የእርሷን ፍቃድ ፍለጋ
መቼ ነው ሻይ ቡና ለማለት እንድንገናኝ የምትፈልጊው ይሄ በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ለማወራቸው(ለምጀናጀናቸው) ሴቶች የማቀርበው ዋነኛ እና የመጨረሻ ጥያቄዬ ነው፡፡ እናም በጠየኩ በአንድ ሰዓት ውስጥ ምላሽ የማላገኝ ከሆነ ለማቃጥለው ጊዜ አይመጥኑም ብዬ ስለምደመድም ወዲያውኑ ግንኙነቴን አየር ላይ አቋርጠዋለሁ፡፡
ይህ አካሄድ የእኔን የተቃራኒ ጾታ የፍቅር ግንኙነት ህይወት ከ5 ዓመት በላይ ወስኖታል፡፡ ከዩንቨርስቲ ከተመረኩኝ በኋላ ስራ ለመጀመር ወደ ትልቋ አዲስ አበባ ጎራ አልኩኝ፡፡ በሰዓቱ አይኖቼ በጣም አስፍተው የሚመለከቱ፣ ውስጤ በጉጉት እና ፍላጎት የተሞላ ነገር ግን በዛው ልክ የፈራሁ ነበርኩኝ፡፡ በግሌ እስከዛሬ ብቻዬን ኖሬ አላውቅም ከትምህርቱ ዓለም ውጪ ማለቴ ነው እናም ከገሃዱ ዓለም ምን መጠበቅ እንዳለብኝ አላውቅም ነበር፡፡ ፍርሃቴ ምንም ያህል ቢኖርም እንኳ አዲስ የህይወቴን ምዕራፍ ለመጀመር እና ከዩንቨስቲ ተማሪዎች ካለፈ አዲስ ማህበረሰብ ጋር ለመቀላቀል በጣም ጓጉቼ ነበር ነገር ግን በሆነ ምክንያት ከሁሉ ይበልጥ ከተቃራኒ ጾታ ጋር የፍቅር ግንኙነት ለመጀመር ይበልጡኑ ጓጉቼ ነበር፡፡
ታዲያ በህይወቴ ከዚህ ቀደም ከሴት ልጅ ጋር የፍቅር ግንኙነት ውስጥ ገብቼ ስለማላውቅ ምን መጠበቅ እንዳለብኝ አላውቅም ነበር ነገር ግን ምን እንደምፈልግ አውቅ ነበር፡፡ በዚህም ፍላጎቶቼ በጣም ከመጽናታቸው የተነሳ ለአካላዊ እርካታ ብቻ ሲባል ከተቃራኒ ጾታ ጋር የፍቅር ግንኙነት መጀመር አንደኛ ቅድሚያ የምሰጠው ነገር ሆነ፡፡
በማህበራዊ የትስስር ገጾች የተቃራኒ ጾታ የፍቅር ግንኙነቶችን መጀመር ሁሉን ነገሬን ወደሚወስድብኝ መንገድ መራኝ፡፡ አስቸጋሪውን የፍቅር ግንኙነት ለመጀመር የሚደረገውን ጉዞ ለማቅለል ቴክኖሎጂ የሰጠኝን እድል እየተጠቀምኩ እንዳለሁ ባስብም ነገር ግን ለራሴ እየዋሸሁት ነበር፡፡ በዋነኝነት የምፈልገው ነገር ቢኖር ሰዎች ከእኔ ጋር በአካል ግንኙነት ለመፍጠር ማራኪ ወይም የምስብ ሆኜ አግኝተውኛል ወይ የሚለውን በፍጥነት በመገምገም እራሴን ተቀባይነት ከማጣት መከላከል እና መጠበቅ ነበር፡፡
ያንን ብቻ ነበር የምፈልገው ያም ብቻ ነበር የሆነው
በማህበራዊ የትስስር መንገድ የማገኛት እያንዳንዷ ሴት እኔ በምናቤ የማሰላስላት አንድ ተጨማሪ ሴት ነበረች፡፡ እንደ እቃ ነበር የማስባት እናም ድርጊቴን ሁሉም ነጠላ ወንዶች ከሚያደርጉት የተለየ አይደለም የማደርገው በማለት ለማሳመን እጥር ነበር፡፡ ቢሆንም ግን በየጊዜው በእያንዳንዷ በማገኛቸው ሴቶች ልክ እኔን የሚሰማኝ ሃፍረት እና ጸጸት ይጨምር ነበር፡፡ ከሴቶች ጋርም ስለሚኖር ጤናማ ግንኙነት ያለኝ አመለካከት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበላሸ አና እየተጣመመ መምጣት ጀመረ፡፡
