቀንሳለሁ ብዬ የጀመርኩት (diet) የአመጋገብ ስርዓት ማስተካከል 15 አመታት ፈጀብኝ በዚህም ለመሞት ጥቂት ቀርቶኝ ነበር።

ታዳጊ እያለው በጣም ይሳቅብኝ ነበር።ይሄም በራስ መተማመኔን አጠፋው። በዚህ ደካማ ጊዜዬ ላይ ሆኜ፤ ምንም ሳይደብቅ ምን ምን መስራትና ማድረግ እንዳለብኝ የሚነግረኝ ጓደኛዬ ጋር በግልጽ ኪሎ መቀነስ ያለብኝ እንደሆነ ጠየኩት “ትንሽ ኪሎ ብትቀንሺ” አለኝ። የምፈልገውን ማበረታቻ ሰጠኝ። በሚቀጥለው ቀን አመጋገቤን አስተካከልኩ።

ፍቅርን ቀጭን ከመሆን ጋር አያያዝኩት።

አምስት ኪሎ ለመቀነስ ብዙ ጊዜ አልወሰደብኝም እና ስለ ራሴ ጥሩ ስሜት እንዲሰማኝ አደረገ። ይሄን ያህል ለውጥ ማግኘት እንደዚህ ደስታን ከፈጠረልኝ ሌላ አምስት ኪሎ ብቀንስ በጣም የተሻለ ይሆናል ብዬ አሰብኩ። ክብደቴን እየቀነስኩ በሄድኩ ቁጥር ታዋቂነቴ፥ ጓደኞቼ እና የወንድ ጓደኞቼ እየጨመሩ መጡ - የምፈልጋቸው ነገሮች ሁሉ። በፍጹምነት ተጠመድኩ እና ከተስተካከለ ነገር ውጪ ሌላ ነገር አልፈልግም ነበር። በየቀኑ ስፖርት ሰራለሁ፤ 1 ኪሎ ሜትር ሮጣለሁ፤ 1000 ሲት አፕ ሰራለሁ እና የበላሁትን የትኛውም ካሎሪ ካለ እንዲቃጠል ኤሮቢክስ ሰራለሁ።

ከውጭ ሁሉንም ተቆጣጥሬ ያለሁ እንዲመስል ብዙ ጥሬያለሁ።

ከስድስት ወራት በኋላ በጣም ያዞረኝ ስለነበር ሀኪም ጋር ሄድኩኝ የአመጋገብ ስርዓት መዛባት (anorexia) እንዳለብኝ ነገረኝ። “47 ኪሎ የሚመዝን ሰው እንዴት የአመጋገብ መዛባት ይኖርበታል?” ብዬ ነበር ያሰብኩት። የተባልኩትን የሰሙ ሰዎችም ይሄንኑ ነበር የጠየቁት። ሌሎች ደግሞ የአመጋገብ ስርዓት መዛባት(anorexia) ያለብኝ እንደማልመስል ነገሩኝ። ስለዚህ ወደፊት ለመቀጠል ወሰንኩ እና በደንብ የአመጋገብ ስርዓት መዛባት (anorexia) በሽተኛ ሆንኩኝ።

ለሚቀጥሉት 15 ዓመታት በጣም ታገልኩ፤ ሁለቴ ከመሞት ተርፌያለሁ። በህክምና ክትትል ስር ነበርኩ እና ለረዥም ጊዜ የማማከር አገልግሎት ተጠቃሚ ሆኛለሁ። ሆኖም ግን ከውጭ ሁሉንም ተቆጣጥሬ ያለሁ እንዲመስል ብዙ ጥሬያለሁ። በጣም ደካማ የሆንኩት ለሁለተኛ ጊዜ ሆስፒታል ስገባ ነው። የልብ ችግር እንዳለብኝ እና ሰውነቴ ውስጥ የውሃ ማነስ እንዳለ ተነገረኝ። ለሞት በጣም ቀርቤ ነበር። 37 ኪሎ የሆነውን ሰውነቴን ለማጠንከር በቀን 3000 ካሎሪ በግድ በሆዴ በኩል በቱቦ ይሰጠኝ ነበር። ግን ቱቦውን በአልጋዬ ስር በኩል ወደ ቆሻሻው እንዲወርድ አደርግ ነበር እና ባገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ ስፖርት ሰራ ነበር።

ግን እዛው ሆስፒታል አልጋዬ ላይ ሆኜ ነገሮች መቀየር ጀመሩ። ብቻዬን ነበርኩ እና ከራሴ ጋር ፊት ለፊት ተጋፈጥኩ። ወደማመን ያመጣኋቸውን ብዙ ውሸቶችን ዘርዝሬ ፤ በልቤ ከማውቃቸው እውነታዎች ጋር ጽፌ ማነጻጸር ጀመርኩ። መጻፍ በቀጠልኩ ቁጥር እውነቱን የበለጠ የማወቅ ጉጉት አደረብኝ። ከዛ በኋላ ረዥም የማማከር አገልግሎት፤ የህክምና እርዳታ እና በቤተሰቦቼ እና ባሌ ጸሎት እና ፍቅር የአመጋገብ ስርዓት መዛባት (anorexia) ሊሰርቀኝ የነበረው ህይወቴ ተመለሰ።

ከልክ ያለፈ ዉፍረት እና የአመጋገብ ስርዓት መዛባት አጋጥሞታል? አሁን ላይ ተስፋ የመቁረጥ እና የጭንቀት ስሜት እየተሰማችሁ ይሆናል ግን ብቻችሁን አይደላችሁም። ከስር ያለውን ቅጽ በመሙላት፤ ቡድናችን ውስጥ ያለ ሰው ያናግራችኋል ታሪካችሁን ያዳምጣል እና ተስፋ እንድታገኙ ይረዳችኋል።


ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡


እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡

የእርስዎ ፆታ:
የዕድሜ ክልል:

ተገቢውን አማካሪ እንዲመድብዎት የእርስዎ ፆታ እና ዕድሜ እንጠይቃለን። የአገልግሎት ውሎች & የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ.

እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!