የአልኮል ሱስ

የአልኮል ሱሰኛ የሆንኩት የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ሳለሁ ነበር፤ በእርግጥ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለመዝናናት ይጠጣሉ፤ ነገር ግን እኔ የምጠጣው ለመዝናናት አልነበረም፤ እኔ የምጠጣው ለመመሳሰል ነበር። ከፍተኛ የሆነ ከማህበረሰቡ ጋር የመቀላቀል ፍርሃት ችግር ስለነበረብኝ የዶርም ክፍሌን ለቅቄ መውጣት ይከብደኛል፤ ጓደኛ ለማፍራት ወይም ሴትን ለማናገር ምንም በራስ መተማመን አልነበረኝም። የሚወዱኝ ቤተሰቦች እና ጓደኞች እንዳሉኝ ባውቅም ሁልጊዜ ብቸኝነት ይሰማኝ ነበር፤ እራሴን እጠላለሁ፤ አልኮል ለጥቂት ሰዓታት ቢሆንም አሪፍ፣ በራሱ የሚተማመን እና ተግባቢ ሰው ወደመሆን የሚቀይረኝ ምትሀታዊ መጠጥ ነበር፤ ህመሜን ያደነዝዘዋል፤ ለሁለት አመት ያህል አልኮል በፍፁም ያልጠበኩት መድሃኒቴ ሆነ።

ከዩኒቨርስቲ ለስራ ከወጣሁ እና ዲግሪዬን ከጨረስኩኝ በኋላ ከሱሴ አንጻር የተቀየረ ነገር ቢኖር የአጠጣጤ ድግግሞሽ ብቻ ነበር። ከቤተሰቦቼ ጋር ስለምኖር አልኮል ወደ ቤት ይዤ መሄድ አልችልም ነበር፤ ስለዚህ ከቤት ውጪ መጠጣት የምችልበትን አጋጣሚ ሁሉ እጠቀም ነበር። የቱንም ያህል ርቀት ማሽከርከር ቢጠበቅብኝም የምችለውን ያህል እጠጣ እና ልክ መሪ ስጨብጥ እራሴን ወይም ሌላን ሰው እንዳልገድል የሚቻለኝን ሁሉ አደርጋለሁ። አልኮል የሚሰጠኝን ስሜት ማሳደድ በህይወቴ በጣም የሚያስደስተኝ ነገር ሆነ፤ በጣም ራስ ወዳድ ከመሆኔ የተነሳ ሙሉ ለሙሉ ሰክሬ ስነዳ እንኳን ምንም ግድ አይሰጠኝም ነበር፤ አደጋ ላይ ስለምጥላቸው ሰዎች እና አንዳንዴም በመኪናው ውስጥ ከእኔ ጋር ስለሚሆኑ ጓደኞቼ እንኳን ግድ አይለኝም ነበር።

በሂደት ሴቶችን ለማናገር አልኮል ላይ መደገፌን አቁሜ ከምመኛት አይነት ልጅ ጋር የፍቅር ግንኙነት ጀመርኩኝ፤ ሁለት ሴት ልጆች ያሏትና ያላገባች ሴት ናት፤ እና የፍቅር ግንኙነቴ ሀላፊነት ብቻ ሳይሆን የአባትነት ተምሳሌትም የመሆን ሃላፊነት አሳደረብኝ፤ ከህፃናቶቹ ጋር ስንሆን ባልጠጣም እነሱ ከሌሉ ታሪኩ የተለየ ነው የሚሆነው። ቀለበት አሰርን፤ ምንም እንኳን በፍቅር ተማርኬ ቀለበት ባስርና እጮኛዬም እንደምታፈቅረኝ ባውቅም ይህ ብቻ ለእኔ በቂ አልነበረም። አሁንም እራሴን አልወድም ነበር፤ መወደድ እንደሚገባኝም አልቀበልም ወይም አላምንም ነበር። ስለዚህ ህይወቴ ምንም ጥቅም እንደሌለው መጠጣቴን ቀጠልኩ፤ ምክንያቱም ለእኔ እኔ ምንም የማልረባ ሰው ነበርኩኝ። ሁሌ ማክሰኞ ማታ ጥንብዝ ብዬ እንደምሰክር ማንም አያውቅም ነበር፤ ስሰክር ስለምቆጣው ቁጣ ማንም አያውቅም፤ እራሴን ምን ያህል እንደምጠላ ማንም አያውቅም ነበር፡፡