በማህበራዊ የትስስር መንገድ የማገኛት እያንዳንዷ ሴት እኔ በምናቤ የማሰላስላት አንድ ተጨማሪ ሴት ነበረች፡፡
ይህ አካሄዴም ከከተማ ወደ ከተማ በምቀያይርበትም ጊዜ አብሮኝ ቀጠለ ነገር ግን ጊዜ በሄደ ቁጥር ለመለወጥ ያለኝም ፍላጎት እየጨመረ መሄድ ጀመረ፡፡ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከነበርኩበት ሱስ መውጣትና መመለስን ፈለኩ ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ ምንም ያክል እንኳን የተቻለኝን ጥረት ባደርግም ወደ አጥፊው ሱሴ ተመለስኩኝ፡፡ ወደ ማህበራዊ ትስስር ገጾች ተመለስኩኝ ምንን ፍለጋ? በእርግጥ አላውቅም ነበር፡፡ ከዛም ቀስ በቀስ ራሴን በጥልቀት የመመልከት እና የማሰላሰል ጉዞ በማድረግ በዚህ ዓይነት መንገድ ለምን እሄድ እንደነበር መረዳት ጀመርኩኝ ይህም ከሴቶች ተቀባይነትን እና ዋጋን ለማግኘት ከመፈለግ ነበር፡፡ ሌላ ነገር ያረካኛል ብዬ አስብ ስላልነበረ በሴቶች ውስጥ የማገኘውን ጊዜያዊ እርካታ እና ደስታ አሳድድ ነበር፡፡
በስተመጨረሻም የምመኘው እና የምፈልገው ዋጋ እና ተፈላጊነት ከእንደዚህ አይነት ግንኙነቶች ፈጽሞ ሊገኙም ሆነ ሊመጡ እንደማይችሉ ተረዳሁኝ፡፡ ዋጋ ቢስ የመሆን ስሜትን ለማሸነፍ እየጣርኩ የነበረው በሰዎች እና በነገሮች ዘንድ ተቀባይነትንና ተወዳጅነትን በማግኘት አንጂ ከብቸኛው እና ትክክለኛ ዋጋዬ እና ውድነቴ ሊገኝበት ከሚችልበት - ከፈጣሪዬ - አልነበረም፡፡
አሁን ላይ በጓደኞቼ እርዳታ የራሴን እና የሌሎችን እውነተኛ ዋጋ በማወቅ ላይ እያደኩኝ ነው፡፡ ተጠያቂነት እና ለራሴ ያለኝ ታማኝነት ነው ከአጥፊው ልማዴ ነጻ እያወጣኝ ያለው፡፡ እናንተስ በእንደዚህ አይነት የህይወት ልምምድ ውስጥ እየተመላለሳችሁ ከሆነ ብቻችሁን አይደላችሁም፡፡ ይህንን ብቻችሁን መጋፈጥ አይጠበቅባችሁም! በእኛ ዘንድ የሚገኙ አማካሪዎች ሊረዱአችሁ በዚህ አሉ:: ምክከራችን ሙሉ በሙሉ ደህንነቱ የተጠበቀ እና በነጻ የሚሰጥ ነው:: ከታች የሚገኘውን ቅጽ በመሙላት በቅርብ ጊዜ ውስጥ ከእኛ ከሆኑ አማካሪዎች ይሰማሉ፡፡
ይህንን ብቻውን መጋፈጥ የለብዎትም ፡፡ ከአማካሪ ጋር ይነጋገሩ ፣ ሚስጥራዊ ነው ፡፡
እኛ ከእርስዎ ጋር መገናኘት እንድንችል እባክዎ ከዚህ በታች ያለውን ቅጽ ይሙሉ ፡፡ ካልተገለጸ በስተቀር ሁሉም መስኮች ያስፈልጋሉ ፡፡
እነዚህ ጉዳዮች ለመቋቋም ከባድ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡ እራስዎን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ ፣ እባክዎን ይህንን ያንብቡ!