ከአደጋው በኋላ ህይወቴ ሊጠፋ ስለነበር አልኮልን ብቻ ጥፋተኛ ማድረግ እንደሌለብኝ ገባኝ፤ እኔ ነኝ፤ጥፋተኛው እኔ ነኝ

ለሰርጋችን ቀን ሁለት ወር ሲቀረው የእጮኛዬን ልደት አክብረን ማታ ስምንት ሰዓት አካባቢ እሷ ከምትኖርበት ቤት ወጣሁ፤ ሙሉ ለሙሉ ሰክሬ ነበር። ከቤቷ ብዙም ርቄ ሳልሄድ ሙዚቃ ለመቀየር ጎንበስ ብዬ ቀና ስል ከመብራት እንጨት ጋር ተጋጨሁ፤ የመብራቱ እንጨት መኪናዬ ላይ ወድቆ እንዴት ጉዳት እንዳልደረሰብኝ አልገባኝም፤ ከሳምንት በኋላ ሰርጌ ተሰረዘ። ከአደጋው በኋላ ህይወቴ ሊጠፋ ስለነበር አልኮልን ብቻ ጥፋተኛ ማድረግ እንደሌለብኝ ገባኝ፤ እኔ ነኝ፤ ጥፋተኛው እኔ ነኝ፡፡ እርዳታ እንደመጠየቅ ፋንታ ከማህበረስብ ጋር የመቀላቀል ችግሬን ችላ ያልኩት እኔ ነኝ፤ መጠጣቴን ከሁሉም ሰው የደበኩት እኔ ነኝ፤ እራሴን ያልወደድኩት እና በዛም ምክንያት እራሴን አጥፍቼ የነበርኩት እኔው እራሴ ነኝ። አልኮል በህይወቴ ችግር ነበር ነገር ግን አልኮል የዋናው ችግሬ ውጤት ነው፤ ዋናው ችግሬ እራሴ ነነበርኩኝ።

ሱስ ሁሌም ወደ ሱሰኛው ይሄዳል፤ ሰዎች የሆነ ነገር ሱስ የሚይዛቸው ከችግሮቻቸው ጋር በሚጋፈጡበት ጊዜ ወይም ሊያመልጡ በሚሞክሩበት ጊዜ ነው፡፡ ሱስ የሚፈጠረው አንድ ሰው የሚፈራውን ነገር ከመጋፈጥ ይልቅ በሚሸሽበት ጊዜ ነው፤ ችግሮቼን መቀብል ስጀምር የአልኮል ሱስ ችግሬን አሸነፍኩት።

ለአራት ወራት በአልኮል ማገገሚያ ቆየሁ፤ ማንም ስላስገደደኝ አልነበረም፤ ነገር ግን የአልኮል ሱስ የሚያስከትለውን አስከፊ እውነታ መጋፈጥ ስለፈለኩኝ ነበር። እራሴን ትሁት ለማድረግ፣ ለመስማት እና ከእኔ በባሰ ችግር ውስጥ ያለፉ ሰዎችን የጥበብ ቃል መስማት ፈልጌ ነበር። ለጓደኞቼ እና ለቤተሰቦቼ ግልፅ በመሆን ችግሬን ተጋፈጥኩት፤ ከሰዎች ጋር በመገናኘት በግልፅ የማስበውን በመናገር፣ በምን እንደምቸገር በመግለፅና ማንም ሰው ስለእኔ ሲጠይቀኝ እውነቱን መናገር ጀመርኩኝ። ያለብኝን ከፍተኛ የሆነ ከማህበረሰቡ ጋር የመቀላቀል ፍርሃት ችግር ሙያዊ እገዛ እንዲደረግልኝ በማድረግ በአልኮል መታከሜን አቆምኩኝ። በማውራት፣ በማሰብ እና እራሴን እንደጠቃሚ በመንከባከብ ችግሮቼን ተጋፈጥኳቸው፤ እራሴን በእውነት ለመውደድ ተማርኩኝ።

በብቸኝነት ከሱስ ማገገም አይቻልም፤ የሚረዳን ማህበረሰብ ያስፈልጋል። በምንም አይነት ሱስ ውስጥ ቢሆኑ ሱሰኛ ሆነው መቅረት የለቦትም። ወደ ሱስ የመራችሁ ማንኛውም አይነት ነገር ውስጥ ቢሆኑ ብቻዎትን መጋፈጥ የለቦትም። አንድ አማካሪ ከእርሶ ጎን ሆኖ አብሮዎት መጓዝ አለበት። አድራሻዎትን ከስር ያስቀምጡ እና ወዲያው እናገኞታለን። ይህንን ለብቻዎት መጋፈጥ የለቦትም። ከታች ያለውን ፎርም ይሙሉና ከእኛ አንድ ሰው በተቻለ ፍጥነት መልስ ይሰጦታል። ሚስጥርዎ የተጠበቀ እና ሁልጊዜም በነፃ የሚሰጥ አገልግሎት ነው። አማካሪዎቻችንን ባለሙያዎች አይደሉም፤ ሰዎችን በመንገዳቸው በሀዘኔታ እና በማክበር ለማገዝ ፍቃደኛ የሆኑ ተራ ሰዎች ናቸው። እባክዎ ከእርሶ ጋር ግንኙነታችን እንዲቀጥል ከስር ያለውን ፎርም ይሙሉ? ካልተጠቀሰ በስተቀር ሁሉንም መሙላት ይጠበቅቦታል።


ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡


እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡

የእርስዎ ፆታ:
የዕድሜ ክልል:

ተገቢውን አማካሪ እንዲመድብዎት የእርስዎ ፆታ እና ዕድሜ እንጠይቃለን። የአገልግሎት ውሎች & የግል መረጃ ደህንነት ፖሊሲ.

እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